Get Mystery Box with random crypto!

በአፍጋኒስታን በደረሰው ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር 2 ሺህ 400 አለፈ ********** | EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

በአፍጋኒስታን በደረሰው ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር 2 ሺህ 400 አለፈ
**********

ቅዳሜ እለት በአፍጋኒስታን በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስከአሁን 2 ሺህ 445 ሰዎች መሞታቸውን ሀገሪቷን እየመሩት ያሉት የታሊባን ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

በዚህ አደጋ 10 ሺህ ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው በሁለት ግዛቶች የሚገኙ የ2 ሚሊዮን ዜጎች መኖሪያ የነበሩ 12 መንደሮች ሙሉ ለሙሉ ጠፍተዋል ተብሏል፡፡

አሁንም በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ እና አደጋ የደረሰባቸውን ዜጎች የመታደጉ ስራ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ የተባለው አደጋ በሬክተር ስኬል 6.2 መሆኑን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመልክቷል፡፡

አፍጋኒስታን ከዚህ ቀደምም በፈረንጆቹ 2022 አጋጥሟት በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ1000 በላይ ዜጎቿን ማጣቷን ሮይተርስ በዘገባው አስታውሷል።