2022-08-24 22:35:46
ኑዛዜ አዘል ነዛዜ.....
(የሚነበብ ብቻ)
ምን አልባት የመጨረሻው መጨርሻ ቢሆንስ?
አውቃለሁ "አለቀ"ን አንወድም::
ግን ማለቂያው ላይ ብንሆንስ?
ይሄ የመጨረሻው ቃል ሊሆን ይችላል:::
ምን አልባት ጉሮሮ ከመናገር ቢከለከል
እጅም ከመፃፍ?
ምን አልባት ለመፍራትም ለመድፈርም እስትንፋስ ካጣን....
ምን አልባት የምንወዳቸውን ለማቀፍ ....
የምንጠላቸውንም ለመንቀፍ
ይሄ ቅጽበት የመጨረሻው ቢሆንስ?
የሚውዱን ሳይነግሩን የሚነቅፉን ሀቃቸውን ሳንስማላቸው ልናመልጣቸው ቢሆንስ?
ምን አልባት
- የተስፋዬ ገሠሠን "ዑመርኻያም" ገፅ 167 ላይ እንዳጠፍኩት
- ያቺን የመሰለች ልጅ እንዳልኩ
- ለራሴ ኪሴ 10ብር ሳይኖረኝ ተማርሬ ሳለ "ናፈቅኽኛል" ስትለኝ"ከዚህ ቡኃላ እንዳትድወይልኝ" እንዳልኳት
- አመታት የራቅኩትን ኪዳን ሰዓታት ነገ እሄዳለሁ እንዳልኩ
- ድሮ ክበብ የተጣላዋቸውን መች አጊንቻቸው እንዳልኩ
- እማዬን ግሸን አቁርቤያት እንዳልኩ
- በየፊናው የወረወርኩት ካልሲ ፓንት ፀሀይ ሲወጣ አጥበዋለሁ እንዳልኩ
- መዝሙር የሞላሁት ስልኬን non-stop ሙዚቃ ከፍቼበት እንዳለሁ
- ያን ሹራብ የሆነ ቀንማ ገዝቼ እለብሰዋለሁ እንዳልኩ
- ቤቴ ያለውን ቆሻሻ እጠለዋለሁ እንዳልኩ
- ያለቁብኝ የማልፈልጋቸውን በፌስታል ያሉትን ሰልባጅ ልብሶቼን ለደሀ እሰጠዋለሁ እንዳልኩ
- ያቺ ምስኪን በኦርቶዶክስና በጴንጤ መሐል ነፍሷ የምተሰቃይባት ፕንኤል "ማሀትብ ገዝተህ ስጠኝ" እንዳለችኝ
- ድምጿን ለመስማት ስል "ይቅር ብዬሻለሁ" ብዬ የውሸቴን እንደታረቅኳት
- የሚፈልጉኝን ሁሉ “busy” ነው ብለው እንዲያስብኝ እንዳደረኩኝ
- ግንቦት መጨረሻ በዘነበው ዝናብ ወደጥቁርነት የተቀየረው ስሙን የማላውቀው “ብራንድ” ጫማዬ አጠበዋለሁ እንዳልኩ
- "ትንሽ ሳንቲም ከያዝን እንጋባለን?" ስባል ዝም እንዳልኩኝ
- የድሮ ፍቅረኛዬን ፎቶ "በፍቅር ስም" መጽሐፍ ውስጥ እንደከተትኩት
- የታሰረ ጎደኛዬን ሰላሙን ባሰማኝ እንዳልኩ
-"ኢትዮጵያን እንደርገጥኩ አንተን ነው ማየት የምፈልገው" እንደተባልኩ
-"ምን ላርግልህ አስበህበት ንገረኝ" እንደተባልኩ
-“ ካንተ አንድ ልጅ ብቻ እኮ ነው ምፈልገው"
"ከዛስ?"
"ከዛ ከፈልክ መጠተህ ታያታለህ"
"ሳታርግዢ ስሟን ጾታዋን ጨርሰሽኛላ"
"አትቀልድ"
"የምርሽን ነው?"
"አዎን ጀርመን ሳልሄድ በፊት እርግጠኛ እንድሆን ሰሞኑን ብናደርገው ምን ይመስልሀል?"እንደተባልኩ
-“ቤተልሔም መጽሐፌን አነበብከው” እንደተባልኩ
- ወገቤን የሚያመኝን ነገር "ፍልውኃ ግብቼ በውኃ ተመትቼ" እንዳልኩ
ይሄ ሰዓት
ይሄ ቅፅበት
ይሄ
ይሄ
ይሄ
የመጨረሻው መጨርሻው ቢሆንስ?
ያስፈራል?...
1.5K views19:35