Get Mystery Box with random crypto!

'ስለነዚህ ሙዚቃዎች ምን ታስቢያለሽ?' ኤልያስ ሽታኹን ~ ~ ~ ~ | የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤

"ስለነዚህ ሙዚቃዎች ምን ታስቢያለሽ?"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ስለነዚህ ሙዚቃዎች ምን ታስቢያለሽ?"

ቋንቋቸው ሳይገባን ስለምንጨፍርባቸው?

ምን እንደሚሉ ሳናውቅ ስለምንገረምባቸው?

ጠረጴዛ እየመታን ስለደንስባቸው?

የቀለለንን እና በቃል የያዝነው ቦታ ላይ ጠብቀን አብረናቸው ስለምንጮሀቸው?

"ለኔ ነው" በሚል ትርጉም ከማይገናኝ ውሽቅ ሀዘናችን ጋር ስለምናገናኛቸው?

ትክሻችንን ስለሰበቅንባቸው?
ወገብ ስለትያያዝንባቸው?

ግጥሞቻቸው ምን እንደሚሉ ሳንውቅ ገና ሰከፈቱ ስለምንጮኽላቸው?

ስለነዚህ ስለማይገቡን ግን እንደገቡን ስለሚሰሙን ሙዚቃዎች ምን ታስቢያለሽ?

መኖር እንደዛ ይሆን?