2023-04-23 22:01:10
ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
1.ጫማ ተደርጎ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ክልክል ነዉ።
ዘጽ.3፥5-6
የሐዋ.7፥39
፪ኛ ዜና 7፥14
2.ለሃጩን የማዝረክረክ ነዉር ያለበት ሰዉ ቤተክርስቲያን መግባት ክልክል ነዉ።
3.በቤተ ክርስቲያን አጸድ ግብዣ ማድረግ አይገባም።ፍት.ነገ አንቀጽ 1..ክርስቶስ ሥጋና ደም በሚሰዋበት ምዕመናን ሥጋ ወደሙን ከሚቀበሉበት ከቤተክርስቲያን ራቅ ብሎ በደረጃ ሰላም አቅራቢያ በዓዉደ ምሕረት ላይ ሥጋዊ መብል መጠጥ ማቅረብ መብላት አይገባም።
4.የቤተክርስቲያን መገልገያ ንዋያተ ቅዱሳት ለግል አገልግሎት ማዋል አይገባም።
ዳን.5፥31-35
ፍት ነገ አንቀጽ 1 አስጣ 28
5.በቅጽረ ቤተክርስቲያን ገበያ መገበያየት አይገባም።
ዮሐ.2፥14-17
ፍት.ነገ.አንቀጽ1
6.በቤተ መቅደስ በማኅበር ጸሎት ወቅት የግል ጸሎት ማድረግ ክልክል ነዉ።
7.ከቤተ መቅደስ በቅዳሴ ስዓት አሀዱ ከተባለ ጊዜ ጀምሮ አቋርጦ መዉጣትም ሆነ መንቀሳቀስ ክልክል ነዉ።
ማቴ.26፥26
ዕንባ.2፥20
8.ሴት ልጅ በወር አበባ ወቅት ወደ ቤተ መቅደስ መግባት አይፈቀድላትም።
ዘሌዋ.15፥18-30
ፍት.ነገ.አንቀጽ.14፥583
9.ወንድ ልጅ ሕልመ ሌሊት /ዝንየት/ ከመታዉ በዕለቱ ወደ ቤተ መቅደስ ከይገባም።
ዘሌዋ.15፥2-18
10.የሌሊት ልብስ /የአረማዉያን ልብስ/ ለብሶ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ክልክል ነዉ።
፩ኛ ቆሮ.11፥5-14
11.ባልና ሚስት ከተራክቦ በኋላ ዕለቱን ወደ ቤተ መቅደስ ለመግባት አይፈቀድላቸዉም።ጋብቻ ቅዱስ መኝታዉም ንጹሕ ሲሆን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ከተራክቦ በኋላ ዕለቱን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት አይቻልም።ቅዱስ ጳዉሎስ "ለጸሎት በመፈቃቀድ ካልሆነ በስተቀር ባልና ሚስት አይከላከሉ" እንዳለዉ ባልና ሚስት ከተራክቦ የሚርቁት በበዓላት፤በአጽዋማት ለጸሎትና ለቅዳሴ በሚዘጋጁበት ዕለታት በሰንበት ነዉ።ስለዚህ ጠዋት ለቅዳሴ በሚዘጋጁበት ጊዜ እራሳቸዉን ሊጠብቁ ይገባል።
፩ኛ ቆሮ.7፥5
ኩፋሌ.34፥12
ዘጸ.19፥15
12.በቤተ መቅደስ ዉስጥ መሳቅ፤መሳለቅ፤ዋዛፈዛዛ ነገር መነጋገር ክልክል ነዉ።ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በምድርዊ ንጉሥ ፊት በቆምክ ጊዜ በምንም ምክንያት ቢሆን ለመሳቅ አትደፋፈርም ታዲያ በሰማያዊ ንጉሠ ነገሥት ፊት ትስቃለህን?ብሏል።
ተግሳጽ ዘዮሐንስ አፈወርቅ አንቀጽ ስድስት(6) በቅዳሴ ስዓት ጊዜ የሚስቅ ዓለማዊ ቢሆን ወደ ዉጭ ያዉጡት ከቅዱስ ምስጢር/ከቁርባኑ/አያቀብሉት ተብሏል።
ቀኖና ባስሌዎስ አንቀጽ 79
13.አብዝቶ ጠጥቶና ሰክሮ መግባት ክልክል ነዉ።እንዳትሞቱ ወደ መገናኛዉ ድንኳን ስትገቡ አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክር ነገር ሁሉ አትጠጡ።
ዘሌዋ.10፥8-10
ሉቃ.21፥34
ምሳሌ.23፥29-35
ይሁንና ይህን ወይን አትጠጣ ቀምሰህ ፈጣሪህን ለማመስገን ያህል ብቻ ይሁን እንጂ እንደ ጢሞቴዎስ ብትታመም ከገድል ጽናት የተነሳ ጽኑ ደዌ ብትያዝ።ግን ከወይን ጥቂት ጠጣ እርሱ ለሥጋ ሕይወት ይሆንሃልና።
፩ኛ ጢሞ.5፥24
ሃይማኖት አበዉ ዘሠለስቱ ምዕት 21፥17-18
14.በቂም በቀል ሰዉን አስቀይሞ የሰዉ ገንዘብ በማጭበርበር ወስዶ ቤተክርስቲያን መጥቶ መጸለይ ክልክል ነዉ።
ማቴ.5፥23-24
ማር.11፥25
ሉቃ.18፥9-14
15.ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ ከተቀደሰ ስፍራ እንደቆምክ አስተዉል።
መክ.5፥1
"ቤተ ክርስቲያን የመሳለም ስርዓት"
ጠዋትና ማታ ቤተክርስቲያንን ለመሳለም መትጋት ያስፈልጋል።ምሳ.8፥34
ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርሱ መሳለም ይገባል።
መዝ.28፥2፣95፥9
ኤር.26፥2
ሕዝ.46፥3
ፊልጵ.2፥9-10
ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ ጫማ አዉልቆ ወገብን ታጥቆ አደግድጎ መግባት ነዉ።
ጫማ አድርጎ ወደ ቤተክርስቲያን መግባት ክልክል ነዉ።
የሐዋ.7፥33
ኢያ.5፥15
ፍት.ነገ.12
"ወደዚህ አትቅረብ አንተ የቆምኽባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማኽን ከእግርኽ አዉጣ"(ዘፀ.3፥5)።
"አሁን ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይክነን ቤት መርጫለኹ ቀድሻለሁም ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይኾናሉ" ፪ኛ.ዜና 7፥16።
"ቤተ መቅደስኽ ቅዱስ ነዉ፤በጽድቅም ድንቅ ነዉ" መዝ.64፥5
"በቅድስት ከተማ ስም የተጠራችሁ ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሚባል በእስራኤል አምላክ የምትደገፉ የያዕቆብ ቤት ሆይ ይኽነን ስሙ"(ኢሳ.48፥2)
"እድፈት ወይንም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲኽ ያለ ነገር ሳይኾንባት ቅድስትና ያለ ነዉር ትኾን ዘንድ ክብርት የኾነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ" (ኤፌ.5፥27)
"እኛም በቅዱሱ ተራራ ከርሱ ጋር ሳለን ይኽነን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን"(፪ኛ ጴጥ.1፥18)
አሳብን በመንፈሳዊ ነገር ወስኖ ወደ ዉጪ ወደ ዓለማዊ ነገር እንዲይሔድ መግታትና መቆጣጠር ያስፈልጋል።
ከካህን ቀርቦ መስቀል መሳለምና በረከትም መቀበል ያሻል።
በቤተ ክስስቲያኑ ዉስጥ ተስለዉ የሚገኙትን የሥላሴን፤የመድኀኒታችንን የኢየሱስ የክርስቶስን፤የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን፤የመላእክትን፤የነቢያትን፤የሐዋርያትን፤የጻድቃንን፤የሰማዕታትን፤የደጋጎች የቅዱሳን አበዉን ሥዕሎች እጅ መንሳትና የአክብሮት የስግደት መስገድ ይገባል።
በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ መሳቅ ስለዓለማዊ ሥራ መሳቅ ስለዓለማዊ ሥራ መነጋገር ክልክል ነዉ።ከገቡ በኋላ በዝምታ፣በጸጥታ፣በፍርሃት፣የእግዚአብሔርን ምሕረት በጥብዓተ ልብ መፈለግ አለ።ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን የመዘምራንን ማሕሌት፣የቅዱሳን መላእክትን ምስጋና፣የነቢያትን ትንቢያትን፣የሐዋርያትን ስብከት መስሚያና የልዑል እግዚአብሔርን ነገር መማሪያ ቦታ ስለሆነች ነዉ።ከዚህ ሌላ የሥጋ ወደሙ ምስጢር የሚፈጸምባት ናት።
ዘሌ.26፥2
ዮሐ.አፈ ወርቅ.19፥32 "እስመ ቤተ ክርስቲያን በአምሳለ ሰማይ ወመሐይምናን ይኩኑ ወሰቲታ አምሳለ መላእክት ወያፅምዑ በትዕግሥት ወበአርምሞ ወይትመሐለሉ በልቦሙ ዘእንበለ ዕረፍት" ዮሐ.አፈ.አንቀጽ48። "ኢይትናገር አሐዱ ለግሙራ በዉስተ ቤተክርስቲያን እስመ ቤተ እግዚአብሔር ቤተ ጸሎት ወአኮ ቤተ ነገር ወዘተናገረ በዉስቴታ ይጻዕ ወኢይቅረብ በይእቲ ዕለት (ቀኖና አቡሊዲስ ከንቀጽ 7) ወሶበ ትቀዉም ቅድመ ንጉሥ ምድራዊ ዘኢትደፍር ከመ.ትስሐቅ ወኢምንተኒ ትስሕቅኑ ሶበ ትቀዉም ቅድመ ንጉሠ ነገሥት ሰማያዊ" ዮሐ.አፈወርቅ.አንቀጽ 6።
"እመኬ ዓለማዊ ሶበ ይስሕቅ በዉስተ ቅዳሴ ያዉጽእዎ አፍአ ወኢይመጥዉዎ እምሥጢር ቅዱስ" ቀኖና ባስልዮስ አንቀጽ 79
አጭርና ያደፈ ልብስ ለብሶ ወደ ቤተክስስቲያን መሔድ ክልክል ነዉ።ረዘም ያለና ንጹሕ ልብስ ለብሶ መሔድ ያስፈልጋል ዘፀ.19፥10-11
በተለይ ሴትች ራሳቸዉን ተከናንበዉ እንዲጸልዩ ታዝዘዋል።"ኢይባዕ ብእሲ ኀበ ቤተ ክርስቲያን ወኢይጸሊ ዉስቴታ ዘእንበለ ይኩን ልብሱ ድርማንቀ በከመ ይቤ ጳዉሎስ ሐዋርያ ለብሔረ ቆሮንጦስ ቀዳማዊ ለእመ ኮነ ዘይጺሊ አልባሲሁ ሐፂረ ወይትከሠት እምኔሁ ጊዜ ስግዴቱ ይእቲ መፅዓሉ ዘቀበጽነ በእንቲአሁ ወይከዉን ጌጋየ ለዘነጸረ ለዘተነጸረ እስመ ለዘነጸረ ይመጽእ ዐቱ ስሐ ወበእንተዝ ይወርድ ላእሌሁ ከመ ወረደ ላዕለ ወልያ ኖኅ ሶበ ስሐቀ ዲበ አቡሁ በከመ ይቤ መጽሐፈ ኦሪት ወዘነጸረ እስመ ኮነ ምክንያተ ለአብጽሖ ጌጋዩ ለዘነጽቱ አበሳሁ " ዮሐንስ አፈወርቅ አንቀጽ 4፥49-72
ዘፍ.9፥21-27
፩ኛ.ቆሮ.11፥5-14
ወደ ቤተ ክርስቲያን ባዶ እጅ መሔድ አይገባም መባዕ፣ምጽዋት ይዞ መሔድ/ዘፀ.34፥20።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
ይቆየን።
3 views19:01