Get Mystery Box with random crypto!

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የሰርጥ አድራሻ: @ebcnewsnow
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 123.82K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-11-05 17:05:32

12.6K viewsBetty Sam, 14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-05 14:37:27
ከ10 ዓመታት በኋላ የአፍሪካ ጂኦተርማል ኢነርጂ የማመንጨት አቅም ከአውሮፓ እንደሚበልጥ ይጠበቃል
*****************

በሪስታድ ኢነርጂ የቅርብ ጊዜ ትንበያ መሠረት፥ የአፍሪካ የጂኦተርማል ዘርፍ በ2050 ቢያንስ 35 ቢሊዮን ዶላር ኢንቬስትመንት ይስባል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም በፍጥነት እያደገ የመጣውን የአህጉሪቱን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት ዘርፉ ወሳኝ ሚና መጫወት ይጀምራል።

በዚሁ ትንበያ መሠረት፥ በአፍሪካ የጂኦተርማል ኢነርጂ ዘርፍ ላይ እየፈሰሰ ያለው መዋዕለ ንዋይ በዚሁ ከቀጠለ፤ ከአስር ዓመታት በኋላ የአፍሪካ ጂኦተርማል ኢነርጂ የማመንጨት አቅም ከአውሮፓ እንደሚበልጥ ይጠበቃል።

ምንም እንኳ የአፍሪካ ጂኦተርማል ኢነርጂ የማመንጨት አቅም አሁን ላይ የአውሮፓን ግማሽ ወይም ወደ 1 ጊጋ ዋት ገደማ ብቻ ቢሆንም፤ እኤአ በ2030 የአፍሪካ ጂኦተርማል ኢነርጂ የማመንጨት አቅም በእጥፍ ያድጋል።

በነገራችን ላይ፥ ይህ ስሌት ታሳቢ ያደረገው እስካሁን ይፋ የተደረጉ የጂኦተርማል ኢነርጂ ፕሮጀክት ዕቅዶችን ብቻ ነው፤ ወደ ፊት ይፋ የሚደረጉ የጂኦተርማል ኢነርጂ ፕሮጀክት ዕቅዶች ሲታከሉበት እኤአ በ2030 የአፍሪካ የማመንጨት አቅም በሁለት እጥፍ ሊድግ ይችላል።

እኤአ በ2050 የአፍሪካ ጂኦተርማል ኢነርጂ የማመንጨት አቅም ወደ 13 ጊጋ ዋት እንደሚያድግ ይጠበቃል፤ ይህም በተጠቀሰው ወቅት አውሮፓ ትደርስበታለች ተብሎ ከሚጠበቀው የ5.5 ጊጋዋት አቅም ጋር ሲነፃፀር ከእጥፍ በላይ ነው።

በተጠቀሰው ወቅት፥ ኢትዮጵያ እና ኬንያ 90 ከመቶ የሚጠጋውን የአፍሪካን ጂኦተርማል ኢነርጂ የማመንጨት አቅም ጠቅልለው በመያዝ የአህጉሪቱን የጂኦተርማል ኢነርጂ ዘርፍ ዕድገት ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
12.7K viewsNesru Jemal, 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-04 14:42:38
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት ከፍተኛ የክብር ሽልማት ተበረከተላት
*****

የጃፓን መንግስት ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የሃገሪቱን ከፍተኛ የወርቅ ኒሻን እውቅና መስጠቱን አስታውቋል።

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል በስፖርታዊ ዲፕሎማሲ እና ልውውጥ ዘርፍ ላበረከተችው የላቀ አስተዋፅዖ ነው የሃገሪቱን ከፍተኛ የወርቅ ኒሻን ሽልማት የተበረከተላት፡፡

ከስፖርት ዲፕሎማሲ ጋር በተያያዘ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በፈረንጆቹ 2014 ሟቹ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አበይ በአዲስ አበባ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን በማሰባሰብ የውይይት መድረክ እንዲመቻች ማድረጓ ተገልጿል፡፡
https://www.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid08horCwr7TxQp4mJDtt9DF4U3Myoj4zjJnrmaCWkkt3f8tRqJSDekepEcCySWPX1hl
14.5K viewsYsehak tariku, 11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-04 12:04:55
በኔፓል በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ
******

በምዕራብ ኔፓል በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ100 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ ከዋና ከተማዋ ካታማንዱ በ500 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኙ ጃጃርኮት እና ሩኩም የተባሉ ከተሞችን መምታቱ ተነግሯል፡፡

በርዕደ መሬት መለኪያ 5.6 ማግኒቲዩድ ሆኖ የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረቱ እስከ ጎረቤት ሀገር ህንድ ድረስ ተሰምቷል ነው የተባለው፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ሰዎች በጃጃርኮት ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፑሽፓ ካማል ዳሃል ጉዳት የደረሰበትን ክልል የጎበኙ ሲሆን የተጠናከረ የነብስ አድን ስራ እንዲሰራ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
13.8K viewsYsehak tariku, 09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-04 11:19:46
በሶማሌ ክልል በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ቢሮ ገለፀ
*********

በክልሉ ሰሞኑን እየዘነበ በሚገኘው ከባድ ዝናብ ሳቢያ በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ የጎርፍ አደጋ መከሰቱን በቢሮው የቅድመ ማስጠንቀቂያ አስተባባሪ በሺር አረፕ አስታውቀዋል።

በጎርፍ አደጋው እስካሁን ከ20 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የገለፁት ሀላፊው፤ ከ12 ሺህ በላይ አባወራዎች መፈናቀላቸውንም ተናግረዋል።

በተጨማሪም በእንስሳት ሀብት፣ በሰብል እና በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።

የሶማሌ ክልል መንግሥት እና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ግብረሰናይ ድርጅቶች የዕለት ደራሽ እርዳታዎችን ለማድረስ እየሰሩ ቢሆንም፤ ድልድዮችና መንገዶች በጎርፉ በመወሰዳቸው ስራውን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል አስተባባሪው።

እየጨመረ ያለው የዝናብ መጠን እና ትንበያዎች እንደሚያሳዩት የጎርፍ አደጋው ስጋት አሁንም ከፍተኛ ነው።

በሞላ አለማየሁ
12.8K viewsYsehak tariku, 08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-04 09:47:13
የደረሱ ሰብሎችን በመጪዎቹ 10 ቀናት መሰብሰብ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ
**

በመካከለኛው፣ በምሥራቅና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል፤ የደረሱ ሰብሎችን በመጪዎቹ 10 ቀናት መሰብሰብ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳስቧል።

ኢንስቲትዩቱ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ይጠበቃል።

ይህም ሁኔታ በደረሱ ሰበሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄና ዝግጅት በማድረግ የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ ተግባር ማከናወን ይኖርባቸዋል።
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02K5mpkq3hCxw8GDuZq7n3hq4ExizXdx4WVzg3PFaF6Guo5Yih9YNhrWspKQas9gG7l
13.8K viewsYsehak tariku, edited  06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 15:53:44
መዲና ኢሳ በዓለም ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ምርጥ አትሌት ምርጫ ፍጻሜ ደረሰች
*********

የዓለም አትሌትክስ ፌዴሬሽን የ2023 ከ20 ዓመት በታች ሴት አትሌቶችን ሦስት የፍጻሜ እጩዎችን ያስተዋወቀ ሲሆን፣ ኢትዮጵያዊቷ መዲና ኢሳ ከሦስቱ እጩዎች እንዷ ሆናለች፡፡

እጩዎቹ በዘንድሮው የወድድር ዓመት በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ በባቱርስት የዓለም አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና፣ በሪጋ የጎዳና ላይ ሩጫ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና በሌሎች ውድድሮች ባሳዩአቸው አስደናቂ ብቃት እንደተመረጡ ፌዴሬሽኑ በገጹ አስታውቋል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0KH8cbtoKM94mUMXqAWDgo8M4FPg7FkSkaroXvUHT5qCPxCTVEcA4s8yJdZPiP9Tfl
15.4K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-03 13:46:26
የጋዛ ጦርነት የሚባባስ ከሆነ የዓለም ኢኮኖሚን 2 ትሪሊዮን ዶላር ሊያሳጣ ይችላል - የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች
********

በእስራኤል ጦር እና በሐማስ ታጣቂ ቡድን መካከል እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት ተባብሶ የሚቀጥል ከሆነ የዓለም ኢኮኖሚን 2 ትሪሊዮን ዶላር ሊያሳጣ እንደሚችል የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ገለፁ።

ኧርነስት ኤንድ ያንግ የተሰኘው ተቋም ዋና ኢኮኖሚስት የሆኑት ግሪጎሪ ዳኮ፤ ጦርነቱ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ዋጋ ንረትን በማባባስ እና የአክስዮን ዋጋ እንዲቀንስ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ብለዋል፡፡

ጦርነቱ የሚቀጥል ከሆነ የዓለም ነዳጅ ዋጋ አሁን ካለው 85 ዶላር ወደ 150 ዶላር ሊያደርሰውም ይችላል ነው ያሉት ኢኮኖሚስቱ፡፡

ጦርነቱ በዚህ ከቀጠለ እና ነገሮች ወደ ከፋ ሁኔታ የሚለወጡ ከሆነ በ1970ዎቹ ከነበረው የነዳጅ ቀውስ ጋር የሚመሳሰል ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ተገልጿል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0eKTvxWKSronsrCmDq2z8dTHSZ4Vw2gKUEowAC2hKAxLi3aZMpYp8FNHVy8oaqzLxl
15.3K views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-02 16:30:44 https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=3761
የዓለም ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጄታ - ከኦለንኮሚ እስከ ነጩ ቤተመንግሥት
13.8K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-01 10:07:58
ሳያስቡት ሰው ገድለው ይሆን?
17.0K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ