Get Mystery Box with random crypto!

'አልወድሽም' ኤልያስ ሽታኹን ~ ~ ~ ~ 'ቋ ቀጭ ቋ ቀጭ | የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤

"አልወድሽም"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~
"ቋ ቀጭ ቋ ቀጭ"
ህይወት መጣች ሳቋን ይዛ
አልቆየችም እንደ ጤዛ ...
እቅፍ ሳም አንገቴ ስር
ለወጠችኝ በቀይ ምስር ....
ተሸጥኩላት ባገኘችው
ተሞኘሁኝ እንዳለችው....
(አልወድሽም)

ቋ ቀጭ ቋ ቀጭ
ጫማዋን አወለቅች
ልብሷን አወለቀች
አብራኝ ተኛች አወላልቃ
እኔ ከፋኝ እርሷ ስቃ
(አልወድሽም)

ህልሟ እንደጠፋባት እንደልጃገርድ
ወዴት ለመሄድ ነው ከአልጋዬ የምወርድ?
ወዴት ?

ህይወት ራሷ ናት አንገቴን ብትቀላ
በሰው ተመስላ::
ህይወት ራሷ ናት ውሸት ብታሰላ
ሞቴን ያስመኝችኝ ፍቅር አስመስላ::

ህይወት ውሸት አሞኝችኝ
ገላ ነፍሴን ቀደድችኝ
አጎነበስኩ እንደስንዴ
ይወጋኛል ዕንባ ቀንዴ
"ህይወት በቃኝ" ስል ሰማችኝ
ሳቀችብኝ እያየችኝ::
(አልወድሽም)

እጠጋበት ባጣም
እተኛበት ባጣም
እሞትበት ባጣም
እስቅበት ባጣም
አለቅስበት ባጣም
እናቅበት ባጣም
እንደወደድ ባጣም
እደርስበት ባጣም
ከእቅፍሽ ባልወጣም
ወዴትም ባልሸሽም
ማርያም ምስክሬ ህይወት አልወድሽም::

አልወድሽም

አልወድሽም

አልወድሽም