Get Mystery Box with random crypto!

የሕይወት ዋጋው ስንት ነው? አንድ ልጅ አብሮ የሚውላቸው አቻዎቹ ሁል ጊዜ እያቃለሉና እንደተራ ሰ | Dr. Eyob Mamo

የሕይወት ዋጋው ስንት ነው?

አንድ ልጅ አብሮ የሚውላቸው አቻዎቹ ሁል ጊዜ እያቃለሉና እንደተራ ሰው እየቆጠሩት ይቸገር ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ አባቱ ሄደና “አባዬ የሕይወት ዋጋው ስንት ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡

አባቱ በማይረሳ ምሳሌ ሊያስተምረው ስለፈለገ፣ አንድ ከረጅም አመታት በፊት በብዙ ብር ገዝቶ ያስቀመጠውን ብዙም ተፈልጎ የማይገኝ የከበረ ድንጋይ (precious stone) በእጁ ሰጠውና ይህንን የከበረ ድንጋይ ይዘህ ወደ ሶስት ቦታዎች በየተራ ሂድ፡፡

በመጀመሪያ፣ መንደር ውስጥ ያለ ገበያ ሂድና እዚያ ስትደርስ በአንድ እጅህ የከበረውን ድንጋይ ይዘህ በማሳየት ሌላኛው እጅህን ከፍ አድርገህ ሁለት ጣቶችህን አሳያቸው፡፡ ያንን ስታደርግ የሚነገሩህን ዋጋ ስማና ምንም መልስ ሳትሰጥ ሂድ፡፡

በመቀጠልም፣ ይህንንው ተግባር በአካባቢያችን ወዳለው የከበሩ ድንጋዮች ወደሚታዩበት ሚውዚየም ድገመው፡፡ በመጨረሻም ይህንኑ ተግባር ከሚውዚዬሙ አልፍ ብሎ ወደሚገኘው ውድ የተባሉ የከበሩ ድንጋዮች ወደሚሸጥበት ሱቅ ሂድና ድገመው አለው

ልጁ እደተነገረው ገበያ ሄደና ድንጋዩን በአንድ እጁ አቅርቦ በሌላ እጁ ሁለት ጣቶቹን ከፍ አድርጎ ሲያሳይ አንድ ሴት እየሮጠች መጣችና፣ “2 ብር ከሆነ አሁኑኑ ከፍዬ እወስደዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም እንደተነገረው መልስ ሳይሰጥ ትቶ ሄደ፡፡

በመቀጠልም ወደ ሚውዚየሙ ሄደና ድንጋዩን በአንድ እጁ አቅርቦ በሌላ እጁ ሁለት ጣቶቹን ከፍ አድርጎ ሲያሳይ አንድ ጎልማሳ ፈጥ መጣና፣ “200 ብር ከሆነ አሁኑኑ እወስደዋለሁ” አለው፡፡ ልጁም እንደተነገረው መልስ ሳይሰጥ ትቶ ሄደ፡፡

በመጨረሻም የከበረ ድጋይ መሸጫ ሱቅ ሄደና ድንጋዩን በአንድ እጁ አቅርቦ በሌላ እጁ ሁለት ጣቶቹን ከፍ አድርጎ ሲያሳይ በእድሜ ጠና ያሉት የሱቁ ባለቤት፣ “ይሄንን ብዙም ተፈልጎ የማይገኝ የከበረ ድንጋይ ከየት አገኘኸው፡፡ 2 ሚሊየን ከሆነ አሁኑኑ እወስደዋለሁ” አሉት፡፡ ልጁም ወደ አባቱ ተመለሰ፡፡

አባቱ ጋር መጥቶ ያጋጠመውን ሲነግረው፣ አባትዬው የሕይወት ዋጋው ልክ እንደዚህ ነው፡፡ የዚህን የከበረ ድንጋይ ዋጋ በዚህ መልኩ ከፍና ዝቅ ያደረገው ያቀረብክበት ቦታ እንደሆነ ሁሉ፣ አንተም ራስህን ያቀረብክለት ቦታና ሰው ዋጋህን ወይ ከፍ ወይም ዝቅ ያደረገዋል፡፡ ምርጫው ያንተ ነው፡፡

ውድ አንባቢዎቼ፣ እንደተግባባን ተስፋ አደርለሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/