2024-03-21 04:59:59
ሚዛን ያልጠበቀ የአንድዮሽ ግንኙነት ምልክቶች (By Sara Kubburic)
ማንኛውም ግንኙነት ትክክለኛና ሚዛናዊ እንዲሆን ሁለትዮሽ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህም ማለት የሁለትን ሰዎች የጋራ መቀራረብ፣ መሰጠትና ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በሁሉ ነገር የሚጦዘው አንደኛው ወገን ብቻ ሲሆን የሆነ የተዛባ ነገር እንዳለ ጠቋሚ ነው፡፡
1. በስልክ፣ በአካልም ሆነ በቻት እናንተ ካላናገራችኋቸው እነሱ ንግግርን የማያነሳሱ ሰዎች . . .
2. አብሮ የማሳለፍን ጥያቄ እናንተ ካልጠየቃችሁና ካላነሳሳችሁ እነሱ በፍጹም ፍላጎት የማያሳዩና የማያነሳሳ ሰዎች . . .
3. አለመግባባት ሲፈጠር እናንተ ብቻ ይቅርታ ካልጠየቃችሁ ጥፋታቸው ሆኖ እንኳን በፍጹም ይቅርታ የማይጠይቁ ሰዎች . . .
4. ለሁሉም ሁኔታ መስዋእትነት ከፋዮች እናንተ እንድትሆኑ የሚጠብቁ ሰዎች . . .
5. ለግንኙነቱ ጤናማነት ሲባል መስዋእትነትን እናንተ ብቻ እየከፈላችሁ እነሱ ግን የማይከፍሉ ሰዎች . . .
6. እጅግ በጣም አስቸጋሪ የሆነውን ባህሪያቸውን ዝም ብላችሁ እንድትሸከሙ የሚፈልጉ ሰዎች . . .
7. ሆን ብለው በማንኛውም ጊዜ ትተዋችሁ ሊሄዱ እንደሚችሉ አይነት ስሜትን የሚሰጧችሁና ሰዎች . . .
8. የእናንተ ፍላጎትና ዓላማ ሙሉ በሙሉ በእነሱ ፍላጎትና ዓላማ ስር እንዲጠቃለል የሚፈልጉ ሰዎች . . .
9. ሁሉንም ነገር (ስራ፣ ጓደኛ፣ መዝናናት …) ከእናንተ የሚያስቀድሙ ሰዎች . . .
10. እናንተ እቅዳችሁን ከእነሱ አንጻር ስታወጡ እነሱ ግን ከራሳቸው አንጻር ብቻ የሚያወጡ ሰዎች፡፡
ሚዛኑ ይጠበቅ!
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
12.6K views01:59