2022-07-08 07:53:13
ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ማለት ልዩ ነው ትርጉሙ።
➊.ኢትዮጵያ ማለት “ለአምላክ የሚሰጥ የወርቅ ሥጦታ” ማለት ነው።
:
➋.ኢት=አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ማለት ሲሆን ዮጵ= ቢጫ ወርቅ፣ ውድ ወርቅ፣ ልዩ ወርቅ ማለት ነው።
:
➌.ኢትዮጵያ ማለት እኔና እናንተ በምናውቃት ልክ ብቻ ያለች ሀገር አይደለችም።
:
➍.ኢትዮጵያ ማለት ከምድር ሀገራት ሁሉ እጅግ ምስጢራዊና ረቂቅ ሀገር ናት።
:
፩."ብሉይ ኪዳን!"
:
➊ኛ).ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ ያስተማረው ኢትዮጵያዊው ዮቶር ነው።
:
ስለዚህ ለእስራኤል ከፈርዖን ነጻ መውጣት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና አለበት ማለት ነው።
:
አዎ የዮቶር ርስት ውብ ሀገር ኢትዮጵያ ነች።
:
➋ኛ).አሁንም የሊቀ ነብያት ሙሴ ሚስት ሲጳራ ኢትዮጵያዊት ነች።
:
ሲጳራ የኢትዮጵያዊው የዮቶር ልጅ ነች። ሙሴ ይቺን ኢትዮጵዊት ሴት በማግባቱ ወንድሙ አሮንና እህቱ ማርያም ያጉረመርሙበት ነበር። እግዚአብሔርም ገሰፃቸው።
:
➌ኛ).አብርሐምን የቀባው የክርስቶስ ምሳሌ የሚባለው የመጀመሪያው ካህን መልከጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው።
፡
ይህ ካህን በክርስትና አስተምህሮ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ ይቆጠራል።
፡
➍ኛ).በሀገረ እስራኤል የራሷ ቦታ ያላት (ዴር ሡልጣን) ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች።
:
ይህንን ቦታ ምዕራባውያንና አንዳንድ የምሥራቅ ሀገራት ለመውሰድ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ታሪክ ይዘክራል።
:
➎ኛ).ከባቢሎን ዘመን አስቀድሞ የነበረው ብቸኛው የሰው ልጅ ቋንቋ (ግዕዝ) የሚገኘው ኢትዮጵያ /ቤተ-ክርስቲያን/ ውስጥ ነው።
፡
ይህ ቋንቋ ዓለም እጅግ የሚያከብረው ትልቅና ቀዳሚ ልሣን ነው። ይሄንን ደግሞ ራሳቸው ምዕራባውያን ይመሰክራሉ። በዚህ ቋንቋ ብዙ እልፍ ድርሳናትና ምሥጢራት ተከትበዋል።
፡
➏ኛ).ጻዲቁ አባታችን የሄኖክ የልጅ ልጅ ኖኅ የተቀበረው ኢትዮጵያ/ጎንደር/ ውስጥ ነው።
:
የሰው ልጅ ኃጢአትን በመሥራቱ እግዚአብሔር ምድርን በንፍር ውኃ መላት፣ ኖኅና ቤተሰቦቹ ብቻ ቀሩ። ይህ ሰው መቃብሩ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
:
➐ኛ). ኖኅ ራሱንና ልጆቹን ከንፍር ውኃ ያዳነባት መርከቡን ያሳረፋት ኢትዮጵያ/ ጣና አካባቢ ከሚገኘው አራራት ተራራ ላይ ነው።
:
➑ኛ).የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረው ከአቱተ ባሕርያተ ሥጋ ነው።
:
ከእነዚህም መካከል ደግሞ የተፈጠረበት እሳት ውኃና ነፋስ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው። ከዚህም በመነሳት አንዳንዶች አዳምና ሄዋን ኢትዮጵያዊያን ናቸው ይላሉ።
:
እውነት ነው! ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ነች። ያች በቁፋሮ የተገኘች የዝንጀሮ አጽም ድንቅነሽ (ሉሲ) ስለተገኘችባት ሳይሆን የእግዚአብሔር የእጁ ሥራ የሆነው አዳም ስለተገኘባት ነው።
:
➒ኛ).ከገነት ከሚመነጩና ገነትን ከሚያጠጡ አራት አፍላጋት/ምንጮች/ ትልቁ ግዮን ኢትዮጵያዊ ነው።
:
ግዮን ከገነት ይመነጭና ወደ ምድር ይፈሳል፣ ከዚያም የኢትዮጵያን ምድር ይከባል። ይህ ወንዝ ጎጃም ውስጥ ሰከላ አካባቢ ግሽ ዓባይ የተሰኘ ቦታ ላይ ነው የሚፈልቀው። ከዚያም ሙሉ ጎጃምን እንደመቀነት ይዞርና ወደ ግብጽ ይፈሳል።
:
➓ኛ).ሞትን ሳይቀምስ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተወሰደውና አዕምሮውን መቶ በመቶ(100%) የተጠቀመበት ብቸኛው የምድራችን ሰው ሄኖክ/ ኢትዮጵያዊ/ ነው።
:
እስከዛሬ ድረስ አዕምሮውን ሙሉ በሙሉ የተጠቀመ ምድራዊ ሰው የለም። የሰው ልጅ የአእምሮው ልዕልና የሚለካው በምድራዊ እውቀት ሳይሆን በሰማያዊ ጥበብ ነው።
:
ሰው የአዕምሮው ልዕልና (IQ) ሲያድግ ወደ ቅድስና ደረጃ ይሸጋገራል እንጅ ምዕራባዊያን እንደሚሉት በምድራዊ ጥበብና እውቀት አይመላም። ይሄን ደግሞ ያደረገ ብቸኛው ሰው ሐበሻው ሄኖክ ብቻ ነው።
:
➊➊ኛ)ሲኦልም ገነትም የሚገኙት በመልአኩ 15 ክንድ ከምድር ከፍ ብለው ኢትዮጵያ (አፋር ኤርታሌና ጎጃም ጣና አካባቢ በቅደም ተከተል) ነው።
:
በድሮው ወሎ ክፍለ ሀገር በዛሬው አፋር ውስጥ የሚገኘው ኤርታሌ የሚባለው ቦታ የራሱ ሰማያዊ ምሥጢር አለው።
:
እዚህ ቦታ ላይ የሚገኘው እሳተ ገሞራ ወይም የእሳት ባህር ሉሲፈር (ሳጥናኤል) የታሰረበት ቦታ መሆኑን አንዳንድ መዛግብት ላይ ለማንበብ ችያለሁ።
:
አዎ ይህ ቦታ የሲኦል መገኛ እንደሆነና ጎጃም የሚባለው ሀገር ላይ በተለይም ደግሞ ጣና ዙሪያ የገነት መገኛ ናቸው።
:
➊➋ኛ).በዓለም ትክክለኛነቱ የተረጋገጠለት የዘመን ስሌት ያለው ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ (ኢትዮጵያ) ውስጥ ነው።
፡
ይህ የዘመን ስሌት አጽዋማትና በዓላት የሚከበሩበት ቀመር የቀናት ብሎም የዓመታት ስሌቱ ያልተበረዘና ትክክለኛ ነው።
:
➊➌ኛ).በነብያት እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የተባለች ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች።
፡
አዎ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መመኪያዋም አለኝታዋም እርሱ ነውና።
:
ይች ሀገር ከፈጣሪዋ ጋር ልዩ ትስስር ያላት የዓለማችን ብቸኛ ሀገር ነች። ፈጣሪ በስጋ የተመላለሰባት ሀገር እስራኤል እንኳን የኢትዮጵያን ያህል ክብር በፈጣሪ ዘንድ የላትም።
:
ለዚህ ደግሞ ማሳያ የሚሆነን ነገር አለ። እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል እስራኤላዊያንን ሲገስጽ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያዊያን ልጆች (ሐበሾች) አይደላችሁም ነበር ያለ። ልብ በሉ! እንደ ኢትዮጵያዊያን!
:
➊➍ኛ).ታቦተ ጽዮን የሙሴ ጽላት የምትገኝባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች።
:
በአምላክ ትዕዛዝና ቀመር የተሰራችው ይህቺ ጽላት በጠቢቡ ሰለሞን የንግሥና ጊዜ የደቡብ ንግስት (ንግስተ አዜብ) ወይም የሳባ ንግስት (ንግስተ ሳባ) ተብላ በምትጠራዋ ንግስት ማክዳ ልጅ በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ነበር ወደ ሀገራችን የገባችው።
:
ምዕራባዊያን ይህቺን መመኪያችንን ጽላት ዘሙሴ ለመውሰድ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል። ነገር ግን አልተሳካላቸውም፣ አይሳካላቸውምም። ምክንያቱም እነርሱን ትታ በእኛ ምድር በሀገራችን ትኖር ዘንድ በእግዚአብሔር ፍቃድ መጥታለችና ሊወስዷት ቢኳትኑም አያገኟትም።
፡
➊➏ኛ).የዘንዶ ራስ ተቀጥቅጦ ልዩ ምግብ (ጤፍ) ከፈጣሪ የተሰጣቸው ሕዝቦች /ሐበሾች/ ያሉባት ምድር ነች ኢትዮጵያ።
:
አንተም የዘንዶውን ራስ ቀጠቀጥህ፣ ለኢትዮጵያዊያን ሰዎችም ልዩ ምግብን ሰጠሀቸው ይላል ቅዱስ መጽሀፍ። አስተውሉ! መርምሩም! የእኛ ምግብ አይጥ፣ እባብ፣ አህያ፣ ውሻ ወይም ሌላ የረከሰ ምግብ አይደለም። እንጀራ ነው እንጅ።
:
፪."ሐዲስ ኪዳን!"
:
➊ኛ).የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ በኮከብ እየተመሩ ሄደው የእጅ መንሻ /ገጸበረከት/ ካቀረቡለት (ሰብዐ ሰገል) መካከል የሀበሻው ንጉሥ ባዜን ይገኛል።
:
መድኃኒታችን ሲወለድ መወለዱን በኮኮብ የገለጸላቸው ለእስራኤላዊያን ወይም ለዐረቦች አይደለም። ለሐበሾች እንጅ። ይሄን ክብር ማን አገኘው?
:
➋ኛ).ማኅደረ መለኮት እመብርሃን ድንግል ማርያም በስደቷ ጊዜ በሰላም ኢትዮጵያ ያረፈችባትና በአስራትነት የተሰጠቻት እንዲሁም በተደጋጋሚ በልጇ መስቀል የባረከቻት ቅድስት ሀገር ቅድስት ኢትዮጵያ
እንዴት ነው ወደዳችሁት? ከተመቻችሁ #share በማድረግ ለሌሎች አድርሱ ።
እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ
7 views04:53