Get Mystery Box with random crypto!

Dr. Eyob Mamo

የሰርጥ አድራሻ: @dreyob
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 67.99K
የሰርጥ መግለጫ

Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-16 05:00:00
ያለፈው ታሪክ ጉዳይ!

“ያለፈውን ታሪክ ያላወቁ ሰዎች ያንንው ታሪክ ከመድገም ውጪ ሌላ ምንም ምርጫ የላቸውም” – Unknown Source

የቤተሰቦቻችሁን ያለፈ ታሪክ በሚገባ አጥኑና ከእሱ ተማሩ! መልካሙንና የተሳካውን አሻሽሉት፡፡ ጤና-ቢሱንና ያልተሳካውን አትድገሙት!

የመሪዎቻችሁን (የሃገር፣ የሕብረተሰብ፣ የኃይማኖት . . . ) ያለፈ ታሪክ በሚገባ አጥኑና ከእሱ ተማሩ! መልካሙንና የተሳካውን አሻሽሉት፡፡ ጤና-ቢሱንና ያልተሳካውን አትድገሙት!

እናንተ ዛሬ የምትከተሉትን ዓላማ (ስራ፣ ንግድ፣ ራእይ . . . ) ከዚህ በፊት ያራመዱ ሰዎችን ያለፈ ታሪክ በሚገባ አጥኑና ከእሱ ተማሩ! መልካሙንና የተሳካውን አሻሽሉት፡፡ ጤና-ቢሱንና ያልተሳካውን አትድገሙት!

ከዚህ በፊት ሞክራችሁት አልሄድ ያለውንና አሁንም እንደገና ለማሳካት የምትታገሉትን ሁኔታ ያለፈ ታሪክ በሚገባ አጥኑና ከእራሳችሁ ጉዞ ተማሩ! መልካሙንና የተሳካውን አሻሽሉት፡፡ ጤና-ቢሱንና ያልተሳካውን አትድገሙ!

ከትናንት ውጪ ዛሬ የለም! ከዛሬ ውጪ ነገ አይኖርም!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
13.7K views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 05:01:11 ዝንባሌያችንን የማወቅ አስፈላጊነት

የስነ-ልቦና አዋቂዎች እንደሚነግሩን፣ ሰዎች የሚያልፉባቸው ጤና ቢስ ልምምዶች በነገው ማንነታቸው ላይ ታላቅ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ አለው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ካሳለፉት ልምምድ የተነሳ በመዛል ማንም እንዳሻው የሚያደርጋቸው “አጥር” የለሽ ሰው ይሆናሉ:: ሌሎች ደግሞ በተቃራኒው ማንም እንደገና “እንዳይደፍራቸው” እና እንዳይነካቸው የተለያዩ “አጥሮችን” በዙሪያቸው ይሰራሉ፡፡ በእንደዚህ ሁኔታ ባለፈው ታሪካቸውና ልምምዳቸው ተጽእኖ ስር የወደቁ ሰዎችን በአራት ልንከፍላቸው እንችላለን፡፡

እነዚህ ዝንባሌዎች በአመራርም ሆነ በማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነታችን ተግባራዊነታቸው አይለወጥም::

1. ለሁሉም ነገር ተስማሚዎች (Compliants)

እንዲህ አይነት መሪዎች ሌሎች የግል ሕይወታቸውን መስመር ረግጠው እንዲያልፉና እደፈለጉ እንዲያደርጓቸው የሚፈቅዱ ሰዎች ናቸው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እንደዚህ የሚሆኑት የሰውን ስሜት የመጉዳት ፍርሃት ስላለባቸው ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች እምቢታ ከአንደበታቸው አይወጣም፡፡ መብታቸውን ካለአግባብ የሚጋፋና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር እንኳ ቢሆን ለሰው ስሜት ለመጠንቀቅ ሲሉ ብቻ ያደርጉታል፡፡ ሰዎች ትተውን ይሄዳሉ ብለው ስለሚፈሩ መዘጋት ያለበትን የስሜት በራቸውን ይከፍታሉ፣ ሰዎች ሰተት ብለው ስለገቡ ደግሞ ተጎዳሁ ብለው ሲወቅሱ ይታያሉ፡፡

2. ገለልተኞች (Avoidants)

እንዲህ አይነት መሪዎች ለሰዎች ክፍት መሆን በሚገባቸው ጊዜና ሁኔታ የማንነት በራቸውን ጥርቅም አድርገው የሚዘጉ ናቸው፡፡ እንደዚህ አይነት መሪዎች ግፊት ያለበት ሁኔታ ሲከሰት ከመቋቋም ይልቅ ዘወር ማለት ይቀናቸዋል፡፡ የቀድሞ የአስተዳደግ ሁኔታ ወይም የኑሮ ልምምድ ካመጣው ተጽእኖ የተነሳ ደግመው ላለመጎዳት ራሳቸውን ዝግ የማድረግ ዝንባሌ አላቸው፡፡ እንዲህ አይነት መሪዎችን ለመርዳት እጅግ አስቸጋሪ ነው፣ ምክንያቱም ያለባቸው ዝግ የመሆን ዝንባሌ ለመርዳት የሚቀርቧቸውንም ሰዎች ጭምር ስለሚያርቅ ነው፡፡

3. ተቆጣጣሪዎች (Controllers)

እንዲህ አይነት መሪዎች የሌሎችን መስመር የማያከብሩና በሰዎች ስሜት፣ ሕይወት፣ ውሳኔና አመለካከት ላይ የሚረማመዱ መሪዎች ናቸው፡፡ ሰው ሊጣስበት የማይገባው መስመር እንዳለው የማያውቁ አይነት ተቆጣጣሪ መሪዎች ናቸው፡፡ ተቆጣጣሪዎች በሁለት ይከፈላሉ፡- “ጉልበተኞች” (aggressive) እና “ለስላሶች” (passive)፡፡

ጉልበተኛ ተቆጣጣሪዎች ኃይልን በመጠቀም መግባት የሌለባቸው ቦታና ሁኔታ ላይ ጥልቅ የሚሉ፣ እንደዚያ የማድረግም መብት እንዳላቸው የሚያስቡና የሚቆጣጠሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ለስላሳ ተቆጣጣሪዎች የጥፋተኝነት ስሜትን በመስጠትና በማታለል ሰዎቹ አንድን ማድረግ የማይፈልጉትን ነገር እንዲያደርጉ የሚገፋፉና በምርጫቸው እንዳደረጉት ስሜትን የሚያሳድሩባቸው አይነት መሪዎች ናቸው፡፡

4. ስሜት የለሾች (Non-responsives)

እንዲህ አይነት መሪዎች ለሰዎች ችግር፣ ጥያቄና ፍላጎት ምላሽን በመንፈግ አጥርን በዙሪያቸው የሚያበጁ ሰዎች ናቸው፡፡ ከማህበሩ ጋር እጅግ የተራራቁና በቀላሉ የማይገኙ ከመሆናቸውም በላይ ምንም አይነት ሁኔታ ቢከሰት ስሜት የማይሰጣቸውና ለመፍትሄ ራሳቸውን የማያቀርቡ አይነት ሰዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ አይነት መሪዎች አንዳንድ ጊዜ በዙሪያቸው በጣም ለህዝቡ የሚጠነቀቁ ሌሎች መሪዎች ከከበቧቸው ይህ ዝንባሌአቸው ብዙም ሳይታወቅ ለተወሰነ ጊዜ ሊጓዙ ቢችሉም የኋላ ኋላ ግን አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡

እንግዲህ አንድ መሪ ራሱን በሚገባ በማወቅና ድካሙንና ብርታቱን በመገንዘብ ወደስኬታማ ጎዳና የሚገባበትን መንገድ መጥረግ ይጠበቅበታል፡፡ አንድ መሪ ራሱን በሚገባ በማያውቅበት ጊዜ ከሚከተሉት ሁለት ችግሮች ለአንዱ ሊጋለጥ ይችላል፡፡

ራሱን በማወቅ በሚገባ ያልበሰለ መሪ በሰዎች ሃሳብ በቀላሉ የሚነዳና ራሱ አቋም የሌለው ሰው ነው፤ እንደመጣው ሰውና እንደተነገረው ሃሳብ አቋሙን ይለዋውጣል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ አንድ መሪ ራሱን በሚገባ በማያውቅበት ጊዜ ስለ ሰዎች ፍላጎት ግድ የለሽ ወደ መሆንም ሊያዘነብል ይችላል፡፡ ራሱን በማወቅ ስላልተደላደለ የሚችለውን መንገድ ሁሉ ተጠቅሞ ራሱን በማግነን ከፍ አድርጎ ለማሳየት ይታገላል፡፡

(አመራር A to Z ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ፡)

መጽሐፉ በአሁን ጊዜ በመደብሮች ሁሉ ይገኛል፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
16.2K viewsedited  02:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 04:59:01
ዝንባሌያችንን የማወቅ አስፈላጊነት
13.7K views01:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 07:46:10

17.1K views04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 06:06:10
እንኳን አደራችሁ የሃገሬ ሰዎች!

“መሆን ትፈልጉ የነበረውን ነገር ለመሆንና ማድረግ ትፈልጉ የነበረውን ነገር ለማድረግ በፍጹም ጊዜው አላለፈም”

ተነሱ! . . . ጸሎት አድርጉ! . . . አቅዱ! . . .ተንቀሳቀሱ!

በርቱ!


https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
13.8K views03:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 05:00:00
እውነተኞቹን ከአስመሳዮቹ መለየት ከፈለጋችሁ

ምናልባት በዙሪያችሁ ከሚገኙ ሰዎች መካከል እውነተኞቹንና አስመሳዮቹን ለመለየት ከፈለጋችሁ እናንተ ሁለት ነገር ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡

1. እውነተኛ ማንነታችሁን መኖር

አስመሳይ ማንነት አስመሳይ ሰዎችን ይስባል፤ እውተኛ ማንነት እውነተኛ ሰዎችን ይስባል፡፡ ይህ የማይለወጥ ማሕበራዊ ሕግ ነው፡፡ እውነተኛ ሆናችሁ ስትኖሩ፣ እውነትን ስትናገሩ፣ እውነታን ስትጋፈጡ . . . እውነተኞችና እውነት ወዳዶች ብቻ ወደ እናንት ይሳባሉ፣ ሌሎቹ ግን ስማይመቻቸው ይርቃሉ፡፡

2. ትክክለኛ የሕይወት ዓላማችሁን መከተል

ያያችሁትን፣ የሰማችሁትንና ለጊዜው “ያበላል” ብላችሁ የምታስቡትን ነገሮች የምትከታተሉ አይነት ሰዎች ከሆናችሁ፣ ይህ የተዛባ ሂደት የተዛባ መርህና አመለካከት ያላቸውን አይነት ሰዎች ወደ እናንተ ይስባል፡፡

ሲጨመቅ፣ በዙሪያችን የሚመጡትንና የሚቆዩትን ሰዎች የሚወስኑ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ማንነታችን እና ዓላማችን ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች መስመር ሲይዙ “የወዳጆቻችን” ነገርም ከዚያው ጋር ይስተካከላል፡፡
የሕይወት ዘይቤያችሁ ወደ እናንተ የሚመጡትንና የሚቆዩትን ሰዎች የመወሰን ጉልበት አለው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
16.8K views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 12:34:24 “በሕይወታችን ከሚደርሱብን ነገሮች ይልቅ ገና ለገና ይደርሱብናል በማለት የምናሰላስላቸው ሃሳቦች ለበለጠ ስቃይና ክስረት ይዳርጉናል” (Unknown Source)

የሃሳቡን ጡዘት ረገብ እናድርገው!!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
12.9K viewsedited  09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 05:00:00 ወርቅ፣ ብርና ነሃስ!

አንዳንድ የስነ-ልቦና ጥናቶችን አገላለጽ ወደ እኛ ቋንቋ ስንመልሳቸው ቢያታግለንም ለትርጉሙ ቀረብ በሚል አገላለጽ ስንገልጻቸው፣ “ከእውነታው ወደላይ የወጣ አመለካከት” (Upward counter factual thinking) እና “ከእውነታው ወደታች የወረደ አመለካከት” (Downward counter factual thinking) የሚባሉ ሁለት አመለካከቶች አሉ፡፡ ይህንን ሃሳብ ለማብራራት በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2020 ዓ/ም የተደረገ አንድ ጥናት፣ “በኦሎምፒክ ውድድር ወቅት አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሽልማትን ከተረከበው ሰው ቀጥሎ ደስተኛው ተሸላሚ ማን ነው? ሁለተኛው የወጣው የብር ተሸላሚ ነው? ወይስ ሶስተኛ የወጣው የነሃስ ተሸላሚ?” ለሚለው ጥያቄ መልስን ይሰጣል፡፡

በጥናቱ ውጤት መሰረት ሁለተኛ በመውጣት ብር ከሚሸለሙ ተወዳዳሪዎች ይልቅ ሶስተኛ በመውጣት ነሃስ የሚሸለሙ ተወዳዳሪዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ካለን ራሳችንን ከግባችን አንጻር ሳይሆን ከሌላው ሰው አንጻር የመመልከት ዝንባሌ የተነሳ ነው፡፡

ጥናቱ እንደሚነግረን፣ ሁለተኛ የሚወጡ ሰዎች ከእውነታው ወደላይ በመመልከት (Upward counter factual thinking) አንደኛ ከወጣው ሰው ጋር ራሳቸውን በማነጻጸር፣ “አንደኛ ብወጣ ኖሮ” የሚልን የጸጸት ስሜት ያስተናግዳሉ፡፡ ምንም እንኳን ከአንድ ሰው በስተቀር ሁሉንም የቀደሙ ቢሆንም “ያጡት” ላይ በማተኮር ያዝናሉ፡፡

በተቃራኒ፣ ሶስተኛ የወጡት ሰዎች ከእውነታው ወደታች በመመልከት (Downward counter factual thinking) ምንም ሽልማት ካላገኙት ሰዎች ጋር ራሳቸውን በማነጻጸር፣ “ሶስተኛ ባልወጣ ኖሮ” የሚልን “የእንኳን አልሆነብኝ” ስሜት ያስተናግዳሉ፡፡ ምንም እንኳን በሁለት ሰዎች ቢቀደሙም ሁኔታው ከዚህ የከፋ ሊሆን እንደሚችል በማሰብ “ያገኙት” ላይ በማተኮር ይደሰታሉ፡፡

በማንኛውም የሕይወታችን ስምሪትና ጥረት ውስጥ ለትንሽ ያመለጠንን ጥሩ “ውጤት” ለነገ ትምህርት፣ ለትንሽ ያመለጥነውን መጥፎ “ውጤት” ደግሞ ፈጣሪን ለማመስገንና ለደስተኛነት ብንጠቀምበት ጥሩ የስነ-ልቦና ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን እንደምናገኘው ጥርጥር የለውም፡፡

በትጋት ከሰራች በኋላ ያመለጣችሁ ነገር ላይ ሳይሆን በልፋታችሁ ያገኛችሁት ውጤት ላይ አተኩሩ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
14.0K views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 16:39:11
አንዳንዴ አረፍ በሉ!

በፈለጓችሁ ጊዜ ሁሉ ጊዜያችሁን፣ በቸገራቸው ጊዜ ሁሉ ገንዘባችሁን፣ ስሜታቸው ወረድ ባለ ጊዜ ሁሉ ትኩረታችሁን፣ ባጠፏችሁ ጊዜ ሁሉ ይቅርታችሁን፣ ባስቸገሩ ጊዜ ሁሉ ትእግስታችሁን . . . ካለምንም መከልከል የምታፈሱላቸው ሰዎች ያንን ባደረጋችሁ መጠን የማይገነዘቧችሁ ከሆነ፣ ከምንም የማይቆጥሩት ከሆነ፣ ግዴታችሁ እንደሆነ የሚያስቡ ከሆነ፣ ሆን ብለው የሚጎዷችሁ ከሆነና እነዚህ መሰል ግድ-የለሽ ስሜቶች የሚሳዩ ከሆነ ያንን ሁሉ ታግሳችሁ ተጨማሪ አመታቶችን መቆየት ከቻላችሁ ግፉበት፣ ፈጣሪም ጸጋውን ይስጣችሁ፡፡

ምናልባት ግን አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ትምህርትን የሚያገኙት እናንተ ወጥራችሁ የያዛችሁትን ለእነሱና ለእነሱ ብቻ የመኖር የውዴታ ግዴታችሁን ለቀቅ አድርጋችሁ ለራሳችሁ ጤንነት ለመስራት አረፍ ስትሉ እንሆነ ላስታውሳችሁ፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሚማሩት እናንተ ለእነሱና ለእነሱ ብቻ ከመኖር ትንሽ አረፍ ስትሉ ብቻ ነው፡፡

በቃ እንደዛ ነው!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
12.7K views13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 05:06:44 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን፣

እንኳን ለየኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ።

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
14.2K views02:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ