Get Mystery Box with random crypto!

Dr. Eyob Mamo

የሰርጥ አድራሻ: @dreyob
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.56K
የሰርጥ መግለጫ

Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-10 05:06:44 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን፣

እንኳን ለየኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ።

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
14.2K views02:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 05:00:00
የትኩረት ለውጥ!

ከሰዎች ጋር ባላችሁ ግንኙነት . . .

1. ያልሆናችሁት ላይ ሳይሆን የሆናችሁት ላይ አተኩሩ፡፡


ያልሆናችሁት ላይ ስታተኩሩ የሆናችሁትን እውነተኛ ማንነት መኖር ያስቸግራችኋል፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት እንዳገኛችሁት ሰው ሁኔታ ያልሆናችሁትን ማንነት እየለዋወጡ መኖር ነው፡፡

2. የሌላችሁ ላይ ሳይሆን ያላችሁ ላይ አተኩሩ፡፡

የሌላችሁ ነገር ላይ ስታተኩሩ ያላችሁን ነገር በትክክለኛው መንገድ መጠቀም ያስቸግራችኋል፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት ከሌላችሁ ነገር በመነሳት በዝቅተኝነት ስሜት የመመታት ሁኔታ ነው፡፡

3. የማታውቁት ላይ ሳይሆን የምታውቁት ላይ አተኩሩ፡፡

የማታውቁት ላይ ስታተኩሩ የምታውቁትን እውቀት ተግባራዊ ማድረግ ያስቸግራችኋል፡፡ የዚህ ሁኔታ ውጤት እውቀታችሁን ተጠቅማችሁ ከማደግ ይልቅ ስለማታውቁት ነገር በማሰብ ጊዜን መፍጀት ነው፡፡

ወሳኙና ጨዋታውን የሚለውጠው ነገር ትኩረታችሁ ነው፡፡ የሆናችሁት፣ ያላችሁና የምታውቁት ነገር ላይ ስታተኩሩና ቀና ብላችሁ በድፍረት ስትኖሩ፣ ያልሆናችሁት፣ የሌላችሁና የማታውቁት ነገር ላይ የመስራትና የማደግም እድላችሁ የሰፋ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
14.2K views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 05:01:56
የጭንቀት ሱስ

የጭንቀት ሱስ ማለት፣ “ሁሉም ነገር አሁኑኑ መፍትሄ ካልተሰጠው በስተቀር ከቁጥጥር ውጪ ይሆናል” በማለት የመጨናነቅ ልማድ ማለት ነው፡፡

ከዚህ አይነቱ የጭንቀት “ሱስ” ለመላቀቅ በየዕለቱ የሚገጥሙንን ሁኔታዎች ከፋፍሎ ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

1. አፋጣኝ ትኩረት የሚፈልጉ ነገሮች

ትኩረት ሰጥተን መፍትሄ ካላገኘንላቸው አስጊ የሆኑ ሁኔታዎች፡፡

“ምን አስጨነቀኝ” በሚል ሰበብ እነዚህን ሁኔታዎች ችላ ካልን ጊዜው ከዘገዬ በኋላ እንድንባንን እንሆናለን፡፡ ለምሳሌ፣ እንደ ህመም ያለ፣ ወይም ደግሞ የልጆች ባህሪይ ሲበላሽ እንደማየት ያሉትን ሁኔታዎች እያዩ ከመጨነቅም ሆነ ከመዘናጋት ይልቅ በቶሎ መፍትሄ የሚገኝበትን መንገድ መፈለግ ተገቢ ነው፡፡

2. ትንሽ ጊዜ የሚሰጡን ነገሮች

ከእነሱ ለባሱ ነገሮች ትኩረት ብንሰጥ ጊዜን የሚሰጡን ሁኔታዎች፡፡

ከአስቸኳይ ሁኔታዎች እኩል ለእነዚህ ሁኔታዎች መጨናነቅ መስመር ወደሳተ ስሜታዊነት ይጨምረናል፡፡ ለምሳሌ ከአንድ አመት በኋላ የሚከፈል መጠኑ አነስተኛ የሆነ ብድር ካለብን አሁን በእጃችን ላይ ያሉ ሌሎች አጣዳፊ ሁኔታዎች ላይ ለማተኮር ጊዜ ሊሰጠን ስለሚችል ከመጨነቅ ይልቅ እቅድ ማውጣቱ ተመራጭ ነው፡፡

3. ዝም ብንላቸው በራሳቸው ጊዜ መስመር የሚይዙ ነገሮች

መጨነቅም ሆነ ምንም ምላሽ ልንሰጣቸው የማይገባን ሁኔታዎች፡፡

አንዳንድ ሁኔታዎች የራሳቸውን ጊዜ ጨርሰው እስኪተነፍሱ ድረስ መተው ያለብን ነገሮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፣ በየጊዜው የሚቀያየር ባህሪይ ያላቸው ሰዎች ይህ እንደነፋስ እየመጣ የሚሄደውን ባህሪያቸውን እያሰቡ ለመፍትሄ ከመጨነቅ ይልቅ ዝም ብሎ በሌሎች ወሳኝ ነገሮች ላይ ማተኮር ይበጃል፡፡ እነሱ ሲበቃቸውና ሲሰለቻቸው ያቆማሉ፡፡

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
13.9K views02:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 05:01:59
በመጀመሪያ ታከሙ

ካለፈው ስቃዩ ያልዳነ ሰው እድሜ ልኩን ሰዎችን እንዳሰቃየ ይኖራል፡፡ ለዚህ ነው በአንድ የስሜትና የስነ-ልቦና ህመም በሚዳርግ ልምምድ ውስጥ ካለፍን በኋላ ወደሌላ ግንኙት ዘልቀን ከማለፋችን በፊት ከመጀመሪያው ሕመም መዳናችንን እርግጠኞች መሆን ያለበን፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ሲጎዱንና ሁለንተናችን ሲቃወስ ያንን ጉዳት ባለመልቀቃችን ሰዎቹን የምንበቀላቸውና የምንጎዳቸው ይመስለናል፡፡ እውነቱ ግን ከዚያ የራቀ ነው፡፡ በሰዎች ከደረሰብን የጉዳት ቀውስ መዳንና መውጣት የሚጠቅመው እኛንው ነው፡፡

የትናንትናውን ቁስሌን በተገቢው መልክ አክሜ ካልዳነ የዛሬውን ግንኙቴን ያዛባዋል፡፡ የዛሬው ግንኙነቴ መዛባት ደግሞ ለነገው ቁስል ይዞ ስለሚቆይ ዑደቱ እንደቀጠለ ይኖራል፡፡

በቅርብ ጓደኛ፣ በፍቅረኛ፣ በስራ አጋር፣ በአለቃ . . . ከተጎዳችሁ በኋላ ሌላ ተመሳሳይ ግንኙነት ውስጥ ዘልቃችሁ ከመግባታችሁ በፊ በመጀመሪያ ቁስላችሁን በሚገባ መታከማችሁን እርግጠኞች ሁኑ፡፡

ስፍራን መቀየርና ጓደኛን መለወጥ ያለው የራሱ የሆነ ጥቅም እንደተጠበቀ ሆኖ ዘላቂ መፍሄ ያለው ግን ከአንድ አቁሳይ ልምምድ በኋላ ሌላ ምንም አይነት የጠለቀ ግንኙነት ውስጥ ከመግባታችን በፊት ራሳችን ላይ መስራት ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
15.2K views02:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 18:48:27 “የምትኖረው በሰዎች ተቀባይነትን ለማግኘት ከሆነ፣ በሰዎቹ ተቀባይነትን ያጣህና የተገፋህ ቀን ትሞታለህ” – Lacrae

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
16.1K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 05:01:18 አራቱ የተዛቡ የጊዜ አጠቃቀም ገጸ-ባህሪያት

(“የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

1. “አቶ የአደጋ ጊዜ ተጠሪ”

ልክ የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች ተግባራቸው በየቦታው እየበረሩ የተነሳን እሳት ማጥፋት እንደሆነ “አቶ የአደጋ ጊዜ ተጠሪ” እዚህና እዚያ ብቅ ለሚሉ ሁኔታዎች ምላሽ በመስጠት ጊዜውን የሚያሳልፍሰው ነው፡፡ ለተለያዩ ችግሮች ምላሽ በመስጠት ከመሯሯጡ የተነሳ ቁጭ ብሎ ጊዜውን በሚገባ ለመጠቀም የሚረዳውን እቅድ ለማውጣት “ጊዜ” የለውም፡፡ ልክ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ከዚህኛው ወደዚያኛው እሳት እንደሚጣደፉ፣ እንዲህ አይነቱ ሰው ብዙውን ጊዜ ከስፍራ ወደ ስፍራ በፍጥነት ሲዘዋወርና በወቅቱ ሃሳቡን ለሳበው ችግር ምላሽ ለመስጠት ሲሯሯጥ ይታያል፡፡

ይህ አይነቱ ዝንባሌ አብዛኛውን ጊዜ ምንጩ የአስተዳደግ ሁኔታ ነው፡፡ አንድ ሰው ለተደወለው ስልክና ተከሰተ ለተባለው ችግር ሁሉ በድንገት ብድግ በማለት በሚሮጡ ቤተሰቦች መካከል ካደገ ያንንው ተምሮ ነው የሚያድገው፡፡

2. “አቶ አስደሳች”

የ“አቶ አስደሳች” ችግር “እምቢ” ለማለት ያለመቻል ችግር ነው፡፡ አንድ ሰው አንድን ነገር እንዲያደርግለት ከጠየቀው፣ ጊዜ ባይኖረው እንኳ “እሺ” በማለት ቃል ይገባል፡፡ ሰውን ሁሉ የመሸኘቱ፣ ለቸገረው ሁሉ ገንዘብ አበዳሪነቱ፣ ከአቅሙ በላይ ቢሆንም እንኳ የተጠየቀውን ስራ ሁሉ በእሺታ የመቀበሉ ዝንባሌ ጊዜ አጠቃሙን ከመስመር አውጥቶበታል፡፡

“አቶ አስደሳች” በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ከሁለትና ከሶስት ሰዎች ጋር ቀጠሮ ሊይዝ ይችላል - በመዘንጋት ሳይሆን እምቢ የማለት የፈቃድ ጉልበት በማጣት፡፡ እንዲህ አይነት ሰው ከአምስትና ከስድስት ኮሚቴዎች በላይ አባል ሆኖ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡እንዲህ አይነቱ ዝንባሌ ከዝቅተኝነት ስሜትና ተቀባይነት ለማግኘት ከሚኖር የውስጥ ምኞት ወይም ደግሞ የሰውን ስሜት ላለመጉዳት ካለ ጽኑ ፍላጎት ሊመነጭ ይችላል፡፡ “አቶ አስደሳች” ብዙ ጊዜ ከሰዎች ሲደበቅ ይታያል - ይህንን አድርግልኝ ተብሎ ተጠይቆ እምቢ ከሚል መደበቁን ይመርጣል፡፡

3. “አቶ ጊዜ አለኝ”

“አቶ ጊዜ አለኝ” አንድን ነገር የሚተገብረው ሲመቸው ወይም “ሙዱን” ሲያገኝ ነው፡፡ ዘና ያለ፣ መጨናነቅ የማይወድና ብዙውን ጊዜ እግሩን ጠረጴዛ ላይ ሰቅሎ የሚታይ ሰው ነው፡፡ ተግባሮቹን ቅደም ተከተል የማስያዝ ልማድ ባይኖረውም በውስጥ ታዋቂነት ግን ማድረግ ደስ ከሚለው ተግባር መጀመር እንደሚወድ እውቅ ነው፡፡ አንድ ነገር ደስ የሚለው ከሆነ ጊዜ አያጣለትም፡፡ በመቀጠልም ለማድረግ ቀለል ያለውን የመምረጥ ዝንባሌ አለው፡፡ አንድ የጀመረውን ነገር ለማስተላለፍ ወይም ለማቆም ትንሽ “እንቅፋት” በቂ ነው፡፡

“አቶ ጊዜ አለኝ” የኑሮው መፈክር፣ “ስደርስ እደርስበታለሁ” ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በጊዜው ያልተከናወነ ተግባር ሊያደርስ የሚችለውን መዘዝም ሆነ ሊጎዳ የሚችለውን ሰው የማየት ብቃት የለውም፡፡ እንዲሁ በመላ-ምት ስለሚኖር ከራሱ አልፎ ቤተሰቡንም ሆነ መስሪያ ቤቱን የሚጎትት ታላቅ የስኬት ጠንቅ ነው፡፡

4. “ወ/ሪት ማሕበረሰብ”

“ወ/ሪት ማሕበረሰብ” የተወለደችው ከሰዎች ጋር ለመሰባሰብ እንደሆነ የሚያስመስልባት ማንነት አላት፡፡ የንግግር ችሎታዋና የመግባባት ፍጥነቷ አስገራሚ ነው፡፡ ከሰዎች ጋር ለመገናኘትና ለማሳለፍ ከምታገኘው አጋጣሚ አንዱም አያመልጣትም፡፡ የሚያስደንቀው ነገር ለማሕበራዊ ሕይወት በምታደርገው የዚህና የዚያ ሩጫ በፍጹም አለመድከሟ ነው፡፡ “ወ/ሪት ማሕበረሰብ” “ጓደኞቼ” ብላ የምትጠራቸው ሰዎች ቁጥር ስፍር የላቸውም፡፡ አብዛኛዎቹን በቀን ውስጥ በአካል ካላገኘቻቸው በስልክ ረዘም ላለ ጊዜ ታነጋግራቸዋለች፡፡ ለመስራት ያልፈለገችው ስራ ካለ ያንን ስራ የምታስተላልፈው ከሰዎች ጋር በመገናኘትና ይህና ያንን በማድረግ ነው፡፡

“ወ/ሪት ማሕበረሰብ” ከስራዋ አካባቢ በፍጹም ሰው አይጠፋም፡፡ ከአንድ ቦታ ወደሌላኛው፣ ወይም ደግሞ ከስራ ቦታ ወደቤቷ ስትሄድ በመንገድ ላይ ሰዎችን ቀጥሮ ሻይ መጠጣትም ሆነ መጨዋወት የተለመደ ተግባሯ ነው፡፡ የአንድን ስራ የቀን ገደብ ከሰዎች ጋር ለማሳለፍ ስትል ማስተላለፍ እንደ ችግር አይታያትም፡፡

ከላይ ከተዘረዘሩት ዝንባሌዎች መካከል ራስህን በየትኛው አገኘኸው? ካላገኘኸውስ ራስህን በምን አይነት ሁኔታ ያየኸው ይመስልሃል? ጊዜ አጠቃቀምህ ሙሉና ስኬታማ ነው ብለህ ታስባለህ?

ጊዜያችሁን በሚገባና በስኬታማነት ለመጠቀም የሚረዳችሁን “የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” የተሰኘው መጽሐፌን ማንበብ አትዘንጉ፡፡ በገበያ ላይ ታገኙታላችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
12.7K views02:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 05:01:17
ከሞት ያልተናነሰ ሕይወት!

• እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ድረስ የምንከተለው ዓላማ ሳይኖረን መኖር!

• ራሳችንን፣ ዓላማችንንና ስራችንን በማሻሻል ላይ ከማተኮር ይልቅ ስለሰዎች ስናስብና ስናወራ መኖር!

• ቢያንስ በአንድ ሰው ላይ መልካም ተጽእኖ ሳያሳድሩ መኖር!

• በየእለቱ ሳይለወጡ ሁልጊዜ በአንድ አይነት አመለካከት፣ ስፍራና ልምምድ እየረገጡ መኖር!

• መንቀሳቀስ እስከማንችን ድረስ በፍርሃት ታስሮ መኖር!

• በሰዎች ላይ ቂም ይዘን እነሱን ካልተበቀልን በስተቀር ውስጣችን አላርፍ እያለንና እየነደደ መኖር!

• አንድ ሰው ስለገፋንና ትቶን ስለሄደ ብቻ ነገን ማየት እስከማንችል ድረስ የወደቀ ስሜት ይዞ መኖር!

• እንደዚህ አይነት አነቃቂ መልእክት ከሰሙና ካነበቡ በኋላ ከመፈክር ባላለፈ ሁኔታ ለውጥን ሳናመጣ ራሳችንን እዚያው ነገር ላይ እያገኙ መኖር!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
13.4K views02:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 05:01:34 ተወርዋሪ ኮከቦች

ተወርዋሪ ኮከቦች (Shooting Stars) መቼ እንደመጡ ሳናውቃቸው በድንገት ከተከሰቱ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ በድንገት የሚሰወሩ ፍጥረቶች ናቸው፡፡ ዛሬ እዚህ ተከስተውና ታይተው ባለፉበት ፍጥነት ሌላ ቦታም እንደዚሁ፡፡

ልክ እንደተወርዋሪ ኮከብ ዛሬ እዚህ ነገ እዚያ የሚሉ ሰዎች በሕይወታችሁ ላይ የሚያመጡት ጉዳትና ክስረት በምንም አይተመንም፡፡ ይህ ክስረት እንዳይደርስባችሁ ከፈለጋችሁ ብቸኛውና ዋነኛው መንገድ ለሰዎች ጊዜን መስጠት ነው፡፡ የሰዎችን እውነተኛነትና “ቋሚ ኮከብነት” ከሚያሳዩ ነገሮች መካከል ዋነኛው መሳሪያ ጊዜ የሚባለው ነው፡፡

በድንገት በሕይወታችሁ ለተከሰቱ ሰዎቸ ጊዜ እንዲፈትናቸውና እውነተኛ የመነሻ ሃሳባችውንም ሆነ ማንነታቸውን ኩልል አድርጎ እንዲያወጣላች ከፈለጋቸሁ ለሁኔታው በቂ ጊዜን ስጡት፡፡

ጊዜ መስጠት ለሁለት ነገር ይጠቅማችኋል፡-

1. እውነተኛ ሰዎች ብቻ መቆየት የሚችሉበትን ሁኔታ በመፍጠር እውነተኛ ያልሆኑት እንዲያልፉ ያጣራላችኋል፡፡

2. በወቅቱ የስሜታችሁ ሁኔታ ተገፋፍታችሁና ተታላችሁ ውሳኔ ውስጥ እንዳትገቡ እናንተን ያረጋጋችኋል፡፡

ሰዎች “ቋሚ ኮከቦች” ይሁኑ ወይም “ተወርዋሪ ኮከቦች” ይሁኑ ለመለየት ጊዜ መስጠት ማለት የሚከተሉትንና መሰል ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ሳታጋሩ መቆየት ማለት ነው፡፡

የጊዜን ፈተና ላላለፈ ሰው በፍጹም . . .

1. ገንዘብና ንብረት (ቁሳቁስ) አታጋሩ

2. ከፍቅር ጋር የተያያዘ ስሜታችሁን አታጋሩ

3. የግል ምስጢራችሁን አታጋሩ

አንድ ጊዜ እነዚህንና መሰል የግል ሁኔታችሁን ካጋራችሁ በኋላ የሰዎቹ እውነተኛ ማንነት ሲገለጥና በመጡበት ፍጥነት ሲያልፉ፣ የልባችሁን ቁራጭ ቦጭቀው ይዘው ነው የሚሄዱት፡፡ ከዚያም፣ ያንን የተቦጨቀውን ልባችሁን ስታክሙና፣ ቡጫቂውን ይዘው የሄዱትን ሰዎች ስትፈልጉ እድሜያችሁን ታሳልፋላችሁ፡፡

ፈጣሪ የሰላም ሕይወት ይስጣችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
13.7K views02:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 04:59:59
ሕይወት! የመጀመሪያም የመጨረሻም እድል!

“ሕይወት የአንድ ጊዜ ብቻ አቅርቦት ነው። በደንብ ኑሩት” (Thoughts Wonder)

ዛሬ ለማድረግ ያልቻልናቸውን ነገሮች ነገ እስከምናደርጋቸው ጓጉተን በመቆይ ጊዜውና እድሉ ሲመቻች እናደርጋቸዋለን፡፡ ሕይወት ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ሕይወት ማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚሰጥ እድል ነው፡፡ አንዴ ካልተጠቀምንበት ደግሞ ተመልሶ አይመጣም፡፡

ይህንን የአንድ ጊዜ ብቻ እድል በተለያዩ ምክንያቶች ሳታጣጥሙትና ሳትኖሩት እንዳታልፉ ብልሆች ሁኑ፡፡

ይህንን ሕይወት በማጣጣም መለመኖር ሃብታም መሆን የለባችሁም፣ አዋቂ መሆን የለባችሁም፣ ዝነኛ መሆን የለባችሁም፣ ትቷችሁ የሄደውን ሰው ማስመለስ የለባችሁም፣ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ ማግኘት የለባችሁም፣ በሁሉም ሰው ተቀባይነት ማግኘት የለባችሁም፣ የትም ሃገር ሄዳችሁ መኖር የለባችሁም . . . ፡፡

ዛሬ ሕይወትን በማጣጣም ለመኖር መወሰን ትችላላችሁ፡፡

• ዛሬ ባላችሁ ነገር ተደሰቱ፣ የሌላችሁን ነገር ለማግኘት ግን ጠንክራችሁ ስሩ፡፡

• ባሏችሁ ወዳጆች ላይ በማተኮ ደስተኞች ሁኑ፣ የራቋችሁን ጓደኞች ደግሞ ለቀቅ ማድረግ ተማሩ፡፡

• በእጃችሁ ላይ ያለውን ስራ በደስተኛነትና በትጋት ስሩ፣ ነገር ግን ለተሻለ ነገ በማቀድ በዓላማ ኑሩ፡፡

• ማንነታችሁን በመቀበል ከራሳችሁ ጋር ደስተኞች ሁኑ፣ መለወጥና መሻሻል የሚገባውን የስብእና ሁኔታችሁ ላይ ግን ካለማቋረጥ ስሩ፡፡

• ግባችሁ እስከምትደርሱ ባላችሁ ጉዞ ተደሰቱ፣ ግባችሁ እስከምትደርሱ ግን እርምጃችሁን ቀጥሉ፡፡

የሰላምና የጤና ሕይወት ይሁንላችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
16.5K views01:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-31 19:02:42 ልጆቻችሁን በጥብቅ ተከታተሉ!

ለወላጆች . . .

የልጆቻችሁን ጥሩ መሆን፣ የፍቅር ልጆች መሆንና ታዛዥ መሆን በድብቅ ሊያደርጉትና ሊደረግባቸው ከሚችሉት ነገሮች ጋር በፍጹም አታምታቱ፡፡ በሌላ አገላለጽ ልጆቻችሁ ከላይ የተጠቀሱትንና መሰል መልካም ባህሪያት እየገለጹ ሳለ በስውር ግን አጥፊ ሁኔታ ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የሚከቱለትን ሃሳቦች እንደመንደርደሪያ በመውሰድ አስቡበት፡፡

ልጆቻችሁ ላይ መልካምነትን፣ ፍቅርንና ታዛዥነትን እያያችሁ . . .

1. መጥፎ ልማድ ሊያዳብሩ ይችላሉ፡፡

የፖርኖግራፊ፣ የአደንዛዥ እጽና የመሳሰሉት ነገሮችን እየተለማመዱ ከእናንተ ጋር ግን እንደቀድሞው “በጨዋነት”፣ “በፍቅርና” እና “በታዛዠነት” ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ ካለማቋረጥ የልጆችን ስልክ አጠቃቀም ተቆጣጠሩ፣ የባህሪይ ለውጥ ሲያሳዩ በሚገባ ተከታተሉ፣ ለብቻቸው መሆንን የመፈለግን ሁኔታ በቅርብ አጢኑ . . . ፡፡

2. በመጥፎ ጓደኛ ተጽእኖ ስር ሊወድቁ ይችላሉ፡፡

ቀስ በቀስ ባህሪያቸውን ለመጥፎ ከሚለውጡ ልጆች ጋር እያሳለፉ ከእናንተ ጋር ግን እንደቀድሞው “በጨዋነት”፣ “በፍቅርና” እና “በታዛዠነት” ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ ጓደኞቻቸው ማን እንደሆኑ ለይታችሁ እወቁ፣ አዲስ ጓደኛን ሲይዙ እንዲያሳውቋችሁ አድርጉ፣ ከጓደኞቻቸው የሚመጡ ግፊቶችን እንዲያሳውቋችሁ መንገድን ጥረጉ፣ አውሯቸው . . . ፡፡

3. የተለያዩ ጥቃቶች ከሰዎች ሊደርስባቸውና ላይነግሯችሁ ይችላሉ፡፡

በትምህርት ቤት ጉልበተኛ የአካል ጥቃት፣ በዘመድና በቅርብ ሰው የወሲብ-ነክ ጥቃት፣ በአስተማሪና በሌላ “ባለስልጣን” የስነ-ልቦና ጥቃትና የመሳሰሉትን እያስተናገዱ ለእናንተ ሳይነግሯችሁ ከእናንተ ጋር ግን እንደቀድሞው “በጨዋነት”፣ “በፍቅርና” እና “በታዛዠነት” ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ እቤት ከሰው ጋር ትታችሁ የምትወጡትን የልጆች ሁኔታ በሚገባ አስቡበት፣ ማንም ሰው ተገቢ ያልሆነ ቦታ ሲነኳቸውም ሆነ ተገቢ የሆነ ሃሳብ ሲያቀርላቸው በግልጽ መንገር እንዳባቸው አሳስቧቸው፡፡

በልጆቻችሁ ላይ የስነ-ልቦናም ሆነ የአካል ጥቃት አታድርሱ፡፡ መሰረታዊና አስፈላጊ ነገሮችንም በመከልከል አትጉዷቸው፡፡ ነገር ግን ተገቢ ያልሆነን ነገር እንዳያደርጉ በመከልከልና ተገቢውን ነገር እንዲያደርጉ በመጫን ብትጎዷቸው ጉዳቱ ጤናማና ለውጤት የሆነ ጉዳት እንደሆነ አስቡ፡፡

ትምህርት ቤት፣ ጓደኛም ሆነ ማሕበራዊ ሚዲያ በእነሱ ላይ ከሚያመጣው ተጽእኖ ይልቅ በበለጠ ሁኔታ እናንተ ተጽእኖን ማድረግ እንደሚገባችሁ አትዘንጉ፡፡ አለበለዚያ መቼ እንዳመለጧችሁ ሳታውቁ ታጧቸዋላችሁ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
15.1K views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ