Get Mystery Box with random crypto!

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ eliasshitahun — የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤
የቴሌግራም ቻናል አርማ eliasshitahun — የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤
የሰርጥ አድራሻ: @eliasshitahun
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.54K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥም በድምጽ በጽሑፍ
ምርጥ አንድ ገፅ
በሰው የተነበቡ ግጥሞች
የአሪፍ መጽሐፍ ጥቁምታ
አጫጭር ታሪኮች
የሀሳብ ንሸጣዎችን ከሁሉም እንቃርማለን፡፡ፈጠራዎችን እንደመምባቸዋለን፡፡የኤልያስንም የሌሎችንም ከያነያንን ስራ እንታደማለን፡፡ ስለሀሳብ እንሰማለን፡፡ እናሰላስላለን፡፡ ሰክረን ሳይሆን ሰክነን፡፡ሀሳብን እናስበዋለን፡፡
ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት 👉 @Elias2127

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-18 16:23:17
2.4K views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 13:45:42 “ምኒልክ የዓለሙ መፋረጃ"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~ ~
ጥቁር ሰማይ አንተ ከለላ ምንዱባን
ጥቁር መሬት አንተ ጥጋብ ለርሁባን
ጥቁር ገነት አንተ ለድሀ አድግ ፅድቁ
ጥቁር ጅራፍ አንተ ለሚመፃደቁ::

እንስፍስፍ ነው እጁ ለጠፋው ለሟቹ
ቅንነት ትዳሩ ደግነት አማቹ
ቅናትና ዕብሪት እንዴት ዓይኑን ይዩ
በየት ነው የወጣው ምኒልክ ፀሀዩ::

ምኒልክ “አብርሃም” ድንኳን ስር ከረመ
ልጅ አልወለደም ወይ በቃል የታተመ?
ምኒልክ “ይስሃቅ” ታረደ በልጁ
ነፃ ያረጋቸው ስለት አበጃጁ?

አባትስ ነበረን ታሪኩን ያቆማት
አፍ አያርፍም እንጂ አምላኩን ከማማት::
ንጉሥስ ነበረን
ነበረን
ነበረ::

ምኒልክ “ክርስቶስ” ተሰቀለ ሀሜት
አምላኩን ይገድላል ሰው ከሞላው ስሜት::
2.2K views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 20:58:04 ሴት ቃል ነው የሚላላት
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ውስጥህ ፍቅር በሚኖርበት ጊዜ
እንደታቦት በተሸከምከው ግዜ
ቃሉ ሁሉ ደስታ ቃል ሁሉ ትካዜ፡፡
(ይሆናል)

(ያኔ- አፍህ)
አሮጌ ቃላትን ለቃቅሞ
አስውቦ ቀምሞ
ይወርዳል ያንበለብላል
እንዴት ለአዲስ ፍቅር አሮጌ ቃል ይሸከማል?
(ግን ሞክር -ይጥማል)

አንዲት ሴት
ፍቅረኛዋን መሳብ
ምትወደውን ከንፈር መሳም
ከተመኘች ከሆሄ ጋር ባልጋ ትቅር
ወንድ ሳይሆን አሮጌ ቃላት ታፍቅር
ከሰዋስው ሕግ ጋር ትተኛ
ቋንቋ ነውና መተተኛ፡፡

አንተም ወዳጄ
ለምወዳት ሴት
"ምንም ነገር አልነገርኳትም"
"ምንም አላልኳትም"
አትበል
ሂድና
አሮጌ ተራ አሮጌ ሆሄ ግዛላት
አሮጌ ቃላት...

የሰነበቱ

የሸበቱ

የተንከራተቱ

ፍቅር ፍቅር የሸተቱ::

"ወድሻለሁ"ን ጣልና
"ካንቺ ፍቅር ይዞኛል" በልና
አሮጌ ቃላት
ንገራት
ዘመኗን አፍራርስና ባሮጌ ስሞቿ ጥራት፡፡

ፈላልገህ ጠብቃት
ሸምተህ ጠብቃት
ሴት ቃል ነው- የሚያጠብቃት::

ከነፀጋዬ የተራረፈ
ከገብረክረስቶስ የተሸረፈ
ደበበ በመንገድ ከረሳው
ሂድና እሱን ቃል አንሳው፡፡

ከዛም
አንበልብልላት
በልላት
ሴት ቃል ነው የሚያላላት፡፡
2.1K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 23:49:45 "ዝም በል"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ከሳሽህ ፊት ዘንበል
ሰዳቢህ ፊት ዘንበል
በነፍስህ ተናገር በቃልህ ዝም በል።

ዝም

እሺ በል አጎንብስ
ፊደል አታገግበስብስ
ዝም በል ጭጭ ጭጭ
ስንፍናን በልምጭ
ዝምታህን እቅጭ
አድርገህ ተቀበል
ዝም ብለህ አስጩህ እንደቅዱስ ፀበል::

አስብ ዝም ብለህ
እንደሊቅ ተራቀቅ
እንደንጉሥ ውደቅ::

ዝም ብለህ ሞክር
ዝም ብለህ ጨክን
ዝምበል ተንገዳገድ
ማስራዳት ሲያስብ ነው ሰው የሚወላገድ::

ዝም::

እግዜርን ተመልከት
ሊያስረዳህ ሲሞክር አታየውም ሲጥር
መች ብዙ አወራ ዓለምን ሲፈጥር።

(ዝም ብለህ ቀጥል
2.4K views20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 01:04:27 ስንብት ሆኗል- ላልተወሰነ ጊዜያት ከፅሁፍም ከማሀበራዊ ሚድያም ርቄያለሁ::

ሰላሙን ፍቅሩን በወጉ ማዘኑን ያድለን!!!

ያድርሰን ደግሞ
ለከርሞ!!!
ሰላም ያገናኘን!
ኑሩልኝ!!!
1.8K views22:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 23:29:44
1.8K views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 22:07:51 የራስሽ ውሽማ
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~

የልጆች ዋጋ ውድ ነው ርካሽ
ሰልስትም አትቆይም ወረት እየነካሽ?

ፈውስ የለም
ዘላለም
ምን ሀኪም አስታሞን?
ሞትሽ የዘላለም ለቅሶሽ የአንድ የሰሞን::

እኔማ
ዕንባና ለቅሶሽን ወረትሽ አርሞት
እጠብቅሻለሁ
እስከምንግናኝ ደሞ በሌላ ሞት::

(እኛ እኮ ክፉ ነን)
ይኸውልማ
ሰው እንዴት ይሆናል የራሱ ውሽማ?
የሞቱ ውሽማ?
የነገው ውሽማ?

አንቺ የሰው ሲኦል አንቺ የሰው ገነት
ስንት ገባ ህይወት ስንት ነው ዜግነት?
ስንት ነው ሰውነት?
ስንት ነው ማንነት?
1.8K views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 19:48:11
1.7K views16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 22:27:14 "ተሳስተን አልነበረም ሳስተን እንጂ"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~
"ቀን ከወጣልን
ስደት ከቀረልን
አሮጊቶች ከተጦሩልን
ችጋርና ችግር ከተወገደልን
ከገዛ ወንድማችን ጋር ከኖርን"
ብለን እንጂ ወዶ ገብ ሆነንም አልነበር::
መሪን መወድዳችን::

"ንጉሥ እና መስከረም አንድ ነው አመሉ
ተስፋ ተሽክመው ሁሉን ይጠራሉ::" እናም ልክ ነበርን::

"ድሮም ብያችሁ ነበር" ለማለት የሚያበቃ የእወቀት መገለጫም አይደለም::

ምክንያቱም አላዋቂ ሆነን አልነበረም
ሰልፍ የወጣን
ቦንብ የመታን::
በአንዲቷ ጎጇችን መጥተውብን እንጂ
ደድበንስ አልነበረም::

እንደዘር ያስቆጠረንን ስርዓት ስለወደቅልን
ደስታ አፍኖን እንጂ ቀሽመንስ አልነበረም::
እናቶች ወንድ ልጆቻችን ታፈሱብን ከማለት ዳኑልን ብለን እንጂ ተራ ሆነን አልነበርም::
ድንበር
መስመር
ዘር
ቀረልን በለን እንጂ ክፉና ደጉን የማንለይ ተላላ ሆንነ አልነበረም አንድ ሰው ንጉሣችን ያልነው::

እንጂማ
"ይብላን ለካደን ሰው
ይበላን ለዋሸን ሰው
ያመነማ ይኑር በሌላ እንዲክሰው::"

ይብላን ለካደን ሰው
1.8K views19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 14:38:53 ይታወቅልን....

"አንድም እናት በወሊድ ምክንያት አትሞትም" እያልን ስለተሳለቅንባት የኢትዮጵያ እናት ከነልጆቿ ስለመፈጅቷ ነው ዓይን ውስጥ መግባታችን::

"በቀን ሶስቴ መበላት" ስለሚባልው ቅንጦት አይደለም - ነገን በዋስትና ሰለማደር ነው ትግላችን::

"ምርጫ ስልጣን" ስለተባለው ወለፈንዲ አይደለም - እንደሰው ብቻ ኖሮ ሰለመሞት ነው ጩኸታችን::

"ብሔር እና እምነትን" ስለማቀንቀን ያይደል - ጠኔ በወረሰው የጦብያ መሬት ላይ አፈር ገፍቶ መኖር ነው መሻታችን::

"ፖለቲካዊ ተሳትፎ" ስለምትሉት ወንበረም አይደልም - ከተማም ገጠርም ሀገሬ ነው ብሎ መኖርን ስጡን ነው ያልነው::

"ስለ አዲሲቷ ኢትዮጵያ" ስለትባለውም አይደል-አሮጌ ያላችሁትን መከባበር ስል አሮጊቶቹ ብላችሁ መልሱልን ነው ዘመቻችን::

ስለእድገት
ስለትምህርት
ስለ
ስለ
ስለ
አይደለም - ስለእናቶች እንባ ስለህፃናት ዋይታ መቆም እንጂ::

ቀና ከሆናችሁ ትንሹን ነው ምንጠይቅ::
አንደግ
አንማር
አንምረጥ
አንሰለፍ

ብቻ "እንደሰው እንኑርበት"
2.0K views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ