Shampagne life vs Wine life ኤልያስ ሽታኹን (የልደት ዳር ጨዋታ) ~ ~ ~ ~ ~ ውልደቱን እና ሞቱን ብቻ የነገረን ታላቁ መጽሐፍ የክርስቶስን ጉርምስና ሸሽጎናል:: ነገርየው አለምታወቁ ጣጣው ብዙ ነው:: ምን አሳለፈ? ከማን አሳለፈ? ከሀሊውን ለማወቅ ተማሪውን ኢየሱስ መረዳት ግድ ይለናል:: ትልቁን ክርስቶስ ለመቀበል ልጅነቱ ያሻናል:: ልጅነት እኔ ጭንቅላቴ ቅርፁ ስለሚያሰጠላ ሴቶች ከሚወዷቸው የክፍላችን ወንዶች መጨረሻ ነኝ:: ሴቶቹ እኔን ከመርሳታቸው የተነሳ "እንደሴት ይቆጥሩኝ ይሆን" እል ነበር:: ፀጉሬ ደጋግሞ ከመቅመሉ ብዛት ቆዳዬ ቆስሎ ሰርክ የምላጭ ወዳጅ አደረግኝ:: ንፁህ ፀጉር ያውም ረጅም መች እንደሚኖረኝ ሳስብ አደግሁ:: ግን አልተሳካልኝም:: በጆሮ ግንዴ ድንገት እጄን ስልከው ቅማል አገኛለሁ:: ከነተበው ሹራቤ ላይ እኩዮቼ አንስተው ሲጥሉልኝ ምድር ብትውጠኝ ደስታዬ:: መላጨት ስራዬ ሆነ:: ከዛ ከአካሌ ጋር አብሮ የማይሄደው ጭንቅላት ቅሌ መታየቱ መከራ:: "ማንጎ ጭንቅላት" ነበር ስሜ:: ከጨለማ ቀናት ባንዱ ቀን መልከጥፉነቴ የሰጠኝን ጨለማነት ድንገት ጭብጭባ ፀሀይ እወጣልኝ:: ተወንኩ ተጨበጨብለኝ ገጠምኩ እንግሊዘኛ ክርክር በሁሉም የትምህርት ቤቱ ሁሉም ሆንኩ:: የናቁኝ ሴቶች ትምህርት ቤቴ ሲጨበጨብ አዩኝ:: (ለካ አለ ብለው-ለካ ወንድ ብለው-ለካ ኤልያስ ብለው) አዩኝ:: በፍጥነት ራሴን እንደሻምፓኝ በጠበጥኩት በሰው ሁሉ ፊት ሊያሳየኝ የሚችለውን መክሊት ፈለኩት:: ታየሁ ግን መታየቴ አለዘለቀም:: ቡዛየሁ ተጣላኝ:: መታኝ ሴት ፊት:: ዳግም ሴት ፊት ስሜ ጠፋ:: እቤት ወንድሜን ትግል ጀመርኩ "ውሹ" ካልተማርኩ:: ቤት "ከመመዝገብህ በፊት እዛ እንዳያምህ እዚሁ ስፒሊት ውረድ" ተባልኩ:: በስቃይ ዘመን ፈጅቶብኝ ወረድኩ:: እሱን እስክወርድ ቡዛየሁን ረሳሁት:: ሳልማር ቀረሁ:: ብቻ መኖር የኃይል ሚዛን እንደሆን የገባኝ በጠዋት ነው:: ክበብ ውስጥ እንደምክትል ምክትል ስቆጠር በእውነት ሰበብ የቦታ የይገባኛል ክርክር ጀመርኩ:: እውቀት መስሎኝ ወዳጄን ከወዳጆቹ ጋር አማሁት:: (በርግጥ ትንሽ እውነት ነበረኝ) ብቻ አቋም መግለጫ ይመስል ተንትኜ አማሁት:: ግን ቀደተውኝ ኖሮ ነገረኝ:: አንደሰማ እወቅኩ:: ልቤ እንደሌባ ቤት ሲበረበር ትሰማኝ:: አብረውኝ ያሙት አሁን ወዳጆቹ ናቸው:: እኔስ እንደእብድ ምን አይሆንኩ እንድሆንኩ እስከምላውቅ ህይወቴ እንደሻምፓኝ ናጥክት:: ታየሁ ለቅፅበትም ቢሆን:: ግን ወይን መሆን ነው መኖር :: ሰክኖ መጣፈጥ:: እስኪረሱ መቀመጥ ከዛም ሲገኙ መጣፈጥ:: ከዛም ልጅና እናት ተማክረው የጠመቁትን ለመሆን መከራ:: ግን የነርሱ ምርጡ እንዲመጣ የነበረው ወይን ማለቅ አለበት:: ኑ ወይኔን ቶሎ እንጨርስ! 1.1K views19:24