Get Mystery Box with random crypto!

ፀሀይ ነበረኝ ኤልያስ ሽታኹን ~ ~ ~ ~ ~ ~ እናቴ ጉል | የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤

ፀሀይ ነበረኝ
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~ ~
እናቴ ጉልበት ላይ በድረቴ ቃኘኝ
ምድሩን አያለሁ ፀሀይ እኔን ሲያየኝ::

ጀርባዬን እርቃኔን የመታችኝ ጀምበር
ማደጌን ጠብቃ የለችም ከኔ በር
የእናቴ መዳፍ በባዝሊን የታሸ
ማደጌን ጠብቆ ምነው ዛሬ ሸሸ::

የት አለ "እሹሩሩ" የእናቴ መዚቃ የትናንት እቅፌ
በሺ ዘፈን የለም ዛሬ ግን እንቅልፌ::
የት ሄደች ፀሀዬ? የልጅነት ወዳጅ
በተራዬ ሆንኩኝ
የሰው ጀምበር አሳሽ ሰው ሰው አሳዳጅ::

የረሳዋት ፀሀይ የናቅኳት ዋጋዋን
ጀርባ የሰጠዋት ሰጠችኝ ጀርባዋን