Get Mystery Box with random crypto!

Dr. Eyob Mamo

የሰርጥ አድራሻ: @dreyob
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.56K
የሰርጥ መግለጫ

Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-23 05:01:26 ልቆ የመገኘት ምርጫ

(“ምርጫና ውሳኔ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

አንደኛው ምርጫህ ለማድረግ የተጠየከውንና የሚጠበቅብህን ብቻ በማድረግ መወሰን ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ከሚጠበቅብህና ከሚገባህ በላይ በማከናወን ልቆ መገኘት ነው፡፡

አንድ ሁለት ልጆች የነበሩት ገበሬ ነበረ፡፡ ሁለቱ ልጆቹ በእርሻ ስራው አይለዩትም ነበር፡፡ አባት ለታናሹ ልጁ የበለጠ ሃላፊነት ስለሚሰጠውና ስለሚያምነው ሁል ጊዜ ታላቅየው ጥያቄ ይፈጥርበት ነበር፡፡ አንድ ቀን አባት አምስት መቶ ብር በእጁ ላይ እንዳለውና፣ አምስት በጎችን እጁ ላይ ባለው የገንዘብ መጠን ቢያገኝ የመግዛት እቅድ እንዳለው ለታላቅ ልጁ እየነገረው ሳለ፣ ታላቅ ልጅ ይንን አጋጣሚ በመጠቀም ለምን ከእርሱ ይልቅ ለታናሹ የበለጠ ሃላፊነትን እንደሚሰጠው ጠየቀው፡፡ ይህንን ሲወያዩ ታናሽ ልጅ በዚያ አልነበረም፡፡ አባትም ቀጥተኛ መልስ ቢሰጠው ይገነዘበዋል ብሎ ስላላሰበ በብልሃት ሊያስተምረው ፈለገ፡፡

አባት ለታላቅ ልጁ፣ “እሰቲ እነዚያ ከብት የሚያረቡት ሰዎች ቤት ሂድና በግ ይሸጡ እንደሆነ አጣርተህ ተመለስ፣ ከዚያም ጥያቄህን እመልስልሃለሁ” አለው፡፡

ታላቅ ልጅ ሄዶ ተመለሰና፣ “አዎን የሚሸጡ በጎች አሏቸው” አለ፡፡

አባትም፣ “ሂድና ዋጋቸው ስንት እንደሆነ ጠይቅ” አለው፡፡

ልጅም ሄዶ መጣና፣ “ባለ 100 ብር በጎች አላቸው” አለው፡፡

አባት እንደገና፣ “ሂድና ነገውኑ በጎቹን ብንገዛቸው እኛ ድረስ ሊያመጡልን እንደሚችሉ ጠይቅ” አለው፡፡
ልጅም ሄዶ መጣና፣ “አዎን ይችላሉ” አለው፡፡

አባትም ታናሽ ወንድምህን ጥራው እስቲ አለው፡፡ ታናሽ ልጅ ሲመጣ አባት፣ “እስቲ እነዚያ ከብት የሚያረቡት ሰዎች ቤት ሂድና በግ ይሸጡ እንደሆነ አጣርተህ ተመለስ” አለው፡፡

ታናሽየው ሄዶ ተመለሰና፣ “ባለ 100 ብር፣ ጎችና እና ባለ 150 ብር በጎች አሏቸው፡፡ ነገውኑ ብንፈልግ ሊያመጡልን እንደሚችሉ ጠይቄ ተስማምተዋል” ብሎ ለአባቱ ነገረው፡፡ በመጨመርም፣ “ስለዚህ፣ የተለየ ሃሳብ ኖሮን ካልነገርኳቸው በስተቀር አምስት በጎችን በ100 ብር ሂሳብ ነገውኑ እንዲያመጡልን ተስማምቼአለሁ” አለው፡፡

አባት ወደታላቅ ልጁ ዘወር ብሎ ሲመለከት፣ ታላቅ ልጁ የራሱንና የታናሽ ወንድሙን መልስ በማሰነጻጸር ላይ እንዳለ ያስታውቅ ነበር፡፡

“አየህ ልጄ፣ አንተንና ታናሽ ወንድምህን የጠየኳችሁ አንድ አይነት ጥያቄ ነው፡፡ ያመጣችሁልኝ መረጃ ግን በጣም ይለያያል፡፡ አንተ ያችኑው የተጠየከውን ጥያቄ ነው ይዘህ የመጣኸው፡፡ ሌላ መረጃ ስፈልግ እንደገና ደጋግሜ መላክ ነበረብኝ፡፡ እርሱ ግን እኔ የፈለኩትን ፍላጎቴን በሚገባ በመረዳት የቻለውን ያህል መረጃ ይዞልኝ ነው የመጣው፣ ከተጠየቀውም በላይ ስራ ሰርቶ ነው የመጣው፡፡ ሁል ጊዜ ከአንተ ይልቅ ለእርሱ ሃላፊነትን የምሰጠው ለዚህ ነው፡፡” በማለት ቀድሞ ለጠየቀው ጥያቄ መልስን ሰጠው፡፡ ለነገሩ፣ ታላቅ ልጅ ገና መልሱ ሳይብራራ ገብቶት ነበር፡፡

የተባሉትንና የሚጠበቅባቸውን ብቻ አድርገው እጆቻቸውን የሚሰበስቡ ሰዎች ተግባርን በማከናወንና የተጠበቀባቸውን ነገር በማድረግ አንጻር ትክክለኛ ነገር አድርገዋል፡፡ በእድገት ልቆ ከመገኘት አንጻር ሲታይ ግን ባሉበት የሚረግጡ አይነት ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ አይነቱ ምርጫ ሰዎች ሊያከናውኑ ከሚችሉት አቅማቸው በታች እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች በእድገትና በተቀባይነት አልፈዋቸው ሲሆዱ እያዩ “ለምን?” እያሉ ከመጠየቅ ያለፈ እድገት አይኖራቸውም፡፡ “ለምን ለሌሎች ያደላሉ? … ለምን ሰውን ይመርጣሉ? …”

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
14.2K views02:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 04:59:01
ልቆ የመገኘት ምርጫ
12.7K views01:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 21:34:21
አዲስ መጽሐፍ! በቅርብ ቀን ይጠብቁ!

“የልጆች አስተዳደግ”
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ልጆችን የማሳደጊያ ስኬታማ መመሪያዎች!

ከመጽሐፉ መግቢያ የተወሰደ

ትናንትና የነበረ እድል ዛሬ ያለመኖሩን ያህል ትናንትና የነበሩ ችግሮችም መልካቸውን ለውጠው ብቅ ይላሉ፡፡ ይህ እውነታ በልጆችም ሕይወት መንጸባረቁ የማይካድ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ልጆች የሚያጋጥማቸው እድሎች፣ ምርጫዎችና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ከመቸውም በበለጠ ሁኔታ ለወላጆች የቤት ስራ ሆኗል፡፡ ይህ የልጆች አስቸጋሪ ሁኔታ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የወላጆች ሸክም መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

ወላጆች የልጆቸውን የወደፊት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ በእነሱ እጅ እንደሆነ አምነው መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡

ልጆችን አስመልክቶ በአንድ ሃገር ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ተቋም ሊሰራው የማይችለውን ስራ የመስራት አቅሙም፣ እድሉም ሆነ ሃላፊነቱ ያለው በወላጆች ላይ ነው፡፡

በዚህች አነስተኛ መጽሐፍ ውስጥ ወላጆች በልጆቻቸውን ሁለንተናዊ እድገት ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ የመልካም ተጽእኖ ተሳትፎ በስፋት እንመለከታለን፡፡

የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ በልጆች አስተዳደግ ሂደት ላይ ወላጆች ሊያስቡባቸውና ራሳቸውን ሊሰለጥኑባቸው የሚገባቸውን ዋና ዋና ሃሳቦች መጠቆምና መሰረታዊ ግንዛቤን ማስጨበጥ ነው፡፡

የመጽሐፉ አወቃቀር

ክፍል አንድ - ልጅ የመውለድ ጉዳይ

ክፍል ሁለት - ልጆችን መቆጣጠር እና ማሳደግ

ክፍል ሶስት - ልጆችን ማወቅ እና መቀበል

ክፍል አራት - ልጆች የሚማሩባቸው መስኮች

ክፍል አምስት - ልጆችን ማስተማር የሌለብን ነገሮች

ክፍል ስድስት - የልጆችን ብልህነት መለየትና መደገፍ

ክፍል ሰባት - ልጆችን ከመገፋት መጠበቅ

ማጠቃለያ - የልጆችን ለውጥ መከታተል!
12.8K viewsedited  18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-22 05:00:47
ጠንካራው መልእክት!

“በሚጮህ ድምጽና በጠንካራ ድምጽ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ” (ካልታወቀ ምንጭ)

የሚጮህ ሁሉ ጠንካራ አይደለም፤ ጠንካራ ሁሉ አይጮህም!

ተገቢ ያልሆነን ነገር ለሚያደርግባችሁ ሰው የክልከላ መልእክትን ለማስተላለፍ የግድ መጮህ የለባችሁም፡፡ መልእክታችሁ ግን ጠንካራ መሆን አለበት፡፡ በሌላ አገላለጽ ጩኸት የጥንካሬ ምልክት አይደለም፡፡ እንዲያውም ሁል ጊዜ እየጮህን ስሜታችን ሲረግብ አሁንም ለሁኔታው ተጋላጭ ሆነን ራሳችንን የምናቀርብ ከሆነ ጩኸታችን የመልእክታችንን ደካማነት ነው የሚያሳየው፡፡

ይህንን ለማረም ከፈለግን ሳንጮህ ጠንካራ መልእክትን ማስተላለፍ እንችላለን፡፡ እንዴት? . . .

1. በትንሹም በትልቁም ስሜታዊ ባለመሆን አንዳንድ ነገሮችን ታግሶ ማለፍ፡፡

2. ሰዎች የአካል፣ የስሜትና የስነ-ልቦና ጤንነታችንን አደጋ ላይ የሚጥልን ሁኔታ ሲያደርጉ ስሜታችንን በግልጽ ማሳወቅ፡፡

3. በተግባር የማንደግፋቸውንና የማናሳያቸውን ስሜታዊነቶች በቃልና በአንደበት ከመናገር መቆጠብ፡፡

4. በጨዋ ንግግራችን እና በተረጋጋ ስሜት የገለጽናቸውን አቋሞቻችንን በጠንካራ ተግባር ማሳየት፡፡

5. ከሰዎቹ ዘላቂ የሆነንና በተግባር የሚታይ ለውጥን እስከምናገኝ ድረስ ከግንኙቱ ራሳችንን መጠበቅ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
14.0K viewsedited  02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 06:16:32 ኃዘንተኛ ለመሆን ከፈለጋችሁ . . .

ሃዘንተኛ ሰው ሆናችሁ መኖር ከፈለጋችሁ ቀላሉ መንገድ ሁልጊዜ፣ በሁሉም ቦታና በሁሉም ሁኔታ፣ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ሲጦዙ መኖር ነው፡፡

ማንም ሰው እንዳያዝንባችሁ፣ ቅር እንዳይሰኝባችሁን ሁል ጊዜ ሁሉም ሰው በእናንተ ሃሳብም ሆነ ተግባር ደስተኛ እንዲሆን የምትፈልጉ ከሆነ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አደገኛ የስሜት ቀውስ ውስጥ መግባታችሁ አይቀርም፡፡ ጉዳዩ ግን ከዚያም ትንሽ ሰፋ ያለ ነው፡፡

ቀላላል እውነቶች . . .

• ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው ሰዎችን ለማስደሰት ሌላ ሌላውን ሲኖር ራሱን ሆኖ መኖር አይችልም፤ ራሱን ሆነ የማይኖር ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡

• ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው ለማስደሰት በሚፈልገው ሰው ቁጥጥር ስር ይውላል፤ ሰው ተቆጣጥሮ እንደፈለገ የሚያደርገው ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡

• ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚሯሯጥ ሰው በየሰዓቱና በየቀኑ የሚለዋወጥ የስሜት ውጣውረድ (ሙድ) ውስጥ ራሱን ያገኘዋል፤ ስሜቱ (ሙዱ) በየጊዜው የሚለዋወጥ ሰው ደግሞ በፍጹም ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡

• ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የሚጦዝ ሰው “ሰዎችን ያስደስትልኛል” ከሚለው ሃሳብ አንጻር እንጂ ከዓላማ አንጻር መኖር አይችልም፤ ከዓላማ ውጪ የሚኖር ሰው ደግሞ ደስተኛ መሆን አይችልም፡፡

በሕይወታችሁ ሰዎችን ማስደሰት እጅግ ደስታን የሚሰጥ ልምምድ መሆኑን ማስመራችንን ሳንዘነጋ፣ የሕይወታችሁ ዋና ዓላማ ግን ማንም ሰው ቅር እንዳይሰኝባችሁ፣ በክፉ እንዳያስባችሁ፣ እንዳያወራባችሁ፣ እንዳይገፋችሁ . . . ከሆነ የዚህች ምድር አጭር እድሜያችሁን በኃዘን የምታሳልፉ ሰዎች ናቸው፡፡ በመጨረሻም፣ ሁሉንም ሰው ማስደሰት እንደማይቻል ትደርሱበትና ያን ጊዜ ደግሞ ያንን የማይቻል ነገር ለመቻል ስትጦዙ ዓመታቶቻችሁን ስላባከናችሁ በመቆጨት ታዝናላችሁ፡፡

በሉ እንግዲህ፣ ማድረግ ወደምትችሉትና ወደሚገባችሁ እውነታ ተመለሱ! ማድረግ የምትችሉት፣ በገባችሁና በአቅማችሁ መጠን ለራሳችሁ ጨዋ ኑሮን መኖር፣ ለሰዎች ደግሞ መልካም ሰው መሆንና ሁልጊዜ ከስህተት ለመታረም የተዘጋጀ ልቦና ማዳበር መሆኑን አትዘንጉ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
12.9K views03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 09:03:03
Coming Soon !

በዶ/ር ኢዮብ ማሞ የሚሰጥ ወሳኝ የስልጠኛ እድል -

ርዕስ፡- “በራእይ የሚመራ ሕይወት”

"የራሳችን ዓላማ ከሌለን የሌላን ሰው ዓላማ እንዳስፈጸምን ኖረን እናልፋለን!"

የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ

• የራእይን ትክክለኛ ትርጉም ለይቶ ለማወቅ!

• የግልን ራእይ ግልጽና ተግባራዊ በሆነ መልኩ ለመቅረጽ!

• የግልን ራእይ ለማሳካት መከተል የሚገባንን ሂደቶች በሚገባ ለመገንዘብ!

• ከሌሎች ሰልጣኞች ጋር በመገናኘት የእነሱን ልምድ ለመከፋፈል!

• ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ በግል በመገናኘት ኮቺንግ ለመቀበልና ለጥያቄዎቻችን መልስን ለማግኘት!

ለስድስት ቅዳሜ ጠዋቶች ብቻ!

ለጥራት ሲባል የሰልጣኞች ቁጥር ከ50 በታች የተገደበ!

ሙሉ መረጃውን በቅርብ ቀን ይጠብቁ!

ከሃገር ውጪ ለምትኖሩ ስልጠናው በ Zoom ስለሚዘጋጅ ፍለጎት ያላችሁ በሚከተለው የቴሌግራም አድረሻ Inbox በማድረግ ፍጎታችሁን መግለጽ ትችላላችሁ @Helinakeb
13.0K viewsedited  06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 05:00:00
ተሳስታችኋል!

• አንድ ሰው ትቷችሁ ስለሄደ ብቻ ከዚያ ሰው ውጪ መኖር እንደማትችሉ የምታስቡ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!

• አንድ ሰው ስለጎዳችሁ ብቻ ሰው ሁሉ ሊጎዳችሁ እንደሚችል ወደማመን ፍርሃት የመጣችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!

• አንድና ሁለት ነገሮች ስላልተሳኩላችሁ ብቻ ስኬተ-ቢስ እንደሆናችሁ አምናችሁ ተቀብላችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!

• ፈተናን ስለወደቃችሁ ብቻ ውዳቂ እንደሆናቸው ወደማሰብ መጥታችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!

• አንድ ሰው ወይም ሁኔታ ስላስቆሟችሁ ብቻ ወደፊት መቀጠል እንደማትችሉ ወደማመን ዝቅታ ወርዳችሁ ከሆነ . . . ተሳስታችኋል!!!

ፈጣሪ የሰጣችሁ ሕይወት ከየእለት የልምምድ ውጣ-ውረዳችሁ በላይ ነች . . . ሰዎች ከሚያደርጉባችሁ፣ ከሚያስቡባችሁና ከሚያወሩባችሁ በላይ ነች . . . ከሆነላችሁና ካልሆነላችሁ ነገር በላይ ነች . . . ከተሳካውና ካልተሳካው ነገር በላይ ነች!

ሕይወታችሁ የሚሽከረከረው ከሰዎችና ከሁኔታዎች መለዋወጥ አንጻር ወደሆነ ሕይወት የወረዳችሁ ጊዜ የስህተትን ሁሉ ትልቅ ስህተት እንደሰራችሁ አትዘንጉ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
15.6K views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 16:02:33 ጥያቄ፡-

ሰላም ዶክተር፡፡ ማግባት እፈልጋለው ለትዳር እሚሆን ወንድ አጣሁ። የሚቀርቡኝ ወንዶች በሙሉ ምክንያቱን ሳይነግሩኝ ይለዩኛል፡፡ መጥፎ ሰው ግን አደለሁም። አሁን አሁንማ ማንም አይጠይቀኝም ምን ይሻለኛል?

መልስ፡-

አሁን ባለንበት ወቅት ትክክለኛና እስከ ትዳር የሚዘልቅ ፍቅረኛ ማግኘት ትንሽ ከበድ እያለ መምጣቱን ሁላችንም እንስማማበታለን ብዬ አስባለሁ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ዘርፈ-ብዙ በመሆኑ እዚህ ለመዘርዘር ያስቸግራል፡፡ አንደኛውን ምክንያት ለመጠቆም ያህል፣ ጋብቻንና መሰል ማሕበራዊ ሂደቶችን አስመልክቶ የተለያዩ ፍልስፍናዎችና ንጽረተ-ዓለሞች እየተስፋፉ በመሄዳቸውና አንድ ወጥ ምልከታ እየቀረ በመሆኑ ነው፡፡

የትዳር አጋር ማግኘት ከባድ የሆነባቸው ምክንያቶች በርካታ የመሆናቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ እንደማንኛውም ማሕበራዊ ግንኙነት የሚያገኙን ሰዎች ሁሉ በእኛ ላይ ያላቸው አመለካከትና የሚያሳዩን ሁኔታ ተመሳሳይ ሲሆን ከሁሉም በፊት ራሳችንን ነው መጠየቅ ያለብን፡፡

ከመልክና ከቁመና ስንጀምር፣ ሁሉም ሰው የማይቀበለው መልክና ቁመና አለ ብዬ አላስብም፡፡ ለአንዱ የሚስበው ለሌላው አይስበውም፤ ለአንዱ ግድ የማይሰጠውን ሁኔታ ደግሞ ሌላው የሚመኘው አይነት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሰው የአንቺን አካላዊ ሁኔታ አይቀበለውም ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡

ምንም እንከን ሳይኖርሽ የትዳር አጋር ያላገኘሽበት ተፈጥሯዊ ሂደት ሊኖር መቻሉ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ምናልባት አብዛኛው ወንድ ስጋት እንዲያድርበት የሚያደርግ ሁኔታ አቀራረብ እንዳይኖረሽ ለማየት ሞክሪ፡፡

1. መስፈርት ማብዛት

አንዳንድ ሴቶች ከወንድ የሚጠብቁት መስፈርት ቢሰበሰብ በአንድ ሰው ላይ ሊገኝ እስከማይችል ድረስ ብዙና ከባድ ነው፡፡ የገንዘቡ፣ የእውቀቱ፣ የቁመናው፣ የአመለካከቱ፣ የራእዩ፣ የሴት አያያዙ . . . መስፈርት ሲበዛ ወንዶችን ሊያርቅ ይችላል፡፡

2. ነገር አክራሪ መሆን

አንዳንድ ሴቶች መካበድ የሌለበትን ነገር በማካበድና በማክረር ወንዶች እንዲርቋቸው ያደርጋሉ፡፡

3. ገና እንደተገናኙ የአቋም መግለጫ ማብዛት

አንዳንድ ሴቶች እንዲረግላቸው የሚፈልጉትና የማይፈልጉት ነገር ብዛቱ ብቻ ሳይሆን ገና በትውውቅ ጊዜ በአንድ ላይ ተዘርግፎ መነገሩ ወንድን ያርቀዋል፡፡

4. አጉል ጠንካራነት

አንዳንድ ሴቶች ከልክ ያለፈ ኮስታሮች፣ ጠንካሮች፣ በወንድና በሴት መካከል ምንም አይነት ልዩነት እንደሌለ (እኩልነትን ወይም የበላይነትን) ለማሳየት የሚሞክሩ አይነት ባህሪይን ሲኖቸውና ያንን ሲያንጻበርቁ ወንድን ሊያሸሹ ይችላሉ፡፡

5. ለራስ አለመጠንቀቅ

አንዳንድ ሴቶች “እኔን የሚፈልግ ሰው ቢያምርብኝም ባያምርብኝም እንዳለሁኝ ሊቀበለኝ ይገባል” የሚል መነሻው ትክክለኛ የሆነን፣ ነገር ግን እንደወረደ ተግባራዊ ከሆነ ወንዶችን ሊያርቅ የሚችል አመለካከት አላቸው፡፡ ራስን መሆንና ራስን አለመንከባከብ ግን የተለያዩ እንደሆኑ ሊያስቡ ይገባል፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
12.9K viewsedited  13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 05:01:04 “ቆልፎ ያስቀረኝ ጽሑፍ!”

ሳይጀመር የተደመደመ ሕይወት


ከሶስት አመት በፊት አንድ የአርባ አመት እድሜ ላይ የነበረ ሰው ሳማክረው፣ የሚሰራውን የስራ አይነት ከገለጠልኝ በኋላ እንዲህ ሲል አጫወተኝ፡-

“የምሰራውን ስራ አልወደውም፣ ምክንያቱም በእጄ ላይ ብዙ ሞያዎች እያሉኝ ስራዬ ግን ምንም ሞያ የማይጠይቅና ከእጅ ወደ አፍ ኑሮ የማያልፍ ክፍያ የሚከፍል ነው፡፡ በዚህ ስራ ከተሰማራሁ አስራ ሁለት አመቴ ነው፡፡ አሁን ግን እጅግ መረረኝ”፡፡

ይህንን ንግግሩን ካደመጥኩ በኋላ በመጀመሪያ የጠየኩት ጥያቄ፣ “ለምን በዚህ ስራ ይህንን ያህል አመት ለመቆየት ፈለክ?” የሚል ነበር፡፡ “በፍላጎት ነው ብለህ ነው?!” አለኝ፣ አንገቱን በማቀርቀር፡፡ “ታዲያ በምንድን ነው?” አልኩት፣ ከተል አድርጌ፡፡ እርሱም በግልጽነት ለምን በዚያ ስራ እንደከረመ በግልጽ ነገረኝ፡፡

“ገና በሃያዎቹ መጨረሻ እድሜዬ ላይ አንድ ቀን በመንገድ ቆሜ ያንኑ ስራዬን እንዴት መቀየር እንዳለብኝ በማሰላሰል ላይ ሳለሁ ነፋስ ያባረረው አንድ የመጽሔት ቁራጭ ፊቴ ደረሰ፡፡ ማንበብ ስለምወድ አነሳሁትና ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ሳይቀደድ የተረፈው ክፍል ርእስ እንዲህ የሚል ነበር፣ `የሚሆነው ይሆናል፣ የማይሆነው ደግሞ አይሆንም`፡፡ ቀልቤን ሳበኝና ማንበብ ቀጠልኩ፡፡ በወቅቱ የሚበላኝን የሕይወቴን ሁኔታ እንዳከከልኝ ተሰማኝ”፡፡ ትንሽ በዝምታ ከተዋጠ በኋላ መናገሩን ቀጠለ፡፡

“ጽሁፉን ሙሉውን ሳነበው የሚናገረው የአንድ ሰው ፍጻሜ ገና ሳይወለድ የተወሰነና የተደመደመ እንደሆነ፣ ሁሉም ሰው ሕይወት የሚያቀብለውን የቅድመ-ውሳኔ ገጠመኝ ከመቀበልና ከመኖርና ውጪ ምንም ማድረግ እንደማይችል ነው፡፡ በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ ጽሑፉ ባለሁበት ኖሬ፣ በዚሁ ሁኔታ ከማለፍ ውጪ ምንም ብታገል የተመደበልኝን መለወጥ እንደማልችል በደንብ አድርጎ አሳመነኝ፡፡ አለቀ! ከእለት ጉርስ ለማያሻግር ስራ ሰክኜ ለአመታት የመቆየቴ ሁኔታ የተቀበልኩት የመጣው ያንን ጽሑፍ ካነበብኩኝ በኋላ ነው፡፡”

“ለምን የጽሑፉን ሃሳብ ዝም ብለህ አምነህ ተቀበልከው” አልኩት፡፡ ሲመልስልኝም፣ “እኔ ቤተሰቦቼ ማን እንደሆኑ የማላውቅ፣ እድሜዬን ሁሉ ብቻዬን ታግዬ የኖርኩ ሰው ነኝ፡፡ ራሴንና ኑሮዬን ለመለወጥ የሞከርኩ፣ ነገር ግን ሁሉም ነገር አልለወጥ ብሎ ያስቸገረኝ ሰው እንደሆንኩ ቀድሞውኑ አስብ ስለነበረ ጽሑፉ ያንኑ ዝንባሌዬን አጠናከረውና አመንኩት፡፡” ከዚህ ንግግራችን በኋላ ከእሱ ጋር ብዙ የምክክር ጊዜ አሳልፈናል፡፡ አሁን አመለካከቱን፣ ራሱንና ስራውን ለውጦ እንዲያውም ሌሎችን መካሪና ደጋፊ ሆኗል፡፡ በቅርቡ ሳገኘው ያየሁበት ለውጥ አስገራሚ ነው፡፡ ይህንን ታሪኩንም በጽሑፌ እንዳካፍልም ፈቀደልኝ፡፡

የሚኖሩት ኑሮ አንዴ የተወሰነና ሊለወጥ የማይችል እንደሆነ የሚያስቡ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ፈረንጆቹ ይህንን አመለካከት fatalistic attitude ይሉታል፡፡ ያለቀለትና ቅድመ-ድምዳሜ ተወስኖለት የተጀመረ ሕይወት እንዳለን ማመንን የሚጠቁም ሃሳብ ነው፡፡

ይህ አይነቱ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በሕይወታቸው ያለውን ምንም ነገር ለመቀየር አቅሙ እንደሌላቸው ነው የሚያስቡት፡፡ የወቅቱ ኑሯቸው ሁኔታ ለእነሱ የተመደበና ምንም ቢታገሉ ሊለወጥ እንደማይችል ያስባሉ፡፡ ስለዚህም የነበረውንና ያለውን በመቀበል ያዘግማሉ፡፡
እንደዚህ አይነት ሰዎች በዙሪያቸው ብዙ ሰዎች በማለም፣ በመስራትና በማመን ሕወታቸውን ሲለውጡ እያዩ እንኳን ንቅንቅ አይሉም፡፡ ምክንያቱም እነዚያኞቹ በሕይወታቸው የሚያዩት ለውጥም ሳይቀር ቀድሞውኑ ለእነሱ የተወሰነላቸው እንደሆነ ስለሚስቡ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ራስን ለማሻሻል ምንም አይነት መነሳሳት ስማይኖራቸው የመጣላቸውን እየተቀበሉና ያንኑ እየኖሩ ዘመናቸውን ይጨርሳሉ፡፡

ሕይወት ግን እንደዚያ አይደለችም፡፡ ሕይወት የምርጫ መስክ ነች፡፡ ሕይወት የዘራነውን የምናበቅልባት መሬት ነች፡፡ ሕይወት ፈቃዳችንን፣ ጉልበታችንንና ሌሎችንም እሴቶቻችንን አስተባብረን ከአንድ ደረጃ ወደሌላኛው ደረጃ እንደመሰላል የምንወጣት የምታጓጓ መስክ ናት እንጂ ታሪካቸው ተጽፎና አልቆ ያከተመለትና ፍጻሜ የተበየነባቸው ሰዎች መተራመሻ አይደለችም . . .

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
13.4K views02:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 05:00:52 የሕይወት ዋጋው ስንት ነው?

አንድ ልጅ አብሮ የሚውላቸው አቻዎቹ ሁል ጊዜ እያቃለሉና እንደተራ ሰው እየቆጠሩት ይቸገር ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ አባቱ ሄደና “አባዬ የሕይወት ዋጋው ስንት ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡

አባቱ በማይረሳ ምሳሌ ሊያስተምረው ስለፈለገ፣ አንድ ከረጅም አመታት በፊት በብዙ ብር ገዝቶ ያስቀመጠውን ብዙም ተፈልጎ የማይገኝ የከበረ ድንጋይ (precious stone) በእጁ ሰጠውና ይህንን የከበረ ድንጋይ ይዘህ ወደ ሶስት ቦታዎች በየተራ ሂድ፡፡

በመጀመሪያ፣ መንደር ውስጥ ያለ ገበያ ሂድና እዚያ ስትደርስ በአንድ እጅህ የከበረውን ድንጋይ ይዘህ በማሳየት ሌላኛው እጅህን ከፍ አድርገህ ሁለት ጣቶችህን አሳያቸው፡፡ ያንን ስታደርግ የሚነገሩህን ዋጋ ስማና ምንም መልስ ሳትሰጥ ሂድ፡፡

በመቀጠልም፣ ይህንንው ተግባር በአካባቢያችን ወዳለው የከበሩ ድንጋዮች ወደሚታዩበት ሚውዚየም ድገመው፡፡ በመጨረሻም ይህንኑ ተግባር ከሚውዚዬሙ አልፍ ብሎ ወደሚገኘው ውድ የተባሉ የከበሩ ድንጋዮች ወደሚሸጥበት ሱቅ ሂድና ድገመው አለው

ልጁ እደተነገረው ገበያ ሄደና ድንጋዩን በአንድ እጁ አቅርቦ በሌላ እጁ ሁለት ጣቶቹን ከፍ አድርጎ ሲያሳይ አንድ ሴት እየሮጠች መጣችና፣ “2 ብር ከሆነ አሁኑኑ ከፍዬ እወስደዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም እንደተነገረው መልስ ሳይሰጥ ትቶ ሄደ፡፡

በመቀጠልም ወደ ሚውዚየሙ ሄደና ድንጋዩን በአንድ እጁ አቅርቦ በሌላ እጁ ሁለት ጣቶቹን ከፍ አድርጎ ሲያሳይ አንድ ጎልማሳ ፈጥ መጣና፣ “200 ብር ከሆነ አሁኑኑ እወስደዋለሁ” አለው፡፡ ልጁም እንደተነገረው መልስ ሳይሰጥ ትቶ ሄደ፡፡

በመጨረሻም የከበረ ድጋይ መሸጫ ሱቅ ሄደና ድንጋዩን በአንድ እጁ አቅርቦ በሌላ እጁ ሁለት ጣቶቹን ከፍ አድርጎ ሲያሳይ በእድሜ ጠና ያሉት የሱቁ ባለቤት፣ “ይሄንን ብዙም ተፈልጎ የማይገኝ የከበረ ድንጋይ ከየት አገኘኸው፡፡ 2 ሚሊየን ከሆነ አሁኑኑ እወስደዋለሁ” አሉት፡፡ ልጁም ወደ አባቱ ተመለሰ፡፡

አባቱ ጋር መጥቶ ያጋጠመውን ሲነግረው፣ አባትዬው የሕይወት ዋጋው ልክ እንደዚህ ነው፡፡ የዚህን የከበረ ድንጋይ ዋጋ በዚህ መልኩ ከፍና ዝቅ ያደረገው ያቀረብክበት ቦታ እንደሆነ ሁሉ፣ አንተም ራስህን ያቀረብክለት ቦታና ሰው ዋጋህን ወይ ከፍ ወይም ዝቅ ያደረገዋል፡፡ ምርጫው ያንተ ነው፡፡

ውድ አንባቢዎቼ፣ እንደተግባባን ተስፋ አደርለሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
17.2K views02:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ