Get Mystery Box with random crypto!

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebcnewsnow — EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
የሰርጥ አድራሻ: @ebcnewsnow
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 124.00K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Broadcasting Corporation (EBC)

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-10-09 13:43:45
በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛው ውጤት ከአዲስ አበባ ከተማ 649 ሆኖ ተመዘገበ
**********

በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከአዲስ አበባ ከተማ 649 ከፍተኛ ውጤት መሆኑን እና በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የተመዘገበ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ 2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጤትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በማህበራዊ ሳይንስ 533 ከደብረ ማርቆስ ከተማ ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

በፈተናው ከ50 በመቶ በላይ ያገኙ ተማሪዎች 27 ሺህ 267 ተማሪዎች መሆናቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ ይህም በመቶኛ ሲሰላ 3 ነጥብ 2 ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ፈተናው አምስት ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ ለሙሉ ማሰለፍ መቻላቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ሌሎች 5 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ውስጥ 95 ከመቶውን ማሳለፋቸውን ተናግረዋል።
12.7K views10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 12:52:21
በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ50 በመቶ በላይ ያገኙ ተማሪዎች 3 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ ናቸው፡- የትምህርት ሚኒስቴር
**************

በ2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 3.2 በመቶ ብቻ ከ50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡

አሁንም በከተማ እና ገጠር ትምህርት ቤቶች መካከል ያለው ልዩነት ከፍተኛ ሆኖ መታየቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ 2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጤትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ነው።
14.7K viewsedited  09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 10:29:26
በአፍጋኒስታን በደረሰው ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር 2 ሺህ 400 አለፈ
**********

ቅዳሜ እለት በአፍጋኒስታን በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስከአሁን 2 ሺህ 445 ሰዎች መሞታቸውን ሀገሪቷን እየመሩት ያሉት የታሊባን ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

በዚህ አደጋ 10 ሺህ ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው በሁለት ግዛቶች የሚገኙ የ2 ሚሊዮን ዜጎች መኖሪያ የነበሩ 12 መንደሮች ሙሉ ለሙሉ ጠፍተዋል ተብሏል፡፡

አሁንም በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ እና አደጋ የደረሰባቸውን ዜጎች የመታደጉ ስራ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ የተባለው አደጋ በሬክተር ስኬል 6.2 መሆኑን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመልክቷል፡፡

አፍጋኒስታን ከዚህ ቀደምም በፈረንጆቹ 2022 አጋጥሟት በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ1000 በላይ ዜጎቿን ማጣቷን ሮይተርስ በዘገባው አስታውሷል።
14.2K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 00:19:17
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለእስራኤል ወታደራዊ እርዳታ ልከዋል
**********************

ጋዛ ሰርጥን እያስተዳደረ የሚገኘው ሐማስ በደቡብ እስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተጨማሪ ወታደራዊ ድጋፍ ወደ እስራኤል መላካቸው ተገልጿል።

ፕሬዚዳንቱ “ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ እና አሰቃቂ” የተባለው ጥቃት ዙሪያ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር መነጋገራቸውን ኋይት ሐውስ ገልጿል።

መግለጫውን የሰጡት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፣ በሐማስ ከተገደሉ እና ከተማረኩ ሰዎች መካከል የአሜሪካ ዜጎች መኖራቸውን ለማረጋገጥ ሀገራቸው እየሠራች መሆኑን ተናግረዋል።

የፍልስጤሙ ሐማስ በእስራኤል ላይ ባደረሰው የአየር፣ የየብስ እና የባህር ጥቃት ከ600 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና 100 ሰዎች መታገታቸውን ሀገሪቱ ገልጻለች።

https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0tvvNjDK8Tq7uZA2APpvGsjdopyDuXRFLNg3YT7B9eDjqvsh7Ma4a3agMMtAd2muvl
15.6K views21:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-08 20:40:48
አርሰናል ማንቸስተር ሲቲን 1ለ0 አሸነፈ
********************
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከ2015 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሊጉ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የአርሰናልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ጋብሬል ማርቲኔሊ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ማንችስተር ሲቲዎች በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።
ብራዚላዊው ተጨዋች ጋብሬል ማርቲኔል ለአርሰናል 34ኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
አርሰናል ከቶተንሀም ጋር እኩል ነጥብ እና ጎል ቢኖራቸውም ብዙ ባገባ በሚለው ህግ በ20 ነጥብ ሁለተኛነት ደረጃን ማግኘት ችሏል።
15.8K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-05 19:42:28 በሀገር ደኅንነት ላይ ሥጋት በሚፈጥር እና የውጭ ምንዛሪን በሚያሳጣ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ 30 ግለሠቦችና የተለያዩ መሣሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
*****************

በአዲስ አበባ፣ ሸገር ከተማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ፣ አዳማ፣ ሃዋሳ እና ጂማ ከተማ በተደረገ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ከ73 በላይ የቴሌኮም ማጭበርበሪያ ማሣሪያ እና 30 ተጠርጣሪ ግለሠቦች እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር፣ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር በመተበበር እንዲሁም ከቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ባለሙያዎችና ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ላለፉት ሦስት ወራት በቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል ተዋንያን ላይ ጥብቅና ምስጢራዊ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተቋማቱ ግኝቱን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን በላኩት የጋራ መገለጫ አመልክተዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተለያዩ የግለሠብ ቤቶችንና ግቢዎችን በመከራየት የማጭበርበሪያ መሣሪያዎችን ተጠቅመው ወንጀሉን ሢሰሩ መቆየታቸውን ያስታወቀው መግለጫው፤ ለዚሁ ሕገ ወጥ ተግባር ሲውሉ የነበሩ ከ200 ሺ በላይ የሳፋሪኮም እና ኢትዮቴሌኮም ሲም ካርዶች መያዛቸውን አመልክቷል፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉ የማጭበርበሪያ ጌትዌይ መካከልም በአንድ ጊዜ 127 የኢትዮቴሌኮም ወይም ሳፋሪኮም ሲም ካርድ መያዝ የሚችል መሣሪያ መገኘቱንም ጠቁሟል፡፡

https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=3200
14.3K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-05 15:55:47
ትምህርት ለሰፊው ሕዝብ ተደራሽ እንዲሆን ትልቅ ተጋድሎ ያደረጉት የሃገር ባለውለታ፡- ብርጋዲየር ጄኔራል ታደሰ ብሩ
***************

ብርጋዲየር ጄኔራል ታደሰ ብሩ የኦሮሞ ሕዝብ ለእኩልነትና ለፍትሕ ባደረገው የዘመናት ትግል ውስጥ ጉልህ ሚና እንደተጫወቱ ይነገርላቸዋል፡፡

በቀዳማዊ አጼ ኃይለስላሴ አስተዳደር ውስጥ ቁልፍ የአስተዳደር ሚና የነበራቸው ጀኔራል ታደሰ ብሩ፤ ለደቡብ አፍሪካውን የነጻነት ተምሳሌት ለሆኑት ኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና የሰጡ፤ በኋላም በኢትዮጵያ ውስጥ ለነጻነት እና ለእኩልነት የታገሉ ታላቅ የሃገር ባለውለታ ናቸው፡፡

ይህ ያለንበት ሳምንት ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ ትርጉም ያለው የኢሬቻ በዓል የሚከበርበት ሳምንት እንደመሆኑ ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነትና እክኩልነት ሁለንተናዊ ትግል ያደረጉትን ብርጋዲየር ጄኔራል ታደሰ ብሩን የዛሬው የአውደ ሰብ ባለታሪካችን አድርገናቸዋል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0VfX547FSAuVhGj94j6Rr7fiXQa4Squ2zUaR9ae5L1nqD5neLyf2VYFJm5ER3aLUPl
14.5K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-05 11:06:22
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣት አመራሮች ቀዳሚ ሆኑ
*********

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ 100 የአፍሪካ ምርጥ ወጣት መሪዎችን ባወጣው ቾይስዩኤል 100 አፍሪካ ቀዳሚ መሆን ችለዋል።

ቾይስዩኤል 100 አፍሪካ በየዓመቱ በቾይስዩኤል ኢንስቲትዩት ጥናት ተደርጎ በኢኮኖሚ፣ በማህበረሰብ ነክ እና በባህል ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ 100 ወጣት መሪዎችን ይፋ የሚያደርግ የጥናት ውጤት ነው።
14.3K views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-05 10:31:57
ቴሌብር የ2023 የፊውቸር ዲጂታል ሽልማት አሸናፊ ሆነ
*************

ቴሌብር የአውሮፓውያኑ 2023 የፊውቸር ዲጂታል ሽልማትን በምርጥ የሞባይል ገንዘብ አቅርቦት ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ጁኒፐር ሪሰርች የ2023 የፊውቸር ዲጂታል ሽልማት አሸናፊዎችን ይፋ ሲያደርግ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፋይናንስ አገልግሎቶችንና ክፍያዎችን በመፈጸም ምርጥ ያላቸውን ይፋ አድርጓል፡፡
https://www.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0wuMw13qmAKf3wFwUpMvCfYECQnrzqkpdzyQdD6gfvLAwpttRRB7Lm82yfFKfCkW8l
14.1K views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-04 21:28:40 https://www.ebc.et/newsdetails.aspx?newsid=3172
የ2030ው የዓለም ዋንጫ በሦስት አህጉሮች ውስጥ ይካሄዳል፦ ፊፋ
14.8K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ