Get Mystery Box with random crypto!

'Purpose on mistake' ኤልያስ ሽታኹን (የመጨረሻው መንደርደሪያ) ~ ~ | የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤

"Purpose on mistake"
ኤልያስ ሽታኹን
(የመጨረሻው መንደርደሪያ)
~ ~ ~ ~ ~
ከኔ ይልቅ የሄድኩት መንገድ ዋጋው ከበረ?
የረገጠኩትን "እናውቃለን" ባዩች ሚዛን ይዘው አሰቃዩኝ::

በሰው ለመወደድ የምንደክመው ሁሉ ፍሬው ከድካሙ ያንሳል::
ስንት አዋጣለሁ?
ገመናዬን ተርኬ ክብር ፈልጌ ይሆን?
በሚስጥሬ ሀዘን ሰብስቤ እግዜርን ልገጥመው ይሆን?
መንገዴ መንገድ እንዳልነበረ ይታወቅልኝ ዘንድ ወሰንኩ::
ስዋሸው እያወቀ ዝም ያለኝ ጏደኛዬ ላድነቀው ልርገመው?
ለምን ውሽታም አላለኝም?
ለምን?
ፈርቶኝ አይደል ወይስ ሳስቶልኝ?
የዋሸዋቸው ለምን ተዋሹሉኝ::

"ለመኖር ምን ያስፈልጋል?"
"በሰዎች መወደድ" ነው መልሴ::
"ባትወደድስ?"
"እዋሻለሁ"
"ለመወደድ ውሽት?"
"እውነት ሆኜ ትወድኛለህ?"
"አዎ"
"ውሸታም:: ይሄም እኔ እንደወድህ ውሸት ነው"

እነዚህ ሁሉ ለምን?
እንጃ?
ለምን ዋሸሁ?
ምን ለማግኘት?
ምን ላለማጣት?
ለምን ለመዋሸት ሰዎች ተደላደሉልኝ::

አንቺ ግን ከውደድሽኝ
መርቂኝ "ያየህ ይርገምህ" በይኝ
መርቂኝ "ውሸትህን ትደበቅበት ቀዳዳ ባጣህ" ብለሽ::

ያኔ እምሆነው ሳጣ ምን እንደምሆን ይገባኝ ይሆን?

ዋጋ ፍለጋ የተሰደድኩብት በርሀ ውጦ አስቀረኝ:: "ስንት አወጣለሁ?" ክርክሬ ላይ ችሎት ቆምኩ:: ተሸነፍኩ::
ያውም በዝረራ::