Get Mystery Box with random crypto!

እውነተኞቹን ከአስመሳዮቹ መለየት ከፈለጋችሁ ምናልባት በዙሪያችሁ ከሚገኙ ሰዎች መካከል እውነተኞቹ | Dr. Eyob Mamo

እውነተኞቹን ከአስመሳዮቹ መለየት ከፈለጋችሁ

ምናልባት በዙሪያችሁ ከሚገኙ ሰዎች መካከል እውነተኞቹንና አስመሳዮቹን ለመለየት ከፈለጋችሁ እናንተ ሁለት ነገር ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡

1. እውነተኛ ማንነታችሁን መኖር

አስመሳይ ማንነት አስመሳይ ሰዎችን ይስባል፤ እውተኛ ማንነት እውነተኛ ሰዎችን ይስባል፡፡ ይህ የማይለወጥ ማሕበራዊ ሕግ ነው፡፡ እውነተኛ ሆናችሁ ስትኖሩ፣ እውነትን ስትናገሩ፣ እውነታን ስትጋፈጡ . . . እውነተኞችና እውነት ወዳዶች ብቻ ወደ እናንት ይሳባሉ፣ ሌሎቹ ግን ስማይመቻቸው ይርቃሉ፡፡

2. ትክክለኛ የሕይወት ዓላማችሁን መከተል

ያያችሁትን፣ የሰማችሁትንና ለጊዜው “ያበላል” ብላችሁ የምታስቡትን ነገሮች የምትከታተሉ አይነት ሰዎች ከሆናችሁ፣ ይህ የተዛባ ሂደት የተዛባ መርህና አመለካከት ያላቸውን አይነት ሰዎች ወደ እናንተ ይስባል፡፡

ሲጨመቅ፣ በዙሪያችን የሚመጡትንና የሚቆዩትን ሰዎች የሚወስኑ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ማንነታችን እና ዓላማችን ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች መስመር ሲይዙ “የወዳጆቻችን” ነገርም ከዚያው ጋር ይስተካከላል፡፡
የሕይወት ዘይቤያችሁ ወደ እናንተ የሚመጡትንና የሚቆዩትን ሰዎች የመወሰን ጉልበት አለው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/