Get Mystery Box with random crypto!

ትንቢተ አሞጽ Amos 9 ምዕራፍ፡9። 1፤ጌታን፡በመሠዊያው፡አጠገብ፡ቆሞ፡አየኹት፤ርሱም፡እንዲህ፡አ | ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።

ትንቢተ አሞጽ Amos 9

ምዕራፍ፡9።
1፤ጌታን፡በመሠዊያው፡አጠገብ፡ቆሞ፡አየኹት፤ርሱም፡እንዲህ፡አለ፦መድረኮቹ፡ይናወጡ፡ዘንድ፡
ጕልላቶቹን፡ምታ፥በራሳቸውም፡ዅሉ፡ላይ፡ሰባብራቸው፤እኔም፡ከነርሱ፡የቀሩትን፡በሰይፍ፡
እገድላለኹ፤የሚሸሽ፡አያመልጥም፥የሚያመልጥም፡አይድንም።
2፤ወደ፡ሲኦል፡ቢወርዱ፡እጄ፡ከዚያ፡ታወጣቸዋለች፤ወደ፡ሰማይም፡ቢወጡ፡ከዚያ፡አወርዳቸዋለኹ፤
3፤በቀርሜሎስም፡ራስ፡ውስጥ፡ቢሸሸጉ፡ፈልጌ፡ከዚያ፡አወጣቸዋለኹ፤በጥልቅ፡ባሕርም፡ውስጥ፡ከዐይኔ፡
ቢደበቁ፡ከዚያ፡እባቡን፡አዛ፟ለኹ፥ርሱም፡ይነድፋቸዋል፤
4፤በጠላቶቻቸውም፡ፊት፡ተማርከው፡ቢኼዱ፡ከዚያ፡ሰይፍን፡አዛ፟ለኹ፥ርሱም፡ይገድላቸዋል፤ዐይኔንም፡
በእነርሱ፡ላይ፡ለክፋት፡እንጂ፡ለመልካም፡አላደርግም።
5፤የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ምድርን፡ይዳስሳል፡ርሷም፡ትቀልጣለች፥የሚኖሩባትም፡ዅሉ፡
ያለቅሳሉ፤መላ፟ዋም፡እንደ፡ግብጽ፡ወንዝ፡ትነሣለች፥ደግሞ፡እንደ፡ግብጽ፡ወንዝ፡ትወርዳለች።
6፤አዳራሹን፡በሰማይ፡የሠራ፥ጠፈሩንም፡በምድር፡ላይ፡የመሠረተ፥የባሕርንም፡ውሃ፡ጠርቶ፡በምድር፡ፊት፡
ላይ፡የሚያፈሰ፟ው፡ርሱ፡ነው፤ስሙም፡እግዚአብሔር፡ነው።
7፤የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥እናንተ፡ለእኔ፡እንደ፡ኢትዮጵያ፡ልጆች፡አይደላችኹምን፧ይላል፡
እግዚአብሔር፦እስራኤልን፡ከግብጽ፡ምድር፥ፍልስጥኤማውያንንም፡ከከፍቶር፥ሶርያውያንንም፡ከቂር፡
አላወጣኹምን፧
8፤እንሆ፥የጌታ፡የእግዚአብሔር፡ዐይኖች፡በኀጢአተኛ፡መንግሥት፡ላይ፡ናቸው፥ከምድርም፡ፊት፡
አጠፋታለኹ፤ነገር፡ግን፥የያዕቆብን፡ቤት፡ፈጽሜ፡አላጠፋም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
9፤እንሆ፥አዛ፟ለኹ፥እኽልም፡በወንፊት፡እንዲነፋ፡የእስራኤልን፡ቤት፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡መካከል፡
እነፋለኹ፤ነገር፡ግን፥አንዲት፡ቅንጣት፡በምድር፡ላይ፡አትወድቅም።
10፤ክፉው፡ነገር፡አይደርስብንም፥አያገኘንምም፡የሚሉ፡የሕዝቤ፡ኀጢአተኛዎች፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ይሞታሉ።
11፤በዚያ፡ቀን፡የወደቀችውን፡የዳዊትን፡ድንኳን፡አነሣለኹ፥የተናደውንም፡ቅጥሯን፡
እጠግናለኹ፤የፈረሰውንም፡ዐድሳለኹ፥እንደ፡ቀደመውም፡ዘመን፡እሠራታለኹ፤
12፤ይኸውም፡የኤዶምያስን፡ቅሬታ፥ስሜም፡የተጠራባቸውን፡አሕዛብን፡ዅሉ፡ይወርሱ፡ዘንድ፡ነው፥ይላል፡
ይህን፡የሚያደርግ፡እግዚአብሔር።
13፤እንሆ፥አራሹ፡ዐጫጁን፥ወይን፡ጠማቂውም፡ዘሪውን፡የሚያገኝበት፡ወራት፡ይመጣል፥ይላል፡
እግዚአብሔር፤ተራራዎችም፡በተሓውን፡የወይን፡ጠጅ፡ያንጠባጥባሉ፥ኰረብታዎችም፡ዅሉ፡ይቀልጣሉ።
14፤የሕዝቤን፡የእስራኤልን፡ምርኮ፡እመልሳለኹ፥የፈረሱትንም፡ከተማዎች፡ሠርተው፡
ይቀመጡባቸዋል፤ወይንንም፡ይተክላሉ፥የወይን፡ጠጁንም፡ይጠጣሉ፤አታክልትንም፡ያበጃሉ፥ፍሬውንም፡
ይበላሉ።
15፤በምድራቸውም፡እተክላቸዋለኹ፥ከእንግዲህም፡ወዲህ፡ከሰጠዃቸው፡ከምድራቸው፡አይነቀሉም፥ይላል፡
አምላክኽ፡እግዚአብሔር፨