Get Mystery Box with random crypto!

“Poker face” ኤልያስ ሽታኹን (የመጨርሻዎቹ መንደርደሪያ) ~ ~ ~ | የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤

“Poker face”
ኤልያስ ሽታኹን
(የመጨርሻዎቹ መንደርደሪያ)
~ ~ ~ ~ ~ ~
ካርታ ተጫዋች ከሆንሽ ይቺ ቃል አትጠፋሽም::
ሲበሉም ሲበሉም አለማሳየት አይነት:: ምንም ስሜትን ለተጋጣሚ አለማካፈል:: የፊት ሸር::
“Poker face”
"an impassive expression that hides one's true feelings.
a person with a poker face."

ፊቴ ፀጉር በዛው መሰለኝ ምን እንድሚሰማኝ አይታይም:: ስቀልድ ነው::

ድብቅ ነኝ:: ያልተጠጉኝ አይነኩኝም:: አይነቁኝምም::
በተቻለኝ አቅም የሰዎች ጥያቄ ለመሆን ስለምፈልግ ምንም ስሜት ያለማሳየት ሸር ለምጃለሁ::

ስወድም ስጠላም
ሲወዱኝም ሲጠሉኝም እዛው ፊቴ ላይ:: ውስጤ አሳ ነባሪው እንደሚረብሸው ባህር ይናወፃል::

ለምን?

ሳሳያቸው የናቁኝ
ስገለጥላቸው የሸረደዱኝ
ስስቅ ያቀለሉኝ
"እሺ" ከማለቴ የተነሳ የረሱኝ ብዙዎች ናቸው::

ግን ግድ የሌለኝ አይመስልሽ::
እያንዳንዷ ቅፅበቴን አጤናታለሁ::
የራሴ "ጌቴሴማኒ" አለችኝ:: አልቅሼባት ተጨንቅባት የምወጣት:: ከዛም እንደበረታ ሰው "ተግታችሁ ፀልዩ" እንጂ የምልበት::

ስሜቴን ስላላየሽው ውሸታም ነው አትበይኝ::
ደሞም ፀሀፊ መሆንን አትርሺ jim carrey አይደለሁም:: ፊቴ ሁሉን አይናገርም::

ግን እምወድሽም እምናፍቅሽም ነበርኩ::
"ስንት ሴት እንደዚህ አልክ?"
"የምወዳቸውን ሁሉ"

ጋሽ ስብሐት
"ካገቧቸው መሐል የትኛዋን አብልጠው ይውዳሉ?"
"ሁሉንም"
(ታዳሚው አሽካካ)
"ከየትኛዋ ጋር ያሳለፉትን አብልጠው ይውዳሉ?"
"ኖሬው የለ ለምን እነግርሀለሁ"
ስብሐት እንደዘበት የሚያወራውን ግን አሳቢያን አያልፉትም::

ያገኘሁትን የመጋደም ጥረት አልነበርኝም:: መወደዴን ማስመስከረም አልሻልም::
"እውድሻለሁ" ብዬ እብለት አልነበረኝም::

እኩዮቼ ላይ የማየው አባዜ አለ:: ሲለያዩ ጠብቆ "የኖርነው ውሽት ነው" የሚል "denial"ውስጥ መግባት::
እውነት የተሰማውን ቅፅበት ያላስቀጠለ ሁሉ ውሽታም ነውን?
እውነት አንድ ነገር እውነት ለመባል የቆየበት ጊዜ ይወስነው ይሆን?

እርግጥ
ስህተት አለብኝ::
መወድዴን ዘላለማዊ ማስመሰሌ::
(ያንቺ እጅ ቢኖርበትም አልከስሽም::)
"ሰርክ አዲስ ጅረት ፍቅር አለኝ" ብዬ ተስፋም ህልምም መቀላቀሌ እርግማን ያሰጠኛል::

እንጂ
"እኔ እሰቀልልሀለሁ" ብሎ ዶሮ ሳይጮህ መካድ
"እሰቀልልሀለሁ" ን ውሸት ያደርገው ይሆን?

ውሸቴን አልነበረም:: ወሸቴ ፍቅሬ አያልቅም ማለቴ ነው::