Get Mystery Box with random crypto!

ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።

የቴሌግራም ቻናል አርማ dereje1678 — ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።
የቴሌግራም ቻናል አርማ dereje1678 — ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።
የሰርጥ አድራሻ: @dereje1678
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 38

2022-07-06 20:48:16 መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ፥ አለቃ አያሌው ታምሩ ሰኔ-30-1999 ዓ.ም

አለቃ ከማረፋቸው ወር ከሁለት ሳምንት ቀደም ብሎ ያስተማሩት ትምህርት ነው!
15 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:48:16 ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ ፴ ፤ በዓለ ልደቱ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና የመጥምቁ ታሪክ ባጭሩ።
17 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 15:22:21 መልክአ_ኢትዮጵያ
#የቅድስት_ድንግል_ማርያም_የአሥራት_ሀገር ፤
#የብዙ_ቅዱሳኑ_መጠጊያ ፤
#ሀገረ_እግዚአብሔር_ቅድስት_ኢትዮጵያ ።
+++
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ኢትዮጵያ !
ሀገሩ ለተክለ ሃይማኖት ሐዋርያ፤
ህዝብኪ ይዜምሩ እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ።
የሃይማኖት ድር የዉበት መለያ፤
ቀደምት ባለ ታሪክ የዓለም አርአያ።
........
ሰላም ለአይንትኪ እለ ርእያ ፈጣሪ፤
ታምረ ኩሉ ገባሪ።
ማዳን ፍቅሩን ላዩ፤
ከጸሎት ላልዘገዩ።
........
ሰላም ለአእዛንኪ እለ ሰምዓ ፈጣሪ፤
በከመ ኮነ እግዚአብሔር መሐሪ፤
ቅዳሴው ሰዓታቱ፤ ላደመጡ ማኅሌቱ።
.......
ሰላም ለአፉኪ ዘነበበ ወንጌሉ፤
እንዘ ይፌጽም ቃሉ፤
ሃሌሉያን ለለመደ፤
አኰቴትን ለወደደ፤
ቅኔ ዜማን ላወረደ።
.......
ሰላም ለገጽኪ ለለብሰ ልምላሜ፤
መልዓ ምሥጢር ወትርጓሜ፤
ለማይሽረው ዘመን እድሜ፤
የመልከኛ ሥያሜ፤
ለሆነው የውበት ፍጻሜ።
......
ሰላም ለሀዳፍኪ እለ ሰፋ ሀበ እግዚአብሔር ህያው፤
ጸሎቱ እና ሙያው፤
ውዳሴ ነውና ግብሩ፤
ጌታሽ ነውና ክብሩ።
.......
ሰላም ለከርስኪ ዘአስረጸ ማዬ፤
ለጸሙ ሰብ ዘአስተዬ፤
ቅዱሱ ጸበል ለፈቀበት፤
የቅዱሳኑ አጽም ላረፈበት፤
ፈዋሹ እምነት ለተገኘበት።
.......
ሰላም ለዘባንኪ እምዘባነ አለም ዘተሌለዬ፤
ጸዊረ ተሰዓቱ ቅዱሳን በሰቢከ ወንጌል ዘአብ፤
እንግዳን መቀበል ላልደከሙ፤
መካናትሽን ለተሸከሙ።
.......
ሰላም ለወልድኪ ያሬድ ማኅሌታይ፤
ወጣእመ ዜማ ቀዳማይ፤
ግዕዝ እዝል ወአራራይ።
ምድርሽን በዝማሬ ላራሰ፤
የአፉን ቅኔ ላፈሰሰ።
......
ሰላም ለወልድኪ አባ ተክለ ሃይማኖት ፤
ዘሖረ በሰናይ ፍኖት፤
እንደ መላእክቱ በክንፍ ለበረረ፤
ባከበረው ንጉስ ለከበረ፤
ጣዖታትን ለሰበረ።
.......
ሰላም ለወልድኪ አባ ዜና ማርቆስ፤
ሐዋርያሁ ለክርስቶስ፤
እምዘመደ ተክለ ሃይማኖት ባህታዊ፤
ጥሪው ሰማያዊ፤
መንገዱ ሰላማዊ።
......
ሰላም ለወለትኪ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ፤
እንበለ መጠን ዘበስዓ እበያ ወክብራ፤
ለተመሰገነች በጽድቅ ሥራ፤
እጅ ላልሰጠች ለዓለም ምርኮ፤
ለጸናች በአምልኮ።
......
ሰላም ለመካንኪ ግሸን ደብረ ከርቤ፤
ለይዜምሩ ካህናት በፍሥሐ ወበይባቤ፤
ፍኖተ ብርሃን ይእቲ፤
መንበረ መስቀሉ ዛቲ፤
መግቢያ በሯ አሐቲ።
........
ሰላም ለመካንኪ መካነ ቅዱሳን ዝቋላ፤
እንተ ጸለዬ በአንቲ ገበረ መንፈስ ቅዱስ በማዕከላ፤
የቅዱሳኑ መፍለቂያ፤
የሰዓታቱ መድመቂያ።
........
ሰላም ለመካንኪ እንተ ተሰይመት ጻድቃኔ፤
በአት ይእቲ ለመናኔ፤
የድውያኑ መፈወሻ፤
የሀዘንተኞች ጭንቅ መርሻ፤
የዲያቢሎስ ድል መንሻ።
.......
ሰላም ለመካንኪ ደብረ ላሊበላ፤
መካነ ትብስእት ወተድላ፤
የጸጋው ዘይት ሲፈላ፤
የተቀባው ልጅሽ፤
ላነጸው መቅደስ በደጅሽ።
........
ሰላም ለመካንኪ መርጦ ለማርያም፤
ደብረ ምሕረት ወሰላም፤
ለማይቋረጥባት እንጣኑ፤
ለሚጸልዩባት ቅዱሳኑ፤
ለፈለቁባት ምሁራኑ።
........
ሰላም ለመካንኪ ደብረ ዮሐንስ ሸንኮራ፤
እምነ ውስቴታ ደናግል ዘይዜምራ፤
ጸበሉ እውራንን የሚያበራ፤
የዮሐንስ ገዳም የመጥምቁ፤
የዘካርያስ ልጅ የጻድቁ።
........
ሰላም ለመካንኪ ደብረ ጽዮን አክሱም፤
እንተ ሀለወ ባቲ ታቦተ ጥንታዊት ወቅድም፤
ለጽዮን መኖሪያ ለከበረችው፤
ዳጎንን ለሰበረችው፤
ዳዊትን ካባ ላስጣለችው።
.......
ሰላም ለመካንኪ ዋልድባ ሰላማዊት፤
አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፤
የአባ ሳሙኤል ገዳማቸው፤
ለሚተረክባት ገድላቸው፤
ላከበራት ጸሎታቸው።
.....
ሰላም ለመካንኪ ደብረ አሰቦት ቅድስት፤
መካነ ቡሩካን ውድስት፤
ጸሎት ላልራቃት ጠዋት ማታ፤
ለቀደሳት ጌታ።
......
ሰላም ለመካንኪ ደብረ ሊባኖስ ገዳሙ፤
እንተ አእረፈ ባቲ ለተክለ ሃይማኖት አጽሙ፤
ቅዱሱ ደብር መታሰቢያ፤
የመናንያን መሰብሰቢያ፤
የባለ ቅኔው ማሸብሸቢያ።
.......
ሰላም ለመካንኪ መካነ ሰላም ደብረ ዳሞ፤
ይጸልዩ ባቲ አበው ቅዱሳን በአርምሞ፤
አረጋዊ በዘንዶ፤
በገደል ላይ ተረማምዶ፤
ለገደማት ጌታ ፈቅዶ።
........
ሰላም ለመካንኪ ምስራቀ ፀሐይ ዘደብረ ዘይት፤
መካነ ሕይዎት አማናዊት፤
ላሳደገችን በውብ ቋንቋ፤
ላስያዘችኝ የዜማ ቃል።
......
ሰላም ለአቡኪ ወልደ ማርያም፤
ንጉሰ ነገስት ስቡህ በአርያም፤
ጠላትሽን ለተዋጋ፤
ለብርታሽ ክንዱን ለዘረጋ፤
ቅጥርሽን በእሳት ለዘጋ።
........
ሰላም ለእምኪ እመ ብዙኃን፤
ዛቲ ይእቲ ተድላ ብዙኃን፤
በአሥራት ለተሰጠሻት፤
በየዘመን ለጠራሻት፤
ስለ ፍቅሯ እናት ላልሻት።
#መልክአ_ኢትዮጵያ።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አስራት ሀገርሽን ኢትዮጵያን
አስቢያት።
+።+።+።+
-ሰለ እናትህ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም:
-ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ
-ስለ ቅዱስ ያሬድ
-ስለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
-ስለ ቅድስት አርሴማ
-ስለ ዜና ማርቆስ
-ስለ አባ ኪሮስ
-ስለ አቡነ ሀብተማርያም
-ስለ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትቅዱስ
-ስለ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ:
-ስለ አቡነ ገብረመንፈስ
-ስለ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ብለህ ኢትዮጵያን ማራት ይቅር በላት። አሜን
21 views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 08:40:53
20 views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 23:03:39
በቅዱሱ አባታችን በየኔታ አባ ነብዩ ልዑል ብተር የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ጎንደር ስማዳ ዉሃዉ ደም ሆነ የፅዋዋዉ ዋንጫ ሞልቶ ፈሰሰ ኦ ክርስቶስ ማረን አድነን
ኢትዮጵያ በደም ታጥባለች ይፈርዳል የላይኛው ጌታ ገዳዮቻችን የት ይሆን መግቢያችሁ
24 views20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 23:01:38
19 views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 21:15:58
20 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ