Get Mystery Box with random crypto!

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ eliasshitahun — የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤
የቴሌግራም ቻናል አርማ eliasshitahun — የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤
የሰርጥ አድራሻ: @eliasshitahun
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.54K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥም በድምጽ በጽሑፍ
ምርጥ አንድ ገፅ
በሰው የተነበቡ ግጥሞች
የአሪፍ መጽሐፍ ጥቁምታ
አጫጭር ታሪኮች
የሀሳብ ንሸጣዎችን ከሁሉም እንቃርማለን፡፡ፈጠራዎችን እንደመምባቸዋለን፡፡የኤልያስንም የሌሎችንም ከያነያንን ስራ እንታደማለን፡፡ ስለሀሳብ እንሰማለን፡፡ እናሰላስላለን፡፡ ሰክረን ሳይሆን ሰክነን፡፡ሀሳብን እናስበዋለን፡፡
ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት 👉 @Elias2127

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-05-29 23:25:25
3.4K views20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 13:49:48 ተነጣጥሎ ያለው የቅዱሳን ጸጋ
ማርያም ጋ ረጋ።

ኤልያስ ሽታኹን

~ ~ ~ ~ ~
ነብያት ይላሉ
"ፈኑ እዴከ እም አርያም"
እጁ ብቻ ያይደል
ስው ሆኖ ተገኘ እግዜር ከማርያም።

እግዚአብሔር ከሰው አንድ ሰው ፈለገ
ልቡ እንደእዮብ ነፍሱ እንደዳዊት የተመነደገ

እንደአብርሃም ቀና እንደኖኅ አሳቢ
እንደሙሴ ያለ ያገር ልጅ ሰብሳቢ
በተግባሩ በስም
ንጉሥም ቅዱስም
ሁሉንም የሆነ።

እግዚአብሄር አየ
ለመንግሥቱ ለየ
ከሔዋን ዘር ሔዋን
ያልበላች ፍርዋን
እግዚአብሔር ለየ
በማርያም ታየ።

ተነጣጥሎ ያለው የቅዱሳን ጸጋ
ማርያም ጋር ረጋ።

እግዜር ሰው ከእንዲሆን
ዓለሙን እንዲምር
ማርያም
ተገኘች የቅዱሳን ድምር።
የምድር ኪሩቤል
የምድር ሱራፌል
ወልደአምላክ መንበር
በሁሉ የሞላ ተዘጋጀለት በር::

ወላዲተአምላክ
ጌታዬን አሰብኩት ለእናቱ ሲላክ።

ኦ ማርያም ትንቢተ ነብያት
ኦ ማርም ጾመ ሐዋርያት
ከዚህ ሁሉ ዓለም ልቡ ከታበየ
አንድ እርሷ ተገኘች ማርያም ርግብየ::
ርግብየ
ርግብየ
ርግብየ ልቧ በትህትና ክንፍ
ገርድ ልሁን ስትል አምላኳን ስታቅፍ

ይህን አንድ ሚስጢር ተጽፎ ቢያየውም
ተደርጎ ቢያየውም
ራሱን ይህ ምስጢር ዓለም አይችለውም።

እሙ ለፀሀዩ ትህትና ነፍሷ
ማነው የሸመነው የማርያም ቀሚሷ?

እንደምስኪን ጎንበስ
የሰው ዕንባ ማብስ
"ንግሥት ናት" ብሎ ሰው ልኳን ቢገምት
የጌታዬ እናት ግን እንደድሀ ኩርምት።

ተበታትኖ ያለው የቅዱሳን ጸጋ
ማርያም ጋር ረጋ።

እግዜር ሰው ከእንዲሆን
ዓለሙን እንዲምር
ማርያም ተገኘች የቅዱሳን ድምር።
3.5K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 19:17:20
3.0K views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 22:52:55 (Ego ክብር በሚል ተተክቶ ይነበብለኝ)

Ego ደበደበኝ
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
የገላጋይ ያለህ "ክብር" ደበደበኝ
ልብ አርጉልኝ ሰዎች መሬት እንደጣለኝ።

ከእጄ እንዳልበላ
እኔን በላ።
ከእጄ እንዳልጎረሰ
አቅሜን ወረሰ።

በሰው ፊት አነቀኝ
በክብር ስም መጥቶ ስንቱ ነው የናቀኝ።

የገላጋይ ያለህ "ክብር" ጣለኝ መንገድ
ይኸው አለሁ ዛሬም
በሰው አፍ ስገዛ በሰው አፍ ስነገድ።

እሰይ ደረስክልኝ
ያሳደኩህ "ክብር" እንድታስታውሰው
ቢያንስ አታርቀኝ
ወስደህ ጣለኝ እንጂ ከማይመዘነኝ ሰው።

ልብ አርጉልኝ ሰዎች
ካንዱ ተደብቆ አይገኝም ግርጌው
"ክብር' ደበደበኝ እኔው አሳድጌው።
3.6K views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ