Get Mystery Box with random crypto!

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የሰርጥ አድራሻ: @ebcnewsnow
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 123.82K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-11-01 07:17:59

16.4K views04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-31 16:17:07
ሳኡዲ አረቢያ የ2034ቱን የዓለም ዋንጫ የማዘጋጀት እድል እንዳላት ተገለፀ
*******

ሳኡዲ አረቢያ ከአስራ አንድ ዓመታት በኋላ የሚካሄደውን የ2034ቱን የዓለም ዋንጫ የማዘጋጀት እድል ልታገኝ እንደምትችል ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ፊፋ የ2034ቱን የዓለም ዋንጫ ለማስተናገድ ከኤሲያ እና ከኦሺኒያ ሀገራት እድሉን እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ውድድሩን ለማስተናገድ ፍላጎት አሳይተው ከነበሩ ሀገራት መካከል ከኦሽኒያ አውስትራሊያ፤ ከኤስያ ደግሞ ሳኡዲ አረቢያ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
https://www.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid0rLScGzUiMaHLaWPBacBQm5k8KBVyeS1qjT3Js5ARBkCciqsX4KQNnU3oHkY9Moqbl
17.4K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-31 12:42:48
የጋዛ ጦርነት በዚህ ከቀጠለ የነዳጅ ዋጋ በበርሚል 150 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል የአለም ባንክ አስጠነቀቀ
**************

በእስራኤል ጦር እና በሃማስ ታጣቂ ቡድን መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት ተባብሶ ከቀጠለ የነዳጅ ዋጋ በበርሚል 150 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል የአለም ባንክ አስጠንቅቋል፡፡

አሁን ላይ የነዳጅ ዋጋ በበርሚል 90 ዶላር አካባቢ መሆኑ እና በቅርቡም ከዚህም በላይ ሊቀንስ ይችላል ተብሎ የተተነበየ ቢሆንም፤ የአለም ባንክ ይህ ሁኔታ በፍጥነት ሊገለበጥ እንደሚችል ነው ያስጠነቀቀው።

እንደ ዓለም ባንክ ማብራሪያ ከሆነ ጦርነቱ በዚህ ከቀጠለ እና ነገሮች ወደ ከፋ ሁኔታ የሚለወጡ ከሆነ በ1970ዎቹ ከነበረው የነዳጅ ቀውስ ጋር የሚመሳሰል ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል አስታውቋል፡፡

በ1970ዎቹ ተፈጥሮ የነበረው የነዳጅ ቀውስ የነዳጅ ዋጋን በበርሚል ከ140 እስከ 157 ዶላር አድርሶት እንደነበር ይገለፃል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid095yZjurriv2QvD2ae5UQmvYW6kCr7RBDmy2zsD3sTDDFDtuvqXj8iqixARyzwyqjl
17.7K views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-31 00:48:41
ሊዮኔል ሜሲ የዘንድሮ የባሎን ደ’ኦር አሸነፊ ሆነ
****

በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ የተካሄደውን የ2023 የባሎን ደ’ኦር ሽልማት አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ለ8ኛ ጊዜ አሸንፏል።

የዚህ ዓመቱ የሽልማቱ አሸናፊ ሜሲ ባለፈው ዓመት ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የዓለም ወንጫን ያነሳ ሲሆን፣ አሁን በሚገኝበት የአሜሪካው ኢንተር ማያሚ ጋርም ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል፡፡

የ2023 የሴቶች ባሎን ደ’ኦር ሽልማት አሸናፊ ስፔናዊቷ አይታና ቦንማቲ ሆናለች፡፡ የ25 ዓመቷ ቦንማቲ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የሴቶች ዓለም ዋንጫን አሸንፋለች፡፡

በዚህ የባሎን ደ’ኦር ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ሌሎች ሽልማቶችም ተሰጥተዋል፡፡ በዚህም መሠረት፡

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=724815906339258&id=100064325666044&mibextid=Nif5oz
13.4K viewsedited  21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-30 20:03:07
በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማስተካከያ ተደረገ
**********
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ የሚዲ-ባሶች እና የሚኒ-ባስ ታክሲዎችን የአገልግሎት ታሪፍ ማስተካከያ አደረገ፡፡
አዲሱ የታሪፍ ማስተካከያው ከነገ ጥቅምት 20 ቀን 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው ቢሮው የገለጸው፡፡
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ቢሮው አዲስ ባሻሻለው ህጋዊ የታሪፍ ተመን ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ቢሮው በጥብቅ ያሳሰበ ሲሆን ይህንን በሚተላለፉት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
ይህ የታሪፍ ማስተካከያ የከተማ አውቶብስንና የቀላል ባቡርን የማይጨምር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ህብረተሰቡም ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ሲያጋጥሙት፤ በአቅራብያው ለሚገኝ የህዝብ ትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥር ባለሙያዎች እና ለትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም በአቅራቢያዎ ባለ የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በአካልና በነፃ የስልክ መስመር 9417 ጥቆማ መስጠት የሚችል መሆኑን ቢሮው አሳውቋል።
13.7K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-30 17:36:06

12.8K views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-30 15:45:39
ፊፋ የቀድሞውን የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ለ3 ዓመታት አገደ
*******

የቀድሞው የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሉዊስ ሩቢያሌስ የፊፋን ዲሲፕሊን ህግ አንቀፅ 13ን በመተላለፋቸው ለ3 ዓመታት ከማንኛውም እግር ኳሳዊ ተግባራት በፊፋ ታግደዋል፡፡

የስፔን የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫን ማሸነፉን ተከትሎ በደስታ ስሜት የአጥቂዋን ጄኒ ሄርሞሶን ከንፈር መሳማቸው ይታወሳል፡፡

ሉዊስ ሩቢያሌስ ከተጫዋቿ ጋር የተሳሳሙት በጋራ ፍላጎት መሆኑን የተናገሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንቱ ራሳቸውን ከስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን አሳውቀው ነበር፡፡
https://www.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid02FVj5La5XTqkGfkZ2DQJvnLAYes1cwfN6KK6T1nCejULXccWhhL5eMVRaaraU36GGl
12.9K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-30 15:25:21
ከ 51 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የሞባይል ቀፎዎች እና የመኪና መለዋወጫዎች ተያዙ
**********

በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት አልበረከቴ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ከ51 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው 2 ሺህ 233 የሞባይል ቀፎ እና የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የሞባይል ቀፎዎቹ በተለያዩ የመኪና ክፍሎች በተሰራ ሻግ ተደብቀው ሊያልፉ የነበረ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸሙ ሶስት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ጥቅም ላይ በዋሉ በቁርጥራጭ ብረቶች ውስጥ ተድብቀው ሊያልፉ የነበሩ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋርም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል፡፡
13.4K views12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 11:19:57
ይገምቱ ይሸለሙ!
*

በስታድየሞቻቸው መካከል ያለው ርቀት የ6.42 ኪሎ ሜትር ርቀት ብቻ ነው። ሁለቱም ክለቦች በየፊናቸው ስኬት የሚሉትን አስመዝገበዋል፡፡ በአንዳቸው ውድቀት ሌላው ይደሰታል፤ እርስ በእርሳቸው ሲጋጠሙ መሸነፍን አምረርው ይጠላሉ፡፡

በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የሁለቱም ደጋፊዎች ስለሚገኙ በዚህ ምክንያት መቃረን ይመጣል፤ አባት እና ልጅ፣ እናት እና ልጅ፣ ባል እና ሚስት እንዲሁም ወንድም እና እህት ለ90 ደቂቃ ያክል ተከፋፍለው ይነቋቆራሉ፤ ምክንያቱም ይህ የማንቸስተር ደርቢ ነው፡፡

ማንቸስተር ሲቲ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ባደረጋቸው ያለፉት 5 ጨዋታዎች 4 ያሸነፈ ሲሆን ዩናይትድ በበኩሉ 1 ብቻ አሸንፏል። በነዚህ 5 ጨዋታዎች 19 ግቦች የተቆጠሩ ሲሆን፣ 13 ማንችስተር ሲቲ ሲያስቆጥር ዩናይትድ 6 አስቆጥሯል።

በማንቸስተር ዩናይትድ ያለው የጉዳት ዜና የካስሜሮ፣ ዋን ቢሳካ፣ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ፣ ሉክ ሾው፣ ማላሲያ እና ማይኖ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ ናቸው። በማንችስተር ሲቲ በኩል ደግሞ ኬቨን ዴብሩይን እና ዛክ ስቴፈን በጉዳት አካንጂ በቅጣት ከጨዋታው ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ውድ ቤተሰቦቻችን! ለመሆኑ ይህን ጨዋታ ማን ያሸንፋል ብለው ያምናሉ? ግምቶን በቴሌግራም ገጻችን በማኖር ይሸለሙ፡፡ ትክክለኛ ግምታቸውን ለሰጡ ሶስት ተከታተዮቻችን የምንሸልም ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- የተስተካከለ ውጤት ተቀባይነት የለውም፡፡ አንድ ሰው የሚሸለመው በአንድ ግምት ብቻ ነው፡፡ በቴሌግራም ገጻችን የተሰጠ ግምት ብቻ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
17.3K views08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 10:36:23 https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=3668
ሩሲያ እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈፀመች ያለው የቦምብ ድብደባ ዓለም አቀፍ ሕግን የሚፃረር ነው አለች
15.2K views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ