Get Mystery Box with random crypto!

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የሰርጥ አድራሻ: @ebcnewsnow
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 124.00K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-11-13 13:50:50
በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከሀማስ ጋር ድርድር ሊካሄድ እንደሚችል ኔታንያሁ ፍንጭ ሰጡ
*************************

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከሀማስ ጋር ድርድር ሊካሄድ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።

"ስለጉዳዩ ከመናገር በተቆጠብኩ ቁጥር፤ የመሳካቱን ዕድል አሰፋዋለሁ ብዬ አስባለሁ" ብለዋል ኔታንያሁ ለኤንቢሲ ኒውስ።

በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ታጋቾች የት እንደሚገኙ ያውቁ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄም፥ "በደንብ እናውቃለን፤ ነገር ግን ስለጉዳዩ ከዚህ በላይ መናገር አልፈልግም" ብለዋል።

"የሚደረገው ማንኛውም ስምምነት የወታደራዊ ጫና ውጤት ነው" ሲሉም አክለዋል።

"ወደ ድርድር ሊያመራ የሚችለው ብቸኛው መንገድ እርሱ ነው፤ ለዚያውም ለድርድር የሚተርፍ ነገር ካለ። ጉዳዩ እዚያ ደረጃ ሲደርስ እናወራዋለን፤ ይሆን እንደሆነ ያኔ እናስታውቃለን" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በድህረ ጦርነቷ ጋዛ ሰርጥ ወደፊት ስለሚኖረው የአስተዳደር ሁኔታ ሲናገሩም፤ የአስተዳደር ለውጥ ሊያስፈልግ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ይህ አዲስ አስተዳደር ምን ቅርጽ ሊኖረው እንደሚችል ግን ያሉት ነገር የለም።
13.2K viewsNesru Jemal, 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-12 16:09:35
በቤይሩት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች ክብረ-ወሰን በማሻሻል አሸነፉ
********

በቤይሩት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች በተደረገው የማራቶን ውድድር የቦታውን ክብረ-ወሰን በማሻሻል አሸንፈዋል፡፡

በቤይሩት ማራቶን አሶሴሽን አማካኝነት በተካሄደው ውድድር በወንዶች አትሌት ጋዲሳ ጣፋ 02፡10፡34 በሆነ ሰዓት በመግባት የቦታውን ክብረ-ወሰን በማሻሻል በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ፤ አትሌት ጎጃም በላይነህ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡

በሌላ በኩል ሴቶች በተደረገው የማራቶን ውድድር አትሌት ሙሉጎጃም ብርሃን 02፡19፡32 በመግባት የቦታውን ክብረ-ወሰን በማሻሻል አሸንፋለች፡፡ https://www.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid0XEx2DVwqCC9YijUPrhFLyWK5oMEa6pd2VEsE9H14fQZPotfpSi7TVuNXToRcLSdtl
15.7K viewsYsehak tariku, 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-11 14:05:41
የኢትዮጵያ አይዶል የምዕራፍ ሁለት ውድድር ሊጀመር ነው!
*************************

የኢትዮጵያ አይዶል የምዕራፍ ሁለት ውድድር ከጥቂት ሳምንታት የዝግጅት ረፍት በኋላ በነገው እለት ህዳር 2 ቀን 2016 ዓም ይጀምራል።

ባለተሰጥኦዎች በልዩ ሁኔታ በተዘጋጀ መድረክ ሥራቸውን ለሕዝብ አቅርበው እንዲያስተዋውቁና እንዲታወቁ፣ በሞያቸው ቋሚ ሥራና ገበያ እንዲፈጥሩ ማስቻልን ዓላማው ያደረገው ይህ ውድድር፤ በየምዕራፉ ለአሽናፊዎች 1 ሚልዮን ብር እና የክብር ዋንጫ ለሽልማት ያበረክታል።

የዳኝነት ሥርዓቱ በተለያየ ሙያ ውስጥ ያሉና የጋራ ሳይሆን የየግል እይታና ልምዳቸውን፣ ከሙያ ባሻገር የስሜት ምዘናቸውን እንዲሰጡ በተመረጡ አራት ዳኞችና በ8600 በተመልካቾች ቀጥታ የSMS ምርጫ የሚከናወን ይሆናል።

በአዲስ ፎርማትና አቀራረብ ከወራት በፊት የጀመረው የኢትዮጵያ አይዶል መደበኛ ከሆኑት የድምፅ እና የተውኔት ውድድር ባሻገር በማንኛውም ዓይነት በተሰጥኦ እና በልምድ በሚገኙ አቅርቦቶች “ሰበር ተወዳዳሪዎችን” በየሳምንቱ ልዩ ተሰጥኦዋቸውን እያቀረቡ ሲሸለሙ የነበረ ሲሆን፤ በምዕራፍ ሁለት ውድድር ወቅትም ይኸው አቅርቦት እንደሚቀጥል ታውቋል።
12.7K viewsNaty Tsegaye, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-10 16:06:06
አስገራሚ እውነታዎች - ስለዝሆን
******************

• ዓለም ላይ ግዙፉ የየብስ እንስሳ ዝሆን ነው።
• የአፍሪካ ዝሆኖች ከ1600 እስከ 6300 ኪ.ግ ይመዝናሉ።
• ዝሆኖች በአማካይ ከ50 እስከ 70 ዓመት ይኖራሉ።
• ዝሆኖች በቀን ከ2 እስከ 3 ሰዓት ይተኛሉ።
• የዝሆኖች የእርግዝና ጊዜ 22 ወር (640 ቀን) ነው።
• ዝሆኖች በቀን እስከ 18 ሰዓት ምግብ በመብላት ያሳልፋሉ።
• የዝሆኖች ኩምቢ እስከ 180 ኪ.ግ ይመዝናል።
• አንድ ወጣት ዝሆን በቀን እስከ 400 ኪ.ግ ምግብ እና እስከ 200 ሌትር ውኃ ይጠቀማል።
• አንድ ዝሆን በቀን እስከ 130 ኪ.ግ እዳሪ ያስወግዳል።
• የዝሆኖች ጥርስ እስከ 200 ኪ.ግ ይመዝናል።
• ሴት ዝሆን እስከ 50 ዓመቷ ድረስ ልጅ መውለድ ትችላለች።
• ዝሆኖች እንደ ሰዎች ቀኞች አሊያም ግራኞች ናቸው።
• ዝሆኖች ልጆቻቸው ሲያጠፉ በኩምቢያቸው ይገርፋሉ።
• የዝሆን ኩምቢ ውስጥ ከ40 ሺህ በላይ ጡንቻዎች አሉ። የሰው ልጅ ሰውነት ውስጥ ያሉት ጡንቻዎች በአጠቃላይ 650 ናቸው።
• ዝሆኖች ንብ እና ጉንዳን ይፈራሉ።
• የዓለማችን ግዙፉ ዝሆን 10 ሺህ 886 ኪ.ግ ክብደት እና 4 ሜትር ቁመት ነበረው። ዝሆኑ እ.አ.አ በ1956 አንጎላ ውስጥ ነው የተገኘው።
• የዓለማችን ዕድሜ ጠገቡ ዝሆን ሊን ዋንግ ይባላል ነበር። ሕንድ ውስጥ ተወልዶ ቻይና እና ታይዋን ውስጥ የኖረው ይህ ዝሆን በ86 ዓመቱ ነበር ከዚህ ዓመት በሞት የተለየው።
• የዝሆኖች አንጎል እስከ 5 ኪ.ግ ይመዝናል። ከየብስ እንስሳት በሙሉ ግዙፍ አንጓል ያላቸው ዝሆኖች ናቸው።

https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0brqhvwPgxwwWVDzQoAnwXbi4xGQwbHky5prnQanrGdwbYN7ppgV1X26m8rohW3z5l
14.3K viewsEndalk, 13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-10 13:26:04 https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=3962
የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች የሕዳሴ ግድብን ጎበኙ
12.9K viewsYona, 10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-10 13:06:22
"ኦል አፍሪካ ፌስቲቫል አቡዳቢ"
All Africa Festival ABU DHABI
Experience the best of African
2nd – 4th February 2024
12.9K viewsNaty Tsegaye, 10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-10 12:17:43
አዲሱ ፕሮግራማችን “ዕይታ”ን ዛሬ ምሽት በኢቢሲ ዩቲዩብ ይጠብቁ
*******************************

ዘወትር አርብ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በኢቢሲ ዩቲዩብ አዲሱ የ“ዕይታ” ፕሮግራማችን መተላለፍ ይጀምራል። “ዕይታ” በፖለቲካ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚዘጋጅ ፕሮግራም ነው።
12.8K viewsEndalk, 09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-08 12:30:37
በመገባደድ ላይ ያለው የፈረንጆቹ 2023 በታሪክ ይበልጥ ሞቃታማው ዓመት እንደሚሆን ይጠበቃል
******

ከባድ የሆነ የሙቀት ማዕበል፣ ጎርፍ እና የእሳት አደጋ የተከሰተበት የፈረንጆቹ 2023 በታሪክ ይበልጥ ሞቃታማው ዓመት እንደሚሆን ይጠበቃል።

በተለይ ባለፈው ወር የተመዘገበውን ከምንጊዜውም በላይ ከፍተኛ ሙቀት ተከትሎ 2023 በታሪክ ይበልጥ ሞቃታማው ዓመት እንደሚሆን ጥርጥር የለውም ብሏል - የአውሮፓ ህብረት የአየር ንብረት ለውጥ አገልግሎት።

አገልግሎቱ እንዳለው፥ በአሁኑ ወቅት የዓለም አማካይ የአየር ሙቀት መጠን ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ተብሎ ከተመዘገበው የጥቅምት 2019 የአየር ሙቀት መጠን ጋር ሲነፃፀር በ0.4 ዲግሪ ሴልሺየስ ይበልጣል።

ያለፈው የጥቅምት ወር በካርቦን ልቀት እና በኤልኒኖ የአየር ክስተት የተነሳ በተከታታይ እየጨመረ የመጣ ከፍተኛ የአየር ሙቀት የተመዘገበበት 5ኛው ወር ነው ብሏል።

ይህ የዓለም የሙቀት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ የመጨመር ሂደት በፈረንጆቹ 2024ም ሊቀጥል እንደሚችል ተመራማሪዎችን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።
13.5K viewsYsehak tariku, 09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-07 15:49:21
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 8 ለ 1 አሸነፈ
********

ከ15 አመት በታች የሴካፋ ሻምፒዮና ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 8 ለ 1 አሸንፏል።

ቡድኑ በመጀመሪያ ጨዋታ ከደቡብ ሱዳን ጋር አንድ አቻ የተለያየ ሲሆን ከሁለት ጨዋታዎችም አራት ነጥብ ማሳካት ችሏል።

ብሄራዊ ቡድኑ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ከአዘጋጇ ኡጋንዳ ጋር እንደሚያደረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመልክቷል።
14.3K viewsYsehak tariku, 12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-05 19:51:27
አትሌት ታምራት ቶላ የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድርን አሸነፈ
**********

አትሌት ታምራት ቶላ በኒው ዮርክ በተካሄደው የማራቶን ውድድር አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡

አትሌት ታምራት ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ58 ሰኮንድ የፈጀበት ሲሆን፤ የገባበት ሰዓትም በኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር ታሪክ አዲስ ክብረ ወሰን ሆኗል፡፡

በውድድሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሹራ ቂጣታ ሶሰትኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል::

በሴቶቹ በኩል አትሌት ለተሰንበት ግደይ የኒው ዮርክ ማራቶን ውድድር ሁለተኛ በመሆን ስታጠናቅቅ፤ ኬኒያዊቷ አትሌት ሄለን ኦቢሪ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፋለች::
13.1K viewsYsehak tariku, 16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ