Get Mystery Box with random crypto!

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የሰርጥ አድራሻ: @ebcnewsnow
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 123.82K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-10-11 15:17:59
በአፍጋኒስታን ለ2ተኛ ጊዜ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ 1 ሺህ ዜጎች ለሞት ተዳርገዋል
******************************

በቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በአፍጋኒስታን የደረሰው ከባድ የተባለው የመሬት መንቀጥቀጥ 1 ሺህ ዜጎችን ለሞት መዳረጉ ተገለጸ፡፡

በሬክተር ስኬል 6.3 ሆኖ የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በሄራት ግዛት የተከሰተ ሲሆን ባለፈው ቅዳሜ ተመሳሳይ አደጋ አጋጥሞ የ2 ሺህ 4 መቶ ዜጎች ሕይወት መቅጠፉ ይታወሳል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ ቅዳሜ በደረሰው ተመሳሳይ አደጋ ያልተነኩትን በቻሃክ መንደር የነበሩ 7 መቶ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ አጥፍቷቸዋል ሲል ኤፒ ዘግቧል፡፡

ለአስርት አመታት በጦርነት የቆየችውና የውጪ እርዳታ ያሽቆለቆለባት አፍጋኒስታን ምቹ መሰረተ ልማት አለመኖሩ የእርዳታ ጥረቱን አስተጓጉሎታ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
14.9K views12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-11 10:09:27
ደቡብ አፍሪካዊው ቲክ ቶከር በማንነት ስርቆት ክስ ተመሰረተበት
*****************************

የማንነት ስርቆት በመፈጸም በሀሰት "ዶክተር” ነኝ ብሎ በቲክ ቶክ ከሕክምና ጋር የተገናኙ መረጃዎችን ለተከታዮቹ ሲያካፍል በነበረ ግለሰብ ላይ ክስ መመስረቱ ተገለጸ።

ራሱን "ዶክተር ማቲው ላኒ” ብሎ ከተከታዮቹ ጋር የተዋወቀው ይህ ግለሰብ ከዊትስ ሕክምና ትምህርት ቤት የተመረቀ መሆኑንም ሲገልጽ ነበር ተብሏል።

ይሁን እንጂ ተማርኩበት ያለው ተቋም የቲክ ቶከሩን "ዶክተር” እንደማያውቀው እና ስሙ በተማሪዎች ዝርዝር ውስጥም አለመኖሩን ይፋ አድርጓል ነው የተባለው።

https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02GkSzyS6ovop3XDuoaGFMWz1gVTFDP2Rx3YHjRatW97NMMHoFtUfKQ73wFv4Qr5sjl
15.9K views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-11 08:49:21

15.1K views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 00:00:27
በውጤት ላይ ቅሬታ ያላቸው የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታቸውን eaes.et ድረ-ገፅ ላይ እስከ ጥቅምት 5 ከቀኑ 11:30 ድረስ ማመልከት ይችላሉ
******************

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ከነገ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚከተሉትን ሶስት አማራጭ አድራሻዎች ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፥

• በዌብሳይት፡- eaes.et
• በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
• በቴሌግራም- @eaesbot

ከላይ ከተገለፁት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌሎች የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን የጠቆመው አገልግሎቱ፤ ተፈታኞች በማመሳሰል ውጤት እንገልፃለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ መክሯል።

ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ምንም ዓይነት ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑንም አክሏል።

https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0kNLrYvB11HdkozBUEph67MtzuaJjb9zFnusLXir9ik9MGcjCK7mcRMqtzPrfKrtTl
24.1K views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 22:13:10
በሞተር ብስክሌት፣ በባለ አራት እና ሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ነገ ይነሳል
***************

በሞተር ብስክሌቶች እንዲሁም በባለ አራት እና ሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ክልከላ ከነገ ማክሰኞ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ያነሳ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።

ሆኖም ፍቃዱ የሚመለከተው በቢሮው እውቅና ተሰጥቷቸው በማህበር ተደራጅተው መስመርና ታፔላ ያላቸው የባጃጅ አሽከርካሪዎችን ብቻ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።

ሞተር ብስክሌቶችን በተመለከተም ፍቃዱ የሚመለከተው በአዋጁ መሰረት ሰሌዳ ወስደው፣ ሕጋዊ መንቀሻቀሻ ፍቃድና ጂፒኤስ (GPS) ያስገጠሙትን ብቻ መሆኑን ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።

ከትራንስፖርት ቢሮው ሕጋዊ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ቢሮው ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ቢሮው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው ፅሁፍ አስጠንቅቋል።
19.9K views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 21:21:31
የ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት
19.2K views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 18:03:06
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን ነገ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ማየት ይችላሉ
******************

የ2015 ዓም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚከተሉት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፦

በዌብሳይት - https://eaes.edu.et/
በአጭር መልዕክት - 6284
በቴሌግራም - https://t.me/eaesbot
13.9K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 15:50:21
የዓመቱ ዲፕሎማሲያዊ ድል ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ነው፡- ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ
****************

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ አባል መሆን መቻሏ የዓመቱ ዲፕሎማሲያው ድል እንደሆነ ፕሬዝዳንት ሣህለውርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ ስራዎች ማከናወኗን አስታውሰዋል፡፡

በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ ትልቅ ድል ነው ያሉት ፕሬዝዳንቷ ይህም በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስክ መነቃቃትን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ይህን ድል እና ተሰሚነቷን በመጠቀም በባለ ብዙ ዲፕሎማሲያዊ መድረኮች ላይ ለአፍሪካ እንድትቆም አድል እንደሚሆናትም ጭምር ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ዲፕሎማሲዊ መድረኮች የተገኘው ሰኬት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በማንሳት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በድንበር ጉዳይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ይሰራል ብለዋል፡፡
13.9K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 14:36:53
በ2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎችን ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 42.8 በመቶ የሚሆኑት ምንም ተማሪ አላሳለፉም፡- የትምህርት ሚኒስቴር
**********

በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተማሪዎችን ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 42.8 በመቶ የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ውጤትን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤ ዘንድሮ 3 ሺህ 106 ትምህርት ቤቶች ፈተና ማስፈተናቸውን ጠቅሰው፤ ከነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ተናግረዋል።

ይህም በመቶኛ ሲሰላ 42.8 ከመቶ የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸው ነው በመግለጫው የተነሳው፡፡
13.3K views11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 14:03:40
ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ፡- የትምህርት ሚኒስቴር
********

በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ በድረ-ገፅ ወይም በአጭር የፅሁፍ መልእክት አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ገልጸዋል፡፡

የ2015 የትምህርት ዘመን የ12ተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ውጤትን በተመለከተ ሚኒስትሩ ለመገነኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፤ የ2015 የትምህርት ዘመን የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ 845 ሺህ 188 ተማሪዎች ውስጥ 27 ሺህ ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ በማምጣት የማለፍያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልፀዋል።

ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 3.2 ከመቶ ተማሪዎች ብቻ ማለፋቸውን የገለፁት ሚኒሰትሩ፤ ያለፉት ተማሪዎች ቁጥር ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ0.01 መቀነሱን ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02RM6qzLwZBkmuZ5zVQwvP5v4HnN1MHX1d8rbpHu9CdkEswspSaNKmxLsKJ6URzC5al
13.8K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ