Get Mystery Box with random crypto!

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ eliasshitahun — የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤
የቴሌግራም ቻናል አርማ eliasshitahun — የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች 💚💛❤
የሰርጥ አድራሻ: @eliasshitahun
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.54K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥም በድምጽ በጽሑፍ
ምርጥ አንድ ገፅ
በሰው የተነበቡ ግጥሞች
የአሪፍ መጽሐፍ ጥቁምታ
አጫጭር ታሪኮች
የሀሳብ ንሸጣዎችን ከሁሉም እንቃርማለን፡፡ፈጠራዎችን እንደመምባቸዋለን፡፡የኤልያስንም የሌሎችንም ከያነያንን ስራ እንታደማለን፡፡ ስለሀሳብ እንሰማለን፡፡ እናሰላስላለን፡፡ ሰክረን ሳይሆን ሰክነን፡፡ሀሳብን እናስበዋለን፡፡
ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡
ለማንኛውም አስተያየት 👉 @Elias2127

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-21 16:32:06 "ትንንሽ ምልክቶች ተገጣጥመው
አንድ አርማ ይሰራሉ::"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ሞኝ ትንታኔ ነውና::

"የመንግሥት የመጀመሪያ ስራ
የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ነው"

"የመንግሥት የመጀመሪያ ስራው የዘላለም መንግሥት መሆን ነው::" እላለሁ::

ከላይ እስከታች ስልጣንን ለበላይነት የመጠቀም አዚም ላለብን ለኛ የተለመደ ነው "መበድል"::

"ከእንጨት መርጦ ለታቦት
ከሰው መርጦ ለሹመት"
ብሂላችን ገና እውነትነቱ ያጠያይቀናል::

"Why nations fail" የሚል መጽሐፍ አይቼ ለኛ ነበር:: ግን ለኛ አይነቱ Why generation fail የሚለው ጥያቄ ይቀርበናልና::

ሞት political philosophy ውስጥ ያለትካተተ common course ነው::

ስነ-መንግሥት እና ቃታ "ስጋማቾች" ናቸው::
በአህጉረ አፍሪቃ ደሞ ስር የሰደደ ተሰጥኦ ነው:: "ሞት"::

የተድጋግሙት እነዚህ ሁሉ ሞቶች
ምልክት ናቸው ብለህ አትጃጃል::
የፖለቲካ "አርማው" ነው::
እነዚህን ትንንሽ ምልክትን "እንደአርማ" እንቀበላቸው::

"የሰው ሞት" ታስቦበት ተቀምሮ የሚሰራ የፖለቲካ simple game ነው::

ዑመርኻያም "ባለድል መች ይታመናል?"
ይለናል:: አሽናፊዎች ድል እንጂ ዕድልን መጠቀም አያውቁበትም::

አብያተ ክርስትያናቱም በታንክኞች ፍቃድ ይመሰርታሉ:: ሸሆች ሶላት ላይ ነገሥታትን ማስጎንበስ ያፍራሉ::

ሁሉ ነገር በማናውቃቸው ሰዎች
በማይታወቁ መንገዶች ቁጥጥር ስር ናቸው:: የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊም ነገውን እንጃለት::

"ብሎ ሞተ" ለመባል ነው እንጂ ስፋቱና ጥልቀቱ ሀልቅወመሳፍርት ለሆነው ለማይስትካከለው የሀገሬ ፖለቲካ እኔም መሰሎቼም ከነጽሑፍችን ኢምንቶች ነን::

ግና መኖር ጥያቄ ነውና እስንሞት እንጠይቃለን::

ሞትና ስልጣን ምንና ምን ናቸው?
2.2K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 22:09:15 ግምኛ ግምኛ
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
የሐበሻ ዓይኖች ምንኛ ውብ ናቸው
ሲያለቅሱ ሲያነቡ ንጉሡ ቢያያቸው
በሌላ ሀዘን ነው የሚያባብላቸው::

የሐበሻ ጥርሱን ማነው የነቀሰው?
ሲሳለቅ ይውላል አንዱ ሰው ባንዱ ሰው::

እግዜርም ወረደ በሰው ቁመት መጠን
አላህም ወረደ በሰው ቁመት መጠን
እኛ ጠፉን እንጂ
ከገዛ ስማችን እያበላለጠን::

የሐበሻን ብሂል ማነው የቀለሰው?
ንጉሥ ላለመክሰስ ሰማዩን አረሰው::

የሐበሻ ዓይኖች ውብ ናቸው ምንኛ
ድንኳን ይስቃሉ ግምኛ ግምኛ::
2.1K views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 18:36:02
2.4K views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 17:36:07
2.2K views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 23:34:36 እሺ በይኝና
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ናፍቀሽኛል ብልሽ መች እናፍቃለሁ
ወድሻለሁ ብለሽ መች ወድሻለሁ?
:
ሌላ ነው መውደዴ ከመውደድ ባሻገር
መዳፍሽን ብስም አያሻኝም ሀገር::
:
በአንድ ቃል ባንድ ስም እንደፈታ አፉን
ሳልጠራሽ አልገልጠው የናፍቆት መጽሐፉን
ሳልጠራሽ አልከፍተው የነገ በራፉን::
:
እሺ በይኝና
አንዴ ስሜን ጥሪ
ሁሉ ጀነት ይግባ ይጥፋ ጦም አዳሪ፡፡

እሺ በይኝና
በመንገድ ስታልፊ ጣትሽ ሽባን ይንካ
በዓለም የተተወ ባንቺ ጣት ይመካ፡፡

እሺ በይኝና
ቃላሽን አፍልቂ
እሺ በይኝና
አንድ ግዜ ሳቂ
እሺ በይኝና
(ኤላዬን ደብቂ)
እሺ በይኝና
ታሪኬን ልጻፈው
እሺ በይኝና
መኖርን ልቀፈው::
2.4K views20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 21:59:10
2.8K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 21:10:54 ናፍቆት "አያ ጅቦ"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~

የናፈቁትን እየዳሩ
የወደዱትን እየሞሸሩ
(የምን እሹሩሩ)

አንዴ ከሆነ ወዲያ ቢባል ሆዴ ባባ
ምን ሊረባ?

ያፈቀሩትን እንዲሳም ሌላን ሲታቀፍ
ላያድኑት አበባን ከማርገፍ....

እንዲያው መቀበጣጠሩ
ላይስተከል ነገሩ
(እሱ ነው መለየት ሸሩ)

እኔማ
እንሆንው ያልኩትን ከሌላ ከሆነሽው
"አፈቅርሻለሁን" የትም ካደረግሽው?

ሁሉ በነበር ሲቀር ቅጽበትም ሲያስፈራ
ህይወት እንደዚህ ናት ያልዘራሽውን ምታፈራ፡፡

አልዘራሁም አንቺን ማጣት
(አጨዳለሁኝ ቅጣት)
አልዘራሁም
አልዘራሁ መለየት
(አጨድኩኝ መሸኘት)
አልዘራሁ መራራቅ
ነገዬ ታየኝ እንደጭራቅ፡፡

እንደልጀነቴ እንደአያጅቦ
ማጣት ሲመጣ በሰው አፍ ታጅቦ፡፡

"ይበልሃል" ሲሉኝ ጥቅልል ሽፍን ብዬ
እንዲያ ነው ምፈራ መለየት አንቺዬ፡፡

እኔማ
ያንን "አያ ጅቦ" ባልፍም ተድበስብሶ
መለየት ግን በላኝ ያውም "ከጅብ" ብሶ፡፡
2.8K views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 20:40:56 እስክትመጣ እንጂ....
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~

የአፍ መፍቻ ቋንቋን
ተክቼበት ሳቋን
ግሱን ተውላጠ ስም
እረሳለሁ ጉንጯን ስስም

የተድፋብኝን ሰማይ
የራቀችኝን ፀሀይ
ድል እነሳታለሁ
ባንድ ቃል አሽንፋለሁ
"ትወደኛለች" እላለሁ::

ስትመጣ
ትናንቴን ጠራርጌ
ወደ ሠርጌ::

የለኝ አዲስ ቋንቋም
እቆማለሁ እንጂ የናፍቆት አቋቋም::
አዲስ ዘመን አበራልኝ
አዲስ ቤቴን አጠረልኝ
(ከየት አገኘልኝ?)

በዓይኖቿ ውበት አቆማለሁ ጊዜ
ስትስመኝ ካወራሁ እሱ ኑዛዜ::

ወይን አያርካው የናፋቂን ጥምስ
እስክትመጣ እንጂ ምን ያርጋል ግጥምስ?
2.8K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 21:43:12 "አፋቸው ላይ ስምሽ ሲያምር::"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ምን ሆኜ ወደድኳት
ያውም ያልለመድኳት

ቀልቡ እንደራቀው
ስል እምራቀቀው
(እግዜሩ ይወቀው)

በታህሳስ ሰማይ አንቺን የማስሰው
ከዚህ ሁሉ ፍጡር ከሚርመሰመሰው
ምንሽን ብቀሰው?
ምንሽን ብለበሰው?
(እግዜር ይመልሰው)

እርሜን በወደድኹሽ
እርሜን ብናፍቅሽ
አንቺም ተራምደሽኝ ገስግስሻልና
አርሞኒካ ጥዬ ለመድኩኝ በገና፡፡

ቢጤዎቼ መጥተው
"ጨከን ነው" ሲሉኝ
እኔም ይኸው ጨክን
"ቆምጠጥ ነው" ሲሉኝ
እኔም ይኸው ቆምጠጥ

ሲሉኝ እየመጡ
"ምንድነው መንሰቀሰቅ?
ምንድነው መራቀቅ?
ፍቅር ገለመሌ
ያውም ለእገሌ
አቦ ተዋት" ሲሉኝ
"እርሳት አቦ " ሲሉኝ "ተውና መንፈቅፈቅ"
ሲጠሩ ሲያነሱሽ ባሰብኝ መናፈቅ::

የከበበኝ አጀብ
እንድተውሽ ብሎ ክፉ ቃል ሲያሰምር
እኔ ግን እላለሁ
አፋቸው ላይ ስምሽ ሲያምር::

ጥፉቱ የማን ነው?
2.9K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 22:47:50 ኤልያስ ሽታኹን
እውነታቸውን ነው?
~ ~ ~ ~ ~
የመታሽ ክንፍሽን
የቀማሽ ሳቅሽን
ማንነው?

እኔን
እኔን የኔ ርግብ
አልችልም ሆኖ ነው ከዓለም ግብግብ
አልችልም ሆኖ እንጂ ባሁኑ ቦታዬ
እኔማ እንድድሮ ባቅፍሽ ነው ደስታዬ
(ብስምሽ ደስታዬ)

ልጠይቅሽማ
ተለያየን ማለት ያስብላል ምን ግዴ?
ሰው ትዝታ ሲሆን አቧራ ነው እንዴ?

ተለያየን ማለት ፍቅራችን በነነ
ተለያየን ማለት ፍቅራችን ተነነ
:
ማለት ይሆን እንዴ?

እኔማ
ተለይቼሽ እንኳ መውደቅሽ ያመኛል
ማዘንሽ ያመኛል
ማኩርፍሽ ያመኛል

ሰው ግን ይመጣና
"አልወጣልችልህም" ማለት ነው ይለኛል፡፡

እውነታችውን ነው?
2.7K views19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ