2024-03-13 05:00:28
በጫጫታ የተደበቀ ማንነት!የአንድ ሰው ከልብ የመነጨ ጥያቄ . . .
ጠዋት እንደነቃሁ ከአልጋዬ ሳልወጣ የመጀመሪያ ስራዬ ሶሻል ሚዲያ በመክፈት ምን እንደተለጠፈና ምን እንደተባለ ማየትና ማድመጥ ነው፡፡ ከአልጋዬ ወጥቼ ለመውጣት ስዘጋጅ የጆሮ ማድመጫ (Earphone) በጆሮዎቼ ላይ ሰክቼ ከሰዎች ጋር እያወራሁ መዘገጃጀት አዘውትራለሁ፡፡
ከቤቴ ስወጣም አሁንም የጆሮ ማድመጫ (Earphone) በጆሮዎቼ ላይ ሰክቼ ጠዋት የጀመርኩትን የሚዲያ ጉብኝት መቀጠል ወይም የሞቀ ሙዚቃ እያደመጡ መሄድ የየእለት ልምምዴ ነው፡፡
ስራዬ ቦታ ግር-ግር ነው፡፡ በሻይ ጊዜ ካፌው ጫጫታ ነው፡፡ ምሳ የምንሄደው በቡድን ሲሆን እዚያም ካለው ጫጫታ ጋር እኛም እንደመርና እየተንጫጫን እንመገባለን፡፡
ከስራ በኋላ ወደቤቴ ከመሄዴ በፊት ከጓደኞቼ ጋር ስንንጫጫ አምሽተን እቤት እገባለሁ፡፡ ማታም እቤት ስገባ ቴሌቭዥኑ ካልጮኸ ቅር ይለኛል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ቲቪው እንደበራና እንዳወራ ሲያድር ደስ ይለኛል፡፡
ለማሰብ፣ ለማሰላሰል፣ ለማቀድ፣ ራስን ለማየት . . . ጊዜ እስከማጣ ደረስ በጫጫታ ተደብቄ ይሆን?
ማናልባት ትኩረት የማጣው፣ አንድን ነገር የማልጀምረው፣ የጀመርኩትን ነገር የማልቀጥለውና የማልጨርሰው፣ ሕይወቴ ከእለት እለት እድገት የማይታይበት ለዚያ ይሆን?
ከአንዱ ጫጫታ ወደሌላው፣ ከአንዱ ማሕበራዊ ግንኙነት ወደሌላው፣ ከአንዱ የማሕበራዊ ሚዲያ ወደሌላው . . . የሚል ሰው ለራሱ የማሰቢያ ጊዜ ስማያገኝ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምን ያህል ኋላ እንደቀረ ይደርስበታል፡፡ ይህንን ለማረም ከተፈለገ . . .
1. በቀን ውስጥ ቢያንስ 30 ደቂቃ፣ ከተቻለ የአንድ ሰዓት ጊዜ በመውሰድ ማሰብ፣ ራስን ማየት፣ ስራን መገምገም፣ እቅድ ማውጣ፡፡
2. የነገን እቅድ ማታ አውጥቶ ማደርና ጠዋት ወደ ስራ ወይም ወደ ማሕበራዊ ሕይወት ከመሰማራት በፊት የማታውን እቅድ አየት በማድረግ ማስታወስ፡፡
3. ትኩረታችንን፣ ስሜታችንንና ጊዜያችንን የምንሰጥበት ሁኔታ በጥንቃቄ መምረጥ፡፡
4. ለብቻ ስንሆን የሚያስጨንቀንን ሃሳብ ከመሸሽ ይልቅ መጋፈጥና መፍትሄ መፈለግ፡፡
https://t.me/Dreyob
https://m.youtube.com/user/naeleyob623
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
14.1K views02:00