Get Mystery Box with random crypto!

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የሰርጥ አድራሻ: @ebcnewsnow
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 123.82K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-10-04 19:29:38 https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=3169
የአዲስ አበባ ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 9 ተሽከርካሪዎችን በመያዝ ለባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ገለጸ
14.5K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-04 16:05:07
ሩስያ ሦስት ሀገራትን በሕዋ ጣቢያ ግንባታ ላይ እንዲሳተፉ ጋበዘች
***************************

የሩስያው ሮስኮስሞስ የሕዋ ምርምር ጣቢያ ፕሮጀክት ላይ ሦስት ሀገራት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

ከአፍሪካ በዚህ ፕሮጀክት ላይ የመሳተፍ አድል ያገኘችው ደቡብ አፍሪካ ብቻ ስትሆን፤ ብራዚል እና ቱርክ እንዲሳተፉ ተመርጠዋል።

ጥሪ የቀረበላቸው ሀገራት በዚህ ፕሮጀከት ላይ የመሳተፍ ፍላጎት የነበራቸው በመሆኑ እንዲሳተፉ እንደተደረጉ የሩስያ ስፔስ ኮርፖሬሽን ኃላፊ ዩሪ ቦሪሶቭ ገልጸዋል።

የሕዋ ምርምር ጣቢያው ግንባታ በአውሮፓውያኑ 2027 እንደሚጀመር ዕቅድ ተይዞለታል።

ጣቢያው የሕዋ ቴክኖሎጂዎችን ለመፈተሸ እንደምርምር ላቦራቶሪ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን ስፑትኒክ ዘግቧል።
16.0K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-02 21:32:43 https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=3101
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምሥራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሦስት ግዙፍ ባንኮች አንዱ መሆን ቻለ
18.5K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-02 16:39:59
በቱርክ አዲስ በራሪ መኪና ይፋ ሆነ
************

የቱርክ የኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የአቪዬሽን፣ የጠፈር እና ቴክኖሎጂ ፌስቲቫል ላይ አዲስ በራሪ መኪና ይፋ ሆኗል፡፡

የቱርክ ቴክኖሎጂ ቡድን ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ አመታዊ ፌስቲቫል ላይ ብዛት ያላቸው የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን እና ፈጠራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ በአንድ ኩባንያ የቀረበችው በራሪ መኪናም በፌስቲቫሉ ላይ ልዩ ድምቀት ነበረች።

ኤር ካር በተሰኘው ኩባንያ ውስጥ የሶፍትዌር ኢንጂነር ባለሙያ የሆነው መህመት ቱራን በራሪ መኪናዋ 450 ኪሎ ግራም እንደምትመዝን ገልጿል።

የበራሪ መኪናዋ ስራ የተጀመረው ከሶስት አመት በፊት መሆኑን የጠቀሰው ባለሙያው፤ እስካሁን ወደ 100 የሚጠጉ የሙከራ በረራዎችን በስኬት ማከናወን መቻሉን ጠቅሷል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid027TGrHGwNLFKgXLVSBDDVJc1guNpKbE7SECnPShqKe4GwYRNToStDy3Zi7Kz3kFjXl
12.9K views13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-01 21:05:01
አትሌት መስታወት ፍቅር የካርዲፍ ግማሽ ማራቶን ውድድርን አሸነፈች

**********

አትሌት መስታወት ፍቅር ዛሬ ለ20ኛ ጊዜ የተካሄደውን የካርዲፍ ግማሽ ማራቶን ውድድር በአሸናፊነት አጠናቃለች።

አትሌቷ የግማሽ ማራቶን ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ08 ደቂቃ ከ13 ማይክሮ ሰከንድ ፈጅቶባታል።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አሚነት አህመድ ግማሽ ማራቶኑን በ1 ሰዓት ከ08 ደቂቃ ከ14 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ 2ኛ ሆናለች።

በላሉ ኢታላ
14.7K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-01 20:16:21
ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን አንድ ለምንም በማሸነፍ ሊጉን በድል ጀምሯል

**********

የ2016ቱ የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሲጀመር አዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

በሊጉ የመጀመሪያ እለት ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን አንድ ለባዶ አሸንፏል።

ለኢትዮጵያ ቡና የማሸነፊያዋን ብቸኛ ግብ ኤርሚያስ ሹምበዛ በ59ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።

የፕሪሚየር ሊጉ አንደኛ ሳምንት ቀጣይ ጨዋታዎቻ የፊታችን ዓርብ የሚቀጥሉ ሲሆን፤ ሻሸመኔ ከተማ ከወላይታ ዲቻ በ9 ሰዓት እንዲሁም ሀምበሪቾ ዱራሜ ከድሬዳዋ ከተማ በ12 ሰዓት እንደሚጫወቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ያወጣው መርሃግብር ያመለክታል።


በላሉ ኢታላ
14.4K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-01 19:11:52
አትሌት ሙክታር እድሪስ እና አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ ዛሬ በጣሊያን በተካሄደ የትሬንቶ ግማሽ ማራቶን አሸነፉ

****

አትሌት ሙክታር እድሪስ እና አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ ዛሬ በጣሊያን በተካሄደ የትሬንቶ ግማሽ ማራቶን አሸንፈዋል።

በወንዶቹ ውድድር አትሌት ሙክታር እድሪስ የግማሽ ማራቶን ርቀቱን በ1 ሰዓት ከ30 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው በአንደኛነት ያጠናቀቀው።

በሴቶቹ ውድድር አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ ርቀቱን በ1 ሰዓት ከ7 ሰከንድ ከ48 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች።

አትሌት እቴነሽ ዲሮ ደግሞ ርቀቱን በ1 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ50 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

በላሉ ኢታላ
13.3K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-01 13:48:41
አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ1 ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ ክብረ-ወሰን በመያዝ አሸነፈች
******************

በላቲቪያ ሪጋ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው በ1 ማይል የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ድርቤ ወልተጂ 4 ደቂቃ ከ21 ሰኮንድ በመግባት አዲስ ክብረ-ወሰን በማስመዝገብ አሸንፋለች፡፡

በርቀቱ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡

በውድድሩ ተጠባቂ የነበረችው ኬኒያዊቷ አትሌት ፌይዝ ኪፒዬጎ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች፡፡
13.5K viewsYsehak tariku, 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-01 13:11:10
አትሌት ሃጎስ ገብረህይወት በ5 ኪሎ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ አሸነፈ
**************

ዛሬ በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው የዓለም የጎዳና ውድድር ላይ የ5 ኪሎ ሜትር ወንዶች ሩጫ አትሌት ሀጎስ ገብረህይወት የወርቅ ሜዳሊያአትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ የብር ሜዳልያ አሸንፈዋል፡፡

አትሌት ሃጎስ ገብረህይወት ርቀቱን ለመጨረስ 12 ደቂቃ ከ59 ሰኮንድ ሲፈጅበት፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ በበኩሉ ርቀቱን በ13 ደቂቃ ከ2 ሰኮንድ አጠናቋል፡፡

በውድድሩ ኬኒያዊው አትሌት ኒኮላስ ኪፕኮሪር ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የነሃስ ሜዳሊያ አሸንፏል፡፡
13.8K viewsYsehak tariku, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-30 22:00:02
ቶተንሃም ሊቨርፑልን 2 ለ 1 አሸነፈ
******************

በዘንድሮው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በ7ኛ ሳምንት ጨዋታ ቶተንሃም ሊቨርፑልን 2 ለ 1 በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 2ኛ ከፍ ማድረግ ችሏል።

https://www.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid0s5tbo1dtRmSt2EQU214xWq3GbhbmvisJzLoEqV5mpETBjLXPrupJd8T62s1FoL3Nl
15.0K viewsYona, 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ