Get Mystery Box with random crypto!

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የሰርጥ አድራሻ: @ebcnewsnow
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 124.00K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-10-29 09:48:07

14.5K views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 06:22:46
‘ፍሬንድስ’ የተሰኘው ‘ሲትኮም’ ተዋናይ ማቲው ፔሪ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
**********************

‘ፍሬንድስ’ የተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ‘ሲትኮም’ ተዋናይ ማቲው ፔሪ በ54 ዓመቱ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ፖሊስ አስታወቀ።

ተዋናዩ ሎስ አንጀለስ በሚገኝ ቤቱ ውስጥ ቅዳሜ ዕለት ሞቶ መገኘቱ የተገለጸ ሲሆን ምናልባት በድንገት ባጋጠመው የመስጠም አደጋ ሕይወቱ ሳያልፍ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

ፎክስ ኒውስ ቲኤምዜድን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ የድንገተኛ አደጋ ሠራተኞች መጀመሪያ ከቤቱ የደረሳቸው ሪፖርት አንድ ሰው በልብ ድካም መያዙን የሚያመላክት ነበር።

እንደ ቲኤምዜድ መረጃ ከሆነ፣ በቦታው ላይ ምንም ዓይነት መድኃኒት (እፅ) አልተገኘም፤ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሟል የሚል ጥርጣሬም የለም።

‘ፍሬንድስ’ የተሰኘው የአሜሪካ የቴሌቪዥን ‘ሲትኮም’ በዴቪድ ክሬን እና ማርታ ካውፍማን የተዘጋጀ ሲሆን መጀመሪያ አየር ላይ የዋለው እ.አ.አ ከመስከረም 22 ቀን 1994 እስከ ግንቦት 6 ቀን 2004 ነበር።

ለ10 ሲዝን የዘለቀው አስቂኝ ድራማው ዋና ተዋናዮች ዛሬ በድንገት ሕይወቱ ያለውፈው ማቲው ፔሪን ጨምሮ ጄኒፈር አኒሽተን፣ ኮርትኒ ኮክስ፣ ሊሳ ኩድሮው፣ ማት ለብላንክ እና ዴቪድ ሽዊመር ነበሩ።
15.3K views03:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-28 20:06:15
ተጠባቂው የሪያል ማድሪድ እና ባርሰሎና ጨዋታ በሪያል ማድሪድ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቀቀ
*************

ተጠባቂው የሪያል ማድሪድ እና ባርሰሎና ጨዋታ ጁድ ቤሊንግሀም ከእረፍት መልስ ባስቆጠራቸው 2 ግቦች በሪያል ማድሪድ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡

ባለሜዳውን የባርሰሎና ቡድን ከሽንፈት ያልታደገውን ግብ ኤልካይ ጉንዶጋን ከእረፍት በፊት ማስቆጠር ችሏል፡፡
ከውጤቱ በኋላ በደረጃ ሰንጠረዡ ሪያል ማድሪድ በ28 ነጥብ ሊጉን የሚመራ ሲሆን ባርሴሎና በአንፃሩ በ24 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል::

በሌላ በኩል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች አርሰናል ሼፊልድ ዩናይትድን 5 ለ 0 መርታት ሲችል፤ ቼልሲ በሜዳው በብሬንትፎርድ የ 2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
15.7K viewsedited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-28 13:44:42
አርሰናል ከሼፊልድ ዩናይትድ ዛሬ 11:00 በኢቢሲ መዝናኛ ቻናል በቀጥታ
************************

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከሼፊልድ ዩናይትድ ዛሬ 11:00 የሚያደርጉትን ጨዋታ በኢቢሲ መዝናኛ ቻናል በቀጥታ ይከታተሉ።

ሁለቱ ቡድኖች ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት ከ 10፡30 ጀምሮ እና ከጨዋታው በኋላ ሰፊ ትንታኔዎች ይቀርባሉ።
16.0K viewsEndalk, 10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-28 12:51:22
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዋርሰሶ ወረዳ የቤንቶኒቴ ማእድን ማውጫ እና ማምረቻን ጎበኙ
*****************************

በአፋር ክልል የልማት ስራዎች ምልከታቸውን በመቀጠል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዋርሰሶ ወረዳ የቤንቶኒቴ ማእድን ማውጫ እና ማምረቻን መጎብኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቤንቶኒቴ ለሴራሚክ እና ቀለም ብሎም ለመሰል ምርቶች ጠቀሜታ በመዋሉ "ትንግርታዊ ርጥብ አፈር" እና "ብዝሃ ጥቅም ያለው ሸክላ አፈር" በመባል በአድናቆት የሚነሳ ሃብት ነው።
16.0K viewsNesru Jemal, 09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-27 16:15:54
ቻይና አዲስ የሮቦት ዜና አንባቢን ስራ ማስጀመሯን ይፋ አደረገች
**********


ቻይና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ሰራሁት ያለችውን 24 ሰዓት ዜና ማንበብ የምትችል አዲስ የሮቦት ዜና አንባቢን ስራ ማስጀመሯን ይፋ አድርጋለች።

በሺዎች የሚቆጠሩ የዜና አንባቢዎችን ያህል ብቃት እንዳላት የተነገረላት ይህቺው ሮቦት የመንግስት ሚዲያ በሆነው ፒፕልስ ዴይሊ ነው የተዋወቀችው።

ሬን ዢያኦሮንግን የተባለችው ሮቦት የ24 ሰአት የዜና አንባቢ እደምትሆን ታምኖባታል። ይህም የመጨረሻው የዘመኑ የቴክኖሎጂ ግኝት ሆናለች ነው የተባለው።

ዜና ከማንበብ ባለፈ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ማለትም ትምህርትን፣ ወረርሽኝ መከላከል፣ ስለ መኖሪያ ቤት እጥረት፣ ስራን፣ የአካባቢ ጥበቃ ጨምሮ ማወያየት እና መልሶችን መስጠት ትችላለች ተብሏል።

በመጀመሪያው ትውውቋ 24 ስዓት 365 ቀናት ያለምንም እረፍት ዜና አቀርብላችኋለሁ በማለት እያንዳንዱ አስተያየት ጥሩ እንድሆን ያደርገኛል ስትል ተደምጣለች ሲል ኒውስ ዶት ኮም ዘግቧል።
13.7K viewsedited  13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-27 12:28:50
በአለም አቀፍ ደረጃ በሞባይል ስልኮች ላይ የሚደርስ የሳይበር ጥቃት በእጅጉ ጨምሯል፡- ጥናት
**********

ታዋቂው የካስፐርስካይ ኩባንያ ባደረገው ጥናት እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2023 በሞባይል ስልኮች ላይ የሚደርሱ የሳይበር ጥቃቶች በአለማቀፍ ደረጃ እያደገ መምጣቱን ገልጿል፡፡

በጥናቱ መሰረት በ2023 በሞባይል ስልኮች ላይ የደረሱ የሳይበር ጥቃቶች ከ2022 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 5 በመቶ ጨምሯል፡፡

የካስፐርስካይ ኩባንያ ባወጣው ጥናት መሰረት ጥቃቱ የደረሰው በአብዛኛው በመካከለኛው ምስራቅ፣ ቱርክ እና አፍሪካ ውስጥ በካስፐርስካይ የተገኙ እና የታገዱ የአንድሮይድ የሞባይል ስልኮች ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid06Xmx6iVBjCZgEKenAip6vzJdqopMGEkq4cYBsnhBA7aGGoydQ4LKpDXbZuoLcgzwl
13.6K views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-26 16:45:17 https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=3618
ጄኔራል ሰዓረ መኮንን (አባ እሳቱ)
14.8K views13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-26 15:44:19
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከ1900 ጀምሮ
*************

• የኢትዮጵያ ሠራዊት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ደረጃ የተቋቋመው ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም ነው።

• ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር ሔሊኮፕተር የገባው ነሐሴ 12 ቀን 1921 ዓ.ም ነው። ከጅቡቲ ተነሥታ አዲስ አበባ (ገፈርሳ) ያረፈችው ሔሊኮፕተሯ “ንሥረ-ተፈሪ” ትባል ነበር።

• በኢትዮጵያ ለመጀመሪያው ጊዜ ዘመናዊ የጦር ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት የተቋቋመው በ1927 ዓ.ም ነው። ተቋሙ “የሆለታ የጦር ትምህርት ቤት ይባላል።

• ኢትዮጵያ የራሷን የማዕረግ ምልክት ንድፍ ደንብ ያወጣችው ታኅሣሥ 15 ቀን 1944 ዓ.ም ነው።

• ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የባሕር ኃይል ጠረፍ ጠባቂ ጀልባ የገባው በ1950 ዓ.ም ነው። ጀልባዋ ፒ.ሲ 11 የሚል ስያሜ ነበራት።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02spPP2d5Ug6iPVcQrDJPTutK6kRdxuMoBzzajKXdr53yLSopx9RVmy2Yqpii5WLNzl
14.6K views12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-26 14:04:20 https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=3611
116 ዓመታትን ስላስቆጠረው የመከላከያ ሠራዊታችን በጥቂቱ
12.6K views11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ