2024-03-16 10:12:25
ጥያቄ፡-
ባለቤቴ ጋ ከተጋባን 7 አመታት ሆነን፤ አንድ ልጅ አለን፡፡ ልጅ የመውለድ ሀሳብ የለውም ባጠቃላይ አይፈልግም፡፡ አብሮኝም አይተኛም ከተጋባን 5 ወይም 6 ጊዜ ቢሆን ነው አብረን የተኛነው፡፡ ሌላ ጊዜስ እርግዝና ፈርቶ ነው ልበል፡፡ እርጉዝም ሆኜ ምንም የለም፡፡
1ኛ ጥያቄ፡- እግዚአብሄርን አሳዝነዋለው ብዬ ፈራለሁ፡፡ ብፈታው እግዚአብሔር ያዝናል?
2ኛ ልጄ ብቻውን ይቀርብኛል ወንድም እህት ሳይኖረው ብዬ ፈራለሁ ደግሞስ ማግባት ሳልችል ብቀር ከአባቱ ለይቼው ብዬ ፈራለሁ፡፡ እባክህን እርዳኝ ዶክተር
መልስ፡-
ከተጋባችሁ ሰባት ዓመት ሆኗችሁ ባለቤትሽ ከአንቺ ጋር ለመተኛት ወይም ወሲብ ለመፈጸም የፈለገው ስድስት ጊዜ ብቻ መሆኑ በምንም መስፈርት ጤናማ አይደለም፡፡
መልሴ ትንሽ ሙሉ እንዲሆን አንዳንድ ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይኖብኛል፡፡ ለምሳሌ ከጋብቻ በፊት በፍቅር ግንኙነት ያሳለፋችሁት ጊዜና በዚያን ጊዜ የነበራችሁ የግንኙነት ጥልቀት እዚህ ጋር ትልቅ ትርጉም ይሰጣል፡፡
ያም ሆነ ይህ ትንሽ መላ ምቶችን መሰንዘር እንችላለን . . .
1. አንዳንድ ወንዶች ስንፈተ-ወሲብ (Sexual Incompetence) ካለባቸው ወሲብ ለማድረግ መነሳሳት ወይም ከተነሳሱ በኋላ እንደዚያ ለማቆየት አለመቻላቸው በጣም ያሳፍራቸዋል ወይም ሞራላቸውን ይነካዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ወሲብ ማድረግ እየፈለጉም ከዚያ ይሸሻሉ፡፡ ይህንን ሁኔታ ለማወቅ ከፈለግሽ ከዘህ በፊት ወሲብ በፈጸማችሁበት ጊዜ የነበረውን ሁኔታ በማጤን መለየት ትችያለሽ፡፡
ለምሳሌ በወሲብ ጊዜ አለመነሳሳት፣ ከተነሳሳ በኋላ አለመቆየት ወይም ደግሞ ይህ ሁኔታ እንዳይታወቅበትና መሳሳቱ ሳይበርድ ተጣድፎ መጨረስና የመሳሰሉት፡፡
2. አንዳንድ ወንዶች ወሲብ-ነክ ምስሎችና (Pornography) የማየት ድብቅ ሱስ ይኖርባቸውና ይህ ሲስ ከትዳር አጋራቸው ጋር ያላቸው የወሲብ ፍላጊትና ሂደት ያዛባበቸዋል፡፡ ይህንን ለማወቅ የማሕበራ ሚዲያ ልማዱን መከታተል፣ ስልኩ ወይም ኮምፒውተሩ ውስጥ በመግባት የተመለከታቸውን ገጾች ማየትና የመሳሰሉትን ሁኔታዎች መሞከር ይቻላል፡፡
3. አንዳንድ ወንዶች ካለምንም የመሳብ ሁኔታና ፍቅር (Sexual attraction) ወደ ትዳር ይገቡና ለዚያ ነገር ምንም መነሳሳቱ አይኖራቸውም፡፡ ይህንን ለመለየት፣ ከአንቺ ጋር ለማሳለፍ የመፈለጉን ሁኔታ፣ ምንም እንኳን ከአንቺ ጋር ወሲብ ባይፈጽምም ከዚያ ውጪ የሆነ አካላዊ ቅርርብ የመኖሩን ሁኔታ፣ ከመጋባታችሁ በፊት ከነበረው የተቃራኒ ጾታ ግንኙነት ጋር አሁን ያለው ንክኪ ካለ ማጤንን ይጠይቃል፡፡
እነዚህን ሃሳቦች የማጤኑ ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለፍቺ ከመቸኮልሽ በፊት ስሜትሽን በግልጽ መናገርና ውይይትን መፍጠርን የመሰለ ነገር የለም፡፡
በነገራችን ላይ የትዳር ትርጉምንና ዓላማን አስመልክቶ ዋና ዋና ቦታዎች ካላቸው ነገሮች መካከል የወሲብ ግንኑነት ይገኝበታል፡፡ ወሲብ አንድነታችሁን ያጠናክራል፣ ፍቅራችሁንና መሳሳባችሁን ለመግለጽ ይጠቅማል፣ እርካታን ይሰጣል፣ ቤተሰብን ለመመስረት መንገድ ያመቻቻል . . . ፡፡ ወሲብ የጎደለው ትዳር ጤናማነቱ አጠራጣሪ ስለሆነና አንቺን በጣም ሊጎዳሽ ስለሚችል በነገሩ በከባዱ ማሰብሽና መረበሽሽ ትክክለኛ ስሜት ነው፡፡
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
12.6K views07:12