Get Mystery Box with random crypto!

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የሰርጥ አድራሻ: @ebcnewsnow
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 123.82K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-10-23 15:23:59
3ኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በካይሮ ተጀመረ
********

ሶስተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅ ደንቦች እና መመሪያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ በካይሮ ተጀምሯል።

በድርድሩ ላይ ባልተፈቱ የቴክኒካል እና የህግ ማእቀፍ ጉዳዮች የተሻለ ውጤት ላይ ለመድረስ ትኩረት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ወገን ተደራዳሪዎች ልኡካን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2015 በመሪዎች ደረጃ የተፈረመው የመርሆች መግለጫ ስምምነት መሰረት ድርድሩን በፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርህ መሰረት ውጤት ላይ ለመድረስ እንደምትሰራም አምባሳደር ስለሺ ገልጸዋል፡፡
15.2K views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-23 15:09:20 https://ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=3533
ወርቃማው ኃይል ላይ የበረታው የጭንቀት በሽታ
13.3K views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-23 14:47:24
ትምህርት ሚኒስቴር የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና የመቁረጫ ነጥብን ይፋ አደረገ
*************

የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የአገራዊ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (National GAT) የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፤ አጠቃላይ ለፈተና ከቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ 62 (50 በመቶ) እና ከዚያ በላይ ጥያቄዎችን የመለሱ ወይም 80 ፐርሰንታይል (80 Percentile) ያገኙ ተፈታኞች ወደሚፈልጉበት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም አመልክተው መማር እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመልካቾች ለማመልከት ሲመጡ ውጤታቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus በመግባት እና የተማሪውን የመግቢያ ስም (Username) እና የይለፍ ቃል (Password) በመጠቀም ማረጋገጥ ይቻላሉ ተብሏል።

በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት፤ በሁሉም የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾች፤ በሙሉ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (National Graduate Admission Test - NGAT) ተፈትነው ያለፉ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አቅጣጫ መቀመጡ ይታወሳል።
13.7K viewsedited  11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 21:13:50

14.7K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 11:58:16
#ነጋድራስ የሥራ ፈጠራ ውድድር በዛሬው ተጠባቂ ፕሮግራሙ ብርቱ ፉክክር ይዞ ይቀርባል::
ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በኢቲቪ ዜና ቻናል እና የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ይተላለፋል::
እንድትከታተሉ ተጋብዛችኃል
16.5K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-21 10:25:55
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቻይና የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገቡ
**********
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቻይና የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት እና የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ ተሳትፎን አጠናቀው ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቻይና የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መግባታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
13.2K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-20 21:45:16
የነጋድራስ የስራ ፈጠራ ውድድር
እሁድ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በኢቲቪ ዜና ቻናል ይጠብቁን።
13.9K viewsedited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-20 20:51:17
በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻሸመኔ ከተማን 3 ለ 2 አሸነፈ
************

በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሦስተኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሻሸመኔ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 3 ለ 2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ብርቱ ፉክክር በታየበት በዚህ ጨዋታ ለቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂው አቤል ያለው እና በረከት ወልዴ ግቦችን ሲያስቆጥሩ፤ ለሻሸመኔ ከተማ ያሬድ ዳዊት እና አለን ካይዋ ግቦችን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

መደበኛው የጨዋታ ጊዜ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሁለቱ ቡድኖች ሁለት አቻ የነበሩ ሲሆን፤ አጥቂው አቤል ያለው በተጨማሪ ሰዓት በፍፁም ቅጣት ምት ባስቆጠራት ግብ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡
13.7K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-20 18:37:55
"ሱፐር ስፖርት (ዲኤስ ቲቪ) ጥሎ አልወጣም በቅርቡ ይመለሳል" - ሊግ ካምፓኒው
********

የ2016 የኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ቢገኝም የሳምንቱ መርሃግብሮች በሱፐር ስፖርት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደማይኖራቸው በፕርምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር በኩል ተገልጿል።

ቀደም ብሎ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድን ግጥሚያዎች ምክንያት ስርጭት እንዳልተሰጠው መገለጹም ይታወቃል።

የዚህ ሳምንት የሊጉ መርሃግብሮች በተመሳሳይ መንገድ መቀጠላቸው በሊጉ ተከታታዮች ዘንድ ጥያቄን አስነስቷል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የሊጉ አክሲዮን ማህበር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ ከኢትዮጵያ ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ሱፐር ስፖርት ውሉን አቋርጦ አልወጣም ፤ የቀጥታ ስርጭት አጋዥ ዕቃዎች ሲሟሉ የቀጥታ ስርጭቱ ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ እንደሚመለስ ገልጸዋል፡፡
https://www.facebook.com/EBCSPORT/posts/pfbid0w3u4jBNyF2NnHSfmNCcMeEQDXAuBqmWqDYUvM8r7iXFqzSrhvERYFKsMhQfTxv1Hl
13.8K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-20 11:48:43
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል የሞባይል ገንዘብ ዝውውር ፈፃሚ ድርጅት የሙከራ ጊዜውን አጠናቅቆ ወደ ስራ ገባ
********************

ካቻ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት የሙከራ ትግበራ ጊዜውን አጠናቅቆ ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሂዷል።

ክፍያ መፈፀም፣ ገቢና ወጪ ማድረግ፣ የዲጂታል ብድርና ኢንሹራንስ መስጠት ካቻ ዲጂታል ፋይናንስ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል ናቸው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የካቻ ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎት ወደ ስራ መግባት አካታች የፋይናንስ አገልግሎትን ለመስጠት በምናደርገው ጥረት ውስጥ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid02HfkP1A633oFFjE1HroyfZimMRM2bN5qWZcTaQfRAnVhnh7CxwGQpXV1hiLJ5UQhtl
15.0K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ