Get Mystery Box with random crypto!

'ምፃጉ ነፍሴ.....'ውሸት' አልጋህን ተሽክመህ ሂድ' ኤልያስ ሽታኹን (የልደት ዳር ጨዋታ) ~ | የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤

"ምፃጉ ነፍሴ....."ውሸት" አልጋህን ተሽክመህ ሂድ"
ኤልያስ ሽታኹን
(የልደት ዳር ጨዋታ)
~ ~ ~ ~ ~
ጭብጨባው ነው ጠላቴ
ድምፄን ያስመለከኝ
ፅሁፌን መስመር የመረጠልኝ
በጎደለ ሞላ ተጫወትኩ::

ሴቶች ተባብረው የወደዱትን ህዝቡ የተቀበለውን "ኤልያስ አደባባይ" በምኔ ልጠረው::
በቆርቆሮ
በግምብ
ብሸምበቆ::

ያሬድ ደደብ ካለው መመህሩ ይልቅ ከትል መማሩ ምንይሉታል? ከራሴ ሸሽቼ ትል ከሆነ ወሸቴ ምን ጠብቄ ነው የማንጋጠው?

ሁሉም ጏደኞቼ ስልክ ይዘው እኔ ቀረሁ::
ነገርኩት:: አንድ ጏደኛዬን "ቤት አይገዙልኝ የላቸውም" አልኩት:: ገዛልኝ Techno ::
እቤት ስሮጥ ደረስኩ::
"በትወና ትምህርትቤት ተሸለምኩ" ሳውጠነጥናት የነበርች ውሸት ጥያቄ አመጣች::
"ምስክር ወረቀት የለውም ስንተኛ ወጥተህ ነው?"
"ትቼው መጥቼ ነው" ቢሮ
"በል እሺ" እቤት እሱን ለማረሳሳት ብዙ ውሸት ተሰራ::

አርብ ለት ስሰግድ ሴት ካየሁ ላብ እስኪፈልቀኝ እሰግዳለሁ::
ሰንበት ትምህርትቤት ድምፁ የሚያምር ልጅ ሲዘምር በጉራ መልክ አጨበጭባለሁ::

አንድ ቦታ
የሚያውቀኝ ሰው እንዳለ ካወቅኩ ውስጤ ይርመጠመጣል:: የሰውነቴ መደንዘዝ የተረጋጋ ሰው ያስመስልኛል::
ውሸታም ነኝ::
እግኝበት ክብር ካለ ከመዋሸት የሚያግደኝ ነገር አለበረም::
እንደቀልድ "እወድሻለሁ" ብዬ የሰው ተስፋ እሆናለሁ::
"እንደወዶቹ አይደለህም" ለመባል ያለፈጠርኩት የለም::
Room ውስጥ ፀጥ ብሎ እስከመትኛት::
(ዋጥ አርጌ አምሮቴን)

"እደወላለሁ" ከዛ እንደምጠበቅ እያወቅኩ መተው::
"እመጣለሁ" ብዬ መቅረት:: ከዛ በሷ ኩርፊያ ውስጥ "ምን ያህል እንደምፈለግ ማረጋገጥ"::

ስንቱን ተስፋ ያስቆርጥኩ
ስንቱን የዋሸሁ
ሀኪም ቤት ያስገባሁ
እኔ በካድኩት ወንድ በቃኝ ያስባልኩ
ዋሾ መልኬን አሳምሬ የምኖር የገዛ እባቤ የነደፈኝ ነኝ::

በሰዎች መሐል የተረሳሁ ከመሰለኝ ሽንቴ ሳይመጣ እንሳለሁ::

አልጋህን ይዘህ ሂድ እንደተባለ ምፃግዑ ውሽቴን የት ይዤ ልሂድ ተሸክሜ:: ረጅም ዘመን ያኖረኝን ወሸቴን::