Get Mystery Box with random crypto!

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ eliasshitahun — የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤
የቴሌግራም ቻናል አርማ eliasshitahun — የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤
የሰርጥ አድራሻ: @eliasshitahun
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.54K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥም በድምጽ በጽሑፍ
ምርጥ አንድ ገፅ
በሰው የተነበቡ ግጥሞች
የአሪፍ መጽሐፍ ጥቁምታ
አጫጭር ታሪኮች
የሀሳብ ንሸጣዎችን ከሁሉም እንቃርማለን፡፡ፈጠራዎችን እንደመምባቸዋለን፡፡የኤልያስንም የሌሎችንም ከያነያንን ስራ እንታደማለን፡፡ ስለሀሳብ እንሰማለን፡፡ እናሰላስላለን፡፡ ሰክረን ሳይሆን ሰክነን፡፡ሀሳብን እናስበዋለን፡፡
ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት 👉 @Elias2127

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 19:40:06
558 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:26:06 "አልወድሽም"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~
"ቋ ቀጭ ቋ ቀጭ"
ህይወት መጣች ሳቋን ይዛ
አልቆየችም እንደ ጤዛ ...
እቅፍ ሳም አንገቴ ስር
ለወጠችኝ በቀይ ምስር ....
ተሸጥኩላት ባገኘችው
ተሞኘሁኝ እንዳለችው....
(አልወድሽም)

ቋ ቀጭ ቋ ቀጭ
ጫማዋን አወለቅች
ልብሷን አወለቀች
አብራኝ ተኛች አወላልቃ
እኔ ከፋኝ እርሷ ስቃ
(አልወድሽም)

ህልሟ እንደጠፋባት እንደልጃገርድ
ወዴት ለመሄድ ነው ከአልጋዬ የምወርድ?
ወዴት ?

ህይወት ራሷ ናት አንገቴን ብትቀላ
በሰው ተመስላ::
ህይወት ራሷ ናት ውሸት ብታሰላ
ሞቴን ያስመኝችኝ ፍቅር አስመስላ::

ህይወት ውሸት አሞኝችኝ
ገላ ነፍሴን ቀደድችኝ
አጎነበስኩ እንደስንዴ
ይወጋኛል ዕንባ ቀንዴ
"ህይወት በቃኝ" ስል ሰማችኝ
ሳቀችብኝ እያየችኝ::
(አልወድሽም)

እጠጋበት ባጣም
እተኛበት ባጣም
እሞትበት ባጣም
እስቅበት ባጣም
አለቅስበት ባጣም
እናቅበት ባጣም
እንደወደድ ባጣም
እደርስበት ባጣም
ከእቅፍሽ ባልወጣም
ወዴትም ባልሸሽም
ማርያም ምስክሬ ህይወት አልወድሽም::

አልወድሽም

አልወድሽም

አልወድሽም
947 views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:14:54 "እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?”
ኤልያስ ሽታኹን
(የምጥ ዋዜማ)
~ ~ ~ ~ ~
ማብራራት ቢድክምም ሰው ይድን ዘንድ መብራራት ራሱ መብራራቱ ግድ ይላል::

script writing ላይ ከህይወት የተቅዳ form አለ::

"With out character there no need.with out need there is conflict. With out conflict there is obstacle. With out obstacle there is no resolution."

የመኖርን እውነት መረዳት ግድ ነው::
ሁላችንም ተመሳሳይ መንገድ ነው ምንሄደው::

ከአባቴ ከወጣው ቢሊየን ዘር መሐል የኔ ሰው መሆን እድል ነው? ወይስ መረገም?

እግዜር ለምን ሰራኝ? እንጃ::
Metaphysical ጥያቄ አይቀሬ ነው::

የመፈጠርህ ጥያቄ መልሱ ከተፈጠርክ ወዲያ መመለሱ ነገሩን ያከረዋል::

በተሳካልን በኩል አይተን ስናበቃ "ለዚህ ነው የተፈጠርከዉ" የሚል አድናቆት ይከበናል::
እውነት ለርሱ ነውን? እጠይቃለሁ::

በኔ ስላለፉ ግን የኔ ስላልሆኑ ቅሪተ ኑሮዎቼ እጠይቃለሁ::

የመከበሬ ዘመን እንደወረቀቶቼ ተጠቅለለው የሚጣሉት መች ነው?
የቱ ነኝ?
"ትሁቱ - እብሪተኛው"
"ጥጋበኛው - አቀርቃሪው"
"ባለ ብዙ ሚስት ወይስ ብቸኛው"
"ልጅ ያለኝ ያውም ሴት ልጅ ወይስ ልጅ ናፋቂው"
"ከሀዲው ወይስ ታማኙ"
"ገጣሚው ወይስ ድምፁ የሚያምረው"
"ክርስቲያኑ ወይስ አስመሳዩ"
"ቆንጆው ወይስ ግርማ ሞገስ እንጂ መልክ እኮ የለውም"
ይሄን ሁሉ ሰው ብሎኝ ያውቃል?
ደንግጬም አፍጥጭም አውቃለሁ::

ማን ይሉኛል?

ክርስቶስ "ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል?"
በየተራ ነገሩት እርሱ ያልሆነውን ሰው ነህ የሚለውን ነገሩት::
በነርሱ አላዘንም
"እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?"
አሁን ነው መፋጠጥ::
የነርሱ መልስ ሊያስከፋም ሊያስድስትም ይችላል:: አላሰፍሩትም::
"አንተማ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ"
እዚህ ጋር
"ስጋና ደም አልገለጠልህም" ን ሰማን :: እውነተኛው እኛን የሚያውቀን የሰማይ አባታችን መሆኑን ልብ ይሏል::

ንጉሥ ባልሆን መዋዕለ ዜና ባይፃፍልኝ ግድ የለኝም:: (አልልም)
እኖርበት መሬት እንጂ እናገረው ምሬት ማሳየት አልሻም::
በርካታ ቃለ መጠይቅ ትጠርቼ ቀረሁ::
ለምን?
እና...እወደድበት ዘንድ መርጬ ልናገር
እና...እከበር ዘንድ ስሌት ልቀባጥር ነው?
እና...ይሄን እወቁልኝን ላበዛ ነው? ከዛስ?
በሰው ሰማይ ፀሀይ ልሆን ከዛስ አንደኛ ለመባል?
ከዛስ?
945 views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:11:58 "ስለነዚህ ሙዚቃዎች ምን ታስቢያለሽ?"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ስለነዚህ ሙዚቃዎች ምን ታስቢያለሽ?"

ቋንቋቸው ሳይገባን ስለምንጨፍርባቸው?

ምን እንደሚሉ ሳናውቅ ስለምንገረምባቸው?

ጠረጴዛ እየመታን ስለደንስባቸው?

የቀለለንን እና በቃል የያዝነው ቦታ ላይ ጠብቀን አብረናቸው ስለምንጮሀቸው?

"ለኔ ነው" በሚል ትርጉም ከማይገናኝ ውሽቅ ሀዘናችን ጋር ስለምናገናኛቸው?

ትክሻችንን ስለሰበቅንባቸው?
ወገብ ስለትያያዝንባቸው?

ግጥሞቻቸው ምን እንደሚሉ ሳንውቅ ገና ሰከፈቱ ስለምንጮኽላቸው?

ስለነዚህ ስለማይገቡን ግን እንደገቡን ስለሚሰሙን ሙዚቃዎች ምን ታስቢያለሽ?

መኖር እንደዛ ይሆን?
907 views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:58:00 "Purpose on mistake"
ኤልያስ ሽታኹን
(የመጨረሻው መንደርደሪያ)
~ ~ ~ ~ ~
ከኔ ይልቅ የሄድኩት መንገድ ዋጋው ከበረ?
የረገጠኩትን "እናውቃለን" ባዩች ሚዛን ይዘው አሰቃዩኝ::

በሰው ለመወደድ የምንደክመው ሁሉ ፍሬው ከድካሙ ያንሳል::
ስንት አዋጣለሁ?
ገመናዬን ተርኬ ክብር ፈልጌ ይሆን?
በሚስጥሬ ሀዘን ሰብስቤ እግዜርን ልገጥመው ይሆን?
መንገዴ መንገድ እንዳልነበረ ይታወቅልኝ ዘንድ ወሰንኩ::
ስዋሸው እያወቀ ዝም ያለኝ ጏደኛዬ ላድነቀው ልርገመው?
ለምን ውሽታም አላለኝም?
ለምን?
ፈርቶኝ አይደል ወይስ ሳስቶልኝ?
የዋሸዋቸው ለምን ተዋሹሉኝ::

"ለመኖር ምን ያስፈልጋል?"
"በሰዎች መወደድ" ነው መልሴ::
"ባትወደድስ?"
"እዋሻለሁ"
"ለመወደድ ውሽት?"
"እውነት ሆኜ ትወድኛለህ?"
"አዎ"
"ውሸታም:: ይሄም እኔ እንደወድህ ውሸት ነው"

እነዚህ ሁሉ ለምን?
እንጃ?
ለምን ዋሸሁ?
ምን ለማግኘት?
ምን ላለማጣት?
ለምን ለመዋሸት ሰዎች ተደላደሉልኝ::

አንቺ ግን ከውደድሽኝ
መርቂኝ "ያየህ ይርገምህ" በይኝ
መርቂኝ "ውሸትህን ትደበቅበት ቀዳዳ ባጣህ" ብለሽ::

ያኔ እምሆነው ሳጣ ምን እንደምሆን ይገባኝ ይሆን?

ዋጋ ፍለጋ የተሰደድኩብት በርሀ ውጦ አስቀረኝ:: "ስንት አወጣለሁ?" ክርክሬ ላይ ችሎት ቆምኩ:: ተሸነፍኩ::
ያውም በዝረራ::
356 views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:00:10 “Poker face”
ኤልያስ ሽታኹን
(የመጨርሻዎቹ መንደርደሪያ)
~ ~ ~ ~ ~ ~
ካርታ ተጫዋች ከሆንሽ ይቺ ቃል አትጠፋሽም::
ሲበሉም ሲበሉም አለማሳየት አይነት:: ምንም ስሜትን ለተጋጣሚ አለማካፈል:: የፊት ሸር::
“Poker face”
"an impassive expression that hides one's true feelings.
a person with a poker face."

ፊቴ ፀጉር በዛው መሰለኝ ምን እንድሚሰማኝ አይታይም:: ስቀልድ ነው::

ድብቅ ነኝ:: ያልተጠጉኝ አይነኩኝም:: አይነቁኝምም::
በተቻለኝ አቅም የሰዎች ጥያቄ ለመሆን ስለምፈልግ ምንም ስሜት ያለማሳየት ሸር ለምጃለሁ::

ስወድም ስጠላም
ሲወዱኝም ሲጠሉኝም እዛው ፊቴ ላይ:: ውስጤ አሳ ነባሪው እንደሚረብሸው ባህር ይናወፃል::

ለምን?

ሳሳያቸው የናቁኝ
ስገለጥላቸው የሸረደዱኝ
ስስቅ ያቀለሉኝ
"እሺ" ከማለቴ የተነሳ የረሱኝ ብዙዎች ናቸው::

ግን ግድ የሌለኝ አይመስልሽ::
እያንዳንዷ ቅፅበቴን አጤናታለሁ::
የራሴ "ጌቴሴማኒ" አለችኝ:: አልቅሼባት ተጨንቅባት የምወጣት:: ከዛም እንደበረታ ሰው "ተግታችሁ ፀልዩ" እንጂ የምልበት::

ስሜቴን ስላላየሽው ውሸታም ነው አትበይኝ::
ደሞም ፀሀፊ መሆንን አትርሺ jim carrey አይደለሁም:: ፊቴ ሁሉን አይናገርም::

ግን እምወድሽም እምናፍቅሽም ነበርኩ::
"ስንት ሴት እንደዚህ አልክ?"
"የምወዳቸውን ሁሉ"

ጋሽ ስብሐት
"ካገቧቸው መሐል የትኛዋን አብልጠው ይውዳሉ?"
"ሁሉንም"
(ታዳሚው አሽካካ)
"ከየትኛዋ ጋር ያሳለፉትን አብልጠው ይውዳሉ?"
"ኖሬው የለ ለምን እነግርሀለሁ"
ስብሐት እንደዘበት የሚያወራውን ግን አሳቢያን አያልፉትም::

ያገኘሁትን የመጋደም ጥረት አልነበርኝም:: መወደዴን ማስመስከረም አልሻልም::
"እውድሻለሁ" ብዬ እብለት አልነበረኝም::

እኩዮቼ ላይ የማየው አባዜ አለ:: ሲለያዩ ጠብቆ "የኖርነው ውሽት ነው" የሚል "denial"ውስጥ መግባት::
እውነት የተሰማውን ቅፅበት ያላስቀጠለ ሁሉ ውሽታም ነውን?
እውነት አንድ ነገር እውነት ለመባል የቆየበት ጊዜ ይወስነው ይሆን?

እርግጥ
ስህተት አለብኝ::
መወድዴን ዘላለማዊ ማስመሰሌ::
(ያንቺ እጅ ቢኖርበትም አልከስሽም::)
"ሰርክ አዲስ ጅረት ፍቅር አለኝ" ብዬ ተስፋም ህልምም መቀላቀሌ እርግማን ያሰጠኛል::

እንጂ
"እኔ እሰቀልልሀለሁ" ብሎ ዶሮ ሳይጮህ መካድ
"እሰቀልልሀለሁ" ን ውሸት ያደርገው ይሆን?

ውሸቴን አልነበረም:: ወሸቴ ፍቅሬ አያልቅም ማለቴ ነው::
772 views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:46:12 "Trauma within drama"
ኤልያስ ሽታኹን
(የልደት ዳር ጨዋታ)
~ ~ ~ ~ ~
* ሞት ይመስለኝ ነበር ክፉ ነገር:: ለካ አሟሟት ነው::
አባቴን በፀብ እንደተኳረፍን አረፈ::

አላሳደግኝም::
ግን አልጎድለብኝም አልልም::
እንኳን አባት ጎረቤትም ያጎድላል::
ከሌላ ለወለዳቸው ታላላቆቼ ሁሉን ሆኖላቸዋል:: ልክ ነው :: እናት አልነበራቸውምና::

ሰዎች ውበቱን የሚናገሩልት በብዛት የሚቆጠር ሱፍ የነበረው:: ደረባባ:: ቢናገር የሚሰማ:: ቢቆጣ የሚፈራ:: እርቅ በእጁ ሽማግሌ ነበር::
እቃ የሚበርከትለት እንዲያውም "ቴፑ" 39 አመት እንደሰማባት ሲያወራ ሰምቻለሁ:: ሽቅርቅር ነው::

ቤት ከሱ የወሰድነው ነገር ብዙ ነው:: ውስጡን ለቄስ ውጪ ውበት:: ሰው የሚድር የራሱን ትዳር ያላቆመ:: የተበላሸ የሰው ልጅ መካሪ የራስ ልጅ ላይ ስነፍ:: ለሰው መሬት ለመግዛት ዋስ ለቤቱ ሩብ ካሬ የሌለው::

ብቻ እንደተጣላን ሞተ:: ለሊቱን ሙሉ ሲያጣጥር አይቸዋለሁ:: አጥንቱ ሲገተር ጥርሱ መግጠም ሲከብደው አይቸዋለሁ::
ጀምበር መውጫ ንጋት ላይ ነፍሱ ተለየችው::
ብቻዬን ከአስክሬኑ ጋ አለቀስኩ::
በብዙ ስሜት መሐል አንባሁ:: እንቀጠቀጣለሁ:: " ይቅር ብዬሀለሁ" ለማለት አቅም አለነበረኝም::

ህመሜን ስላልነገርኩት ንደድኩ እንጂ:: ቅያሜዬን በውል ሳላስርዳው ሞተ:: እውነቱን ሳልያስረዳኝ ሄደ:: እንድልጅ ሳይሆን እንደእኩያ አለቅስኩ:: እሱ አብሮኝ አይሁን እንጂ ስልሱ የማስበው አብሮኝ ኖሯልና:: እሱ እናቴ ላይ አጠፋ የምለውን እኔ ዛሬ ስንት ሴቶች ላይ አርጌ አየሁት::

ወንዶች አባቶቻቸውን ይርግማሉ:: ግን እንደአባቶቻቸው ናቸው:: ነገ የልጄ እናት እና ልጆቼ የሚወቅሱኝ እውንታቸውን ሳስብ የረገምኩትን አባቴን አዘንኩለት::

ግን ለመታረቅም ለመጣላትም መኖር ነበርበት::

በጊዜ ሂደት
ታቦቴን የተነጥኩ መቅደስ ነፍሴን ይዤ እኳትናለሁ::
በምናገረው በምፅፈው ሁሉ ድሞ ምን አጣ ይሆን?ስል እረበሻለሁ::

እንማን ይቀብሉኛል?
እንማን ይርቁኛል?
"እኔ ቦታ የለኝም
የቆምኩበት አያውቀኝም" እንዳለ ኪሩቤል::

ራሴን ለሰዎች ኖሬያለሁ ብልም ውሸት ነው::
ለምወዳቸው በሚል ሰበብ ለራሴ አልነበርም ወይ የኖርኩት::
ግጥምን ከድኜ
ፂሜን ላጭቼ
ፀጉሬን አንስቼ
ድምፄን ዘግቼ
ንባቤን ቀድጄ
ስሜን አንስቼ ራሴን ሳየው
የት አለሁ?

በርግጥ ውሸት ብቻ አይደለንም:: እውነትም እንደዛው:: ቅልቅል መርዝ ነን:: ላንዱ መድኃኒት ላንዱ ገዳይ::

ተከታይ ካበጀን ወዲያ መልሰን የተከተለንን ጀሊል እንከተለዋለን:: እሱ ሚወደውን ለበሰን አውርተን አጊጠን እንታያለን:: የሚከተሉንን የመከተል ድራማ ላይ እንገባለን::

በ 14 አመቴ ይመለኛል:: እቤት ሽሮ በልተን ተኛሁ::

ወንድሜ ማታ አምሽቶ ሲመጣ ስጋ እጁ ላይ ነበር:: ሲጠበስ ሸተተኝ::
"ሁሉም በልተዋል"
እናቴ "አዎ አንተ ብላ"ትለዋለች
አቃተኝ:: እንደባነንኩ አስመሰልኩ:: ደነገጡ ::
"ምነው?"
"አባዬ ሲሞት አየሁ" እናቴ አማተበች::

ልተኛ ልመለሰ ወደትራስ መንገዴን ጀመርኩ::
"አቢ" ተጣራ ወንድሜ :: ጎሽ ብላ ሊሉኝ ነው::
"በል:: እንኳን ነቃህ ና ብላ"

ያኔ በስራሁት ያኔ ተሰራሁ::
ድራማዬን ሰርቼ ስጋዬን በልቼ ተኛሁ::
"አልወደውም" በምለው ሰው ስም እንዴት ታሪክ ሰራሁ:: እንዴት? በስሙ በላሁ?

በትንሹ ልቤ ሸረኛ ሆኜ ራሴን አየሁት::

የውነት ሞቷል ዛሬ:: ግን አልበላበትም::

ስሙንም አላነሳም:: ዛሬም አንስቼው ከሆነ አላውቅም....
845 views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 23:07:42 "ምፃጉ ነፍሴ....."ውሸት" አልጋህን ተሽክመህ ሂድ"
ኤልያስ ሽታኹን
(የልደት ዳር ጨዋታ)
~ ~ ~ ~ ~
ጭብጨባው ነው ጠላቴ
ድምፄን ያስመለከኝ
ፅሁፌን መስመር የመረጠልኝ
በጎደለ ሞላ ተጫወትኩ::

ሴቶች ተባብረው የወደዱትን ህዝቡ የተቀበለውን "ኤልያስ አደባባይ" በምኔ ልጠረው::
በቆርቆሮ
በግምብ
ብሸምበቆ::

ያሬድ ደደብ ካለው መመህሩ ይልቅ ከትል መማሩ ምንይሉታል? ከራሴ ሸሽቼ ትል ከሆነ ወሸቴ ምን ጠብቄ ነው የማንጋጠው?

ሁሉም ጏደኞቼ ስልክ ይዘው እኔ ቀረሁ::
ነገርኩት:: አንድ ጏደኛዬን "ቤት አይገዙልኝ የላቸውም" አልኩት:: ገዛልኝ Techno ::
እቤት ስሮጥ ደረስኩ::
"በትወና ትምህርትቤት ተሸለምኩ" ሳውጠነጥናት የነበርች ውሸት ጥያቄ አመጣች::
"ምስክር ወረቀት የለውም ስንተኛ ወጥተህ ነው?"
"ትቼው መጥቼ ነው" ቢሮ
"በል እሺ" እቤት እሱን ለማረሳሳት ብዙ ውሸት ተሰራ::

አርብ ለት ስሰግድ ሴት ካየሁ ላብ እስኪፈልቀኝ እሰግዳለሁ::
ሰንበት ትምህርትቤት ድምፁ የሚያምር ልጅ ሲዘምር በጉራ መልክ አጨበጭባለሁ::

አንድ ቦታ
የሚያውቀኝ ሰው እንዳለ ካወቅኩ ውስጤ ይርመጠመጣል:: የሰውነቴ መደንዘዝ የተረጋጋ ሰው ያስመስልኛል::
ውሸታም ነኝ::
እግኝበት ክብር ካለ ከመዋሸት የሚያግደኝ ነገር አለበረም::
እንደቀልድ "እወድሻለሁ" ብዬ የሰው ተስፋ እሆናለሁ::
"እንደወዶቹ አይደለህም" ለመባል ያለፈጠርኩት የለም::
Room ውስጥ ፀጥ ብሎ እስከመትኛት::
(ዋጥ አርጌ አምሮቴን)

"እደወላለሁ" ከዛ እንደምጠበቅ እያወቅኩ መተው::
"እመጣለሁ" ብዬ መቅረት:: ከዛ በሷ ኩርፊያ ውስጥ "ምን ያህል እንደምፈለግ ማረጋገጥ"::

ስንቱን ተስፋ ያስቆርጥኩ
ስንቱን የዋሸሁ
ሀኪም ቤት ያስገባሁ
እኔ በካድኩት ወንድ በቃኝ ያስባልኩ
ዋሾ መልኬን አሳምሬ የምኖር የገዛ እባቤ የነደፈኝ ነኝ::

በሰዎች መሐል የተረሳሁ ከመሰለኝ ሽንቴ ሳይመጣ እንሳለሁ::

አልጋህን ይዘህ ሂድ እንደተባለ ምፃግዑ ውሽቴን የት ይዤ ልሂድ ተሸክሜ:: ረጅም ዘመን ያኖረኝን ወሸቴን::
960 views20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 00:02:10 ፀሀይ ነበረኝ
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~ ~
እናቴ ጉልበት ላይ በድረቴ ቃኘኝ
ምድሩን አያለሁ ፀሀይ እኔን ሲያየኝ::

ጀርባዬን እርቃኔን የመታችኝ ጀምበር
ማደጌን ጠብቃ የለችም ከኔ በር
የእናቴ መዳፍ በባዝሊን የታሸ
ማደጌን ጠብቆ ምነው ዛሬ ሸሸ::

የት አለ "እሹሩሩ" የእናቴ መዚቃ የትናንት እቅፌ
በሺ ዘፈን የለም ዛሬ ግን እንቅልፌ::
የት ሄደች ፀሀዬ? የልጅነት ወዳጅ
በተራዬ ሆንኩኝ
የሰው ጀምበር አሳሽ ሰው ሰው አሳዳጅ::

የረሳዋት ፀሀይ የናቅኳት ዋጋዋን
ጀርባ የሰጠዋት ሰጠችኝ ጀርባዋን
1.1K views21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:24:32 Shampagne life vs Wine life
ኤልያስ ሽታኹን
(የልደት ዳር ጨዋታ)
~ ~ ~ ~ ~
ውልደቱን እና ሞቱን ብቻ የነገረን ታላቁ መጽሐፍ የክርስቶስን ጉርምስና ሸሽጎናል::
ነገርየው አለምታወቁ ጣጣው ብዙ ነው::
ምን አሳለፈ? ከማን አሳለፈ? ከሀሊውን ለማወቅ ተማሪውን ኢየሱስ መረዳት ግድ ይለናል:: ትልቁን ክርስቶስ ለመቀበል ልጅነቱ ያሻናል::

ልጅነት እኔ
ጭንቅላቴ ቅርፁ ስለሚያሰጠላ ሴቶች ከሚወዷቸው የክፍላችን ወንዶች መጨረሻ ነኝ:: ሴቶቹ እኔን ከመርሳታቸው የተነሳ "እንደሴት ይቆጥሩኝ ይሆን" እል ነበር::

ፀጉሬ ደጋግሞ ከመቅመሉ ብዛት ቆዳዬ ቆስሎ ሰርክ የምላጭ ወዳጅ አደረግኝ:: ንፁህ ፀጉር ያውም ረጅም መች እንደሚኖረኝ ሳስብ አደግሁ:: ግን አልተሳካልኝም:: በጆሮ ግንዴ ድንገት እጄን ስልከው ቅማል አገኛለሁ:: ከነተበው ሹራቤ ላይ እኩዮቼ አንስተው ሲጥሉልኝ ምድር ብትውጠኝ ደስታዬ:: መላጨት ስራዬ ሆነ:: ከዛ ከአካሌ ጋር አብሮ የማይሄደው ጭንቅላት ቅሌ መታየቱ መከራ:: "ማንጎ ጭንቅላት" ነበር ስሜ::

ከጨለማ ቀናት ባንዱ ቀን
መልከጥፉነቴ የሰጠኝን ጨለማነት ድንገት ጭብጭባ ፀሀይ እወጣልኝ::
ተወንኩ ተጨበጨብለኝ
ገጠምኩ
እንግሊዘኛ ክርክር
በሁሉም የትምህርት ቤቱ ሁሉም ሆንኩ::

የናቁኝ ሴቶች ትምህርት ቤቴ ሲጨበጨብ አዩኝ:: (ለካ አለ ብለው-ለካ ወንድ ብለው-ለካ ኤልያስ ብለው) አዩኝ::

በፍጥነት ራሴን እንደሻምፓኝ በጠበጥኩት በሰው ሁሉ ፊት ሊያሳየኝ የሚችለውን መክሊት ፈለኩት::

ታየሁ ግን መታየቴ አለዘለቀም::

ቡዛየሁ ተጣላኝ:: መታኝ ሴት ፊት::
ዳግም ሴት ፊት ስሜ ጠፋ::
እቤት ወንድሜን ትግል ጀመርኩ "ውሹ" ካልተማርኩ:: ቤት "ከመመዝገብህ በፊት እዛ እንዳያምህ እዚሁ ስፒሊት ውረድ" ተባልኩ:: በስቃይ ዘመን ፈጅቶብኝ ወረድኩ:: እሱን እስክወርድ ቡዛየሁን ረሳሁት::
ሳልማር ቀረሁ::

ብቻ መኖር የኃይል ሚዛን እንደሆን የገባኝ በጠዋት ነው::

ክበብ ውስጥ እንደምክትል ምክትል ስቆጠር በእውነት ሰበብ የቦታ የይገባኛል ክርክር ጀመርኩ::

እውቀት መስሎኝ ወዳጄን ከወዳጆቹ ጋር አማሁት:: (በርግጥ ትንሽ እውነት ነበረኝ) ብቻ
አቋም መግለጫ ይመስል ተንትኜ አማሁት::
ግን ቀደተውኝ ኖሮ ነገረኝ:: አንደሰማ እወቅኩ:: ልቤ እንደሌባ ቤት ሲበረበር ትሰማኝ::
አብረውኝ ያሙት አሁን ወዳጆቹ ናቸው::

እኔስ እንደእብድ ምን አይሆንኩ እንድሆንኩ እስከምላውቅ ህይወቴ እንደሻምፓኝ ናጥክት:: ታየሁ ለቅፅበትም ቢሆን:: ግን ወይን መሆን ነው መኖር :: ሰክኖ መጣፈጥ:: እስኪረሱ መቀመጥ ከዛም ሲገኙ መጣፈጥ:: ከዛም ልጅና እናት ተማክረው የጠመቁትን ለመሆን መከራ::
ግን የነርሱ ምርጡ እንዲመጣ የነበረው ወይን ማለቅ አለበት:: ኑ ወይኔን ቶሎ እንጨርስ!
1.1K views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ