Get Mystery Box with random crypto!

ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።

የቴሌግራም ቻናል አርማ dereje1678 — ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።
የቴሌግራም ቻናል አርማ dereje1678 — ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።
የሰርጥ አድራሻ: @dereje1678
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-16 04:23:14
2 views01:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 06:43:06 ቅዳሜ፡
ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡
የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር  ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡
 
ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡
በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡  
የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡
ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡
ዘፍ.6፥11-22
ዘፍ.7፥1-24
ዘፍ.8፥6-11
ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡
ምእመናን ሆይ፣ በአጠቃላይ ሥርዓተ ሕማሙን፤ ሰሙነ ሕማማት ብለው የተለየ ሥርዓት አውጥተው አባቶቻችን ተግተው ያቆዩልንን ሥርዓተ መላእክት ልንጠብቀውም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ የዕለታቱን ክብርና ስያሜ ከማወቅና ከመረዳት ጋር በዕለታቱ የታዘዙትን ሃየማኖታዊ ግዴታዎችን መወጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡
1 view03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 06:43:06
ቀዳም ሥዑር
1 view03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 18:49:49
ዕለተ አርብ 11:00
    አሥራ አንድ ሰዓት
    ============
የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ልውሰድ ብሎ ጲላጦስን ለመነ ጲላጦስም ፈቀደለት።
ጲላጦስ በፈቀደላቸው ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ የእጆቹን ችንካሮችና የእግሮችሁን ችንካሮች ነቅለው ከመስቀል አወርደው በትከሻቸው ተሸክመው ዮሴፍ በበፍታ ኒቆዲሞስ ሽቶ አምጥቶ በሰው ሥርዓት ሊገንዙ ሲሉ ዓይኖችሁ ተከፈቱ በሰው ሥርዓት ልትገንዙኝ ነውን? በሉ እንዲህ ብላችሁ ገንዙኝ አላቸው።
እነሱም እንዲህ ብለው ገነዙት

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጠ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን።

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ በዮርዳኖስ የተጠመቀ በመስቀል የተሰቀለ  አቤቱ ይቅር በለን ።

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት የማይለወጥ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሣ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ወጣ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ በጌትነት ይመጣል  አቤቱ ይቅር በለን።

ለአብ ምስጋና ይሁን
ለወልድም ምስጋና ይሁን
ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይሁን  ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን አሜን ይሁን ይሁን ይደረግልን  ልዩ ሦስት ሕያው እግዚአብሔር ሆይ አቤቱ ይቅር በለን።

ብለው ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት።
2 views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 10:50:28
2 views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 10:50:27 #የሰሙነ_ሕማማት_ዓርብ

➯ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያን ልዩ ቀን ነው፡፡ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁ ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሳ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግብር ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት፣ ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን፤ አሳዳጅ አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነው። ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡

#የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦

➯የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለ ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል። (ማቴ 27፡35)

#መልካሙ_ዓርብም_ይባላል፦

➯ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ሲያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ። በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይር ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርአያ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ ስላደረገውና በዕለተ ዓርብ በሞቱ ሕይወትን ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡

➯በዚህ ዕለትም ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱ ፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ ተአምራት አሳይቷል፦

1. ፀሐይ ጨልማለች
2. ጨረቃ ደም ሆናለች
3. ከዋክብት ረግፈዋል
4. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዷል
5. ምድር ተናወጣለች (ተንቀጥቅጣለች)
6. መቃብሮች ተከፍተዋል
7. ሙታን ተነስተዋል

➯በዓመት አንድ ጊዜ የምናገኘው ይህ ዕለት ቀራንዮን የምናስብበት ነገረ መስቀሉን የምናስተውልበት እንጂ ስለምድራዊ ኑሮአችን ስንባክን የምንውልበትና በዋዛ ፈዛዛ ልናሳልፈው አይገባም፡፡
1 view07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 09:27:13
የጌታችን የመዳኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ  13ቱ ሕማማተ መስቀል እነዝ ናቸው።

1.  በብረት ሃብል መጋፋው እስክጋጠመው
      ድረስ የዋልት መታሰሩን
2. ከአፍንጫው ደም እስክወጣው ድረስ .25
    ጊዜ. በጡንቻ መመታቱ
3. .65 ጊዜ . ከግንድ መጋጨቱ
4. .120 ጊዜ. ፍቱን መመታቱ
5.  .165 ጊዜ. በሽመል መደብደቡ
6.  .80 ጊዜ. ፅሙን መነጨቱ
7. .6666 ጊዜ. መገረፉ
8.  አክሊለ ሾክ በራሱ ላይ መድፋቱ
9. .136 ጊዜ. በምድር ላይ መውደቁ

10.  ሳዶር ፥ አላዶር ፥ ዳናት ፥ አዴራ ፥ ሮዳስ
        በተባሉ በሃምስቱ (5) ቅንዋተ ችንካር
         መቸንከሩ
11.  መራራ አሞትን መጠጣቱ
12.  መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ
13.  በመስቀል ላይ መሰቀሉን ናቸው።

እነዝ አሥራ ሦስትቱ ሕማማተ መስቀል አምላካችን መድኃኔዓለም የተቀበላቸው
መከራዎች ናቸው በቸርነቱና በምረቱ ብዛት እንደ በደላችን ሳይሆን እንደ ይቅርታ ብዛቱ ይቅር ይበለን ይማረን አሜን።
2 views06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 20:49:48 አርብ የሚነበቡና የሚጸለዩ ምንባባት
ኤር.8፥17-22
ኤር.9፥1-3
ሕዝ.36፥16-23
ጸሎተ ሰምዖን አምዳዊ
መጽሐፈ ዲድስቅልያ
ድርሳን ዘአበዊነ ሐዋርያት
ሕዝ.22፥23-28
ድርሳን ዘዮሐንስ አፈወርቅ
ሃ.አበ.ይቤ ቅዱስ ኤራቅሊስ48፥1-7
ሃ.አበ.ዘአባ ዮሐንስ107፥27-28
ሃ.አበ.ዘአቡነ አባ ዘካርያስ 108፥1፣12-15
ኤር.9፥7-11
ሕዝ.21፥28-32
ኢሳ.27፥11-15
ዘዳግ.8፥18-19
ዘዳግ.9፥1-24
ኢሳ፥1፥2-9
ኢሳ.33፥5-22.
ኤር.22፥29-30
ኤር.23፥1-6
ሰቆቃወ ኤርሚያስ7፥1-5
ኤር.12፥1-8
ጥበብ.2፥13-23
ሚክ.7፥2-4.
አሞ.2፥4-16
አሞ.3፥1-7.
ሆሴ.10፥5-9
ሃ.አበ.ይቤ ቅዱስ እለስክንድሮስ 16፥2-10
እመልእክተ ሲኖዲቆን ዘአባ ዘካርያስ108፥24-32.
ተግሳጽ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅምንተ ንብል ኦ አኃዉ
ዘፍ.48፥1-19
ኢሳ.63፥1-9
ኢሳ.64፥1-4
ኢሳ.50፥4-9
ኢሳ.3፥9-15
ሃ.አበ.ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ 61፥4-13
እመልእክተ ሲኖዲቆን
ዘአባ ሱንትዮስ 110፥49
ዘኁል.21፥1-9
ኢሳ.53፥7-12
ኢሳ.12፥2-6
ኢሳ.50፥10-11
ኢሳ.51፥1-8
አሞ.88፥14
አሞ.9፥1-15
ሃ.አበ.ዘእመልእክተ ሲኖዲቆን ዘአባ ዲዮናሲዮስ 111፥11-13
ዘአባ ክርስቶዶሎስ 112፥11
ተግሳጽ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ስንክሳር መጋቢት ሃያ ሰባት
ኢያ.5፥10-12
ሩት.2፥11-14
ኤር.11፥18-23
ኤር.12፥1-13
ኢሳ.24፥1-23
ኢሳ.25፥1-12
ኢሳ.26፥1-17
ዘካ.14፥5-1
ኢዮ.16፥12-20
ሃይማኖት አበዉ 26፥11-21
ድርሳነ ማኅየዊ 27፥5-10
የማርያም ኃዘን
ዘፅአ.12፥1-14
ኢሳ.51፥9-23
ኢሳ.52፥1-16
ሶፎ.2፥5-15
ሶፎ.3፥1-8
ተግሳጽ ዘአቡነ አትናቴዎስ
ሰቆቃዎ ኤርሚያስ 3፥1-62
መኃልየ ሰለሞን 3፥20-24
ሃ.አበ.7፥30-31፣17፥5-8፣60፥30-34
2 views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 20:49:48 በመስቀል ላይ ሳለ ጌታችን ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ሁሉ ተፈጸመ አለ፤ (ማር. ፲፭፥፴፯)፤ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በፈቃዱ ለየ፡፡ አይሁድም እኒህ ሰዎች እንደተሰቀሉ አይደሩ፤ ምክንያቱም ቀጣዩ ቀን ሰንበት ነውና ጭናቸውን ሰብረው ያወርዷቸው ዘንድ ጲላጦስን ጠየቁት፤ እርሱም ፈቀደላቸው፡፡ የሁለቱ ወንበዴዎች፤ ፈያታይ ዘየማንንና ፈያታይ ዘጸጋምን አብረው አወረዷቸው፤ ከጌታችን ዘንድ ቢቀርቡ ፈጽሞ ሞቶ አገኙት፤ በዚህም ጭኑን ሳይሰብሩት ቀሩ፡፡ ሌላው ግን የተመሰለው ምሳሌ ፍጻሜ ሲያገኝ ነው፤ የፋሲካውን በግ ‹‹አጥንቱን ከእርሱ አትስበሩ›› የተባለው አሁን ተፈጸመ፤(በዘፀ.፲፪፥፲)፡፡ ከጭፍሮቹም አንዱ ቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው እንዲል ከወታደሮቹ አንዱ የሆነው ለንጊኖስ የጌታችንን ጎን ቢወጋው ትኩስ ደምና ቀዝቃዛ ውኃ ፈሷል፡፡ ለንጊኖስ ጥንተ ታሪኩ አንድ ዐይኑ የጠፋ ሲሆን ጌታችን በተሰቀለበት ጊዜ ወደ ጫካ ሸሽቶ ርቆ ነበር፤ ምክንያቱም ከዚህ ሰው ሞት አልተባበርም በማለት ነው፡፡ አመሻሹ ላይ የአይሁድ አለቆች ሲመለሱ ከመንገድ አገኘቱ፤ስለምን ከመሢሑ ሞት አልተባበርክም አሉት? እርሱም ምንም ስላላገኘሁበት አላቸው፡፡ ከዚያም በኋላ እንደሕጋቸው እንደሚቀጡት ቢነግሩት እየሮጠ ሔዶ የጌታችንን ጎን ሲወጋው ደሙ በዐይኑ ላይ ፈሰሰ፤ ያን ጊዜ ዐይኑ በራለት፤ከጌታችን ጎን የፈሰሰው ደም እንደ  ቅርጽ ሆኖ በሁለት ወገን ደምና ውኃ ሆነ፡፡ ከጌታችንም የፈሰሰውን ትኩስ ደም መላእክት በጽዋ ቀድተው በዓለም ላይ ረጩት፤ ይህ መሠረት ሆኖ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን የሚታነጸው የጌታችን ደም የነጠበበት  ነው፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ›› ያለው (ሐዋ.፳፥፳፰)፡፡ ከጌታ ጎን የፈሰሰው ውኃ ደግሞ ምእመናን የልጅነት ጥምቀትን ስንጠመቅ ውኃውን ካህኑ ሲባርከው ማየ ገቦ ይሆናል፡፡
2 views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 20:49:48 የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት


በጲላጦስ ዘመን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለ ሰው ልጅ በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት፤ ትንቢቱም ይፈጸም ዘንድ መከራን ተቀበለ፤ ጲላጦስ በ፫ ሰዓት ይሰቅል ዘንድ ሲፈርድበትም፤ ‹‹መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ወጣ›› (ዮሐ.፲፱፥፲፯) የራስ ቅል ስፍራ ቀራንዮ-ጎልጎታ አዳም ዐጽም የተቀበረበት ቦታ ነበር፡፡ በዚያም የአዳም መቃብር የሆነች ዋሻ አለች፤ የመስቀሉንም እንጨት በዚያ በምድር መካከል አይሁዶች ተከሉት፡፡ የአዳም አጽም ቀድሞ ከአዳም ትውልዶች ሲተላለፍ ከኖኅ ደርሷል፤ ኖኅም ወደ መርከብ እንደታቦት አስገብቶት በኋላ መልከጼዴቅ ቀብሮታል፡፡ ጌታችንም ከአዳም የራስ ቅል በላይ ሊያድነው መስቀል ተሸከሞ ተንገላታ፤ አይሁዶችም የቀራንዮን ዳገት  እየገረፉ ከወደ ጫፍ አደረሱት፤ሁለቱንም እንጨት አመሳቅለው ዐይኖቹ እያዩ እጆቹንና እግሮቹን ቸነከሩት፤ በዕለተ ዐርብ ቀትር ፮ ሰዓት ላይም ተሰቀለ፡፡
ጌታችን የተሰቀለበት ሰዓት ፀሐይ በሰማይ መካከል በሆነ ጊዜ የጥላ መታየት በሚጠፋበት፤ ወደ ሰው ተረከዝም በሚገባበት ነበር፡፤ ከ፮ ሰዓት ጀምሮ እስከ ፱ ምድር ጨለመች፤ ፀሐይ፤ጨረቃ፤ከዋክብት ብርሃናቸውን ከለከሉ፤ ምክንያቱም የፈጣሪያቸውን ዕርቃኑን ይሸፍኑ ዘንድ ነበር፤ ‹‹ቀትርም በሆነ ጊዜ ፀሐይ ጨለመ፤ምድርም ሁሉ እስከ ፱ ሰዓት ድረስ  ጨለማ ሆነ›› ማር.፲፭፥፴፫፡፡
በ፱ ሰዓት በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ስለ ጌታችን በሰማይ ፫ት በምድር ፬ት ተአምራትን ሲያደርጉ አይቶ በእውነት አምላክ እንደሆነ አመነ፤ ‹‹አቤቱ በመንግሥት በመጣህ ጊዜ አስበኝ›› ባለ ጊዜ በግራ የተሰቀለው ዳክርስ ግን ‹‹እስቲ አምላክ ከሆነ እራሱን ያድን›› ብሎ ተዘባበተ፡፡ ፍያታዊ ዘየማን ግን ‹‹እኛስ በበደላችን ነው የተሰቀልን፤ እርሱ ግን ምንም ሳይበድል ነው፤ እንዴት በአምላክ ላይ ክፉ ነገርን ትናገራለህ›› ብሎ ገሰጸው ፤ፍያታዊ ዘየማንም ጌታችን በጌትነት መንበረ ጸባዖት(መንግሥት) ሆኖ ታየው፤እርሱንም አይቶ ‹‹ተዘከረኒ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ›› ቢለው ጌታችን ‹‹ዮም ትሄሉ ምስሌየ ውስተ ገነት›› ብሎ ደመ ማኅተሙን ሰጥቶታል፤ በኋላ ገነት ሲገባም መልአኩ አንተ ማነህ፤ አዳም ነህ፤ አብርሃም ወይንስ ይስሐቅ? እያለ ጠይቆታል፡፡ መልአኩ ሳያውቅ የጠየቀ ሆኖ አይደለም፤እንኳን በመጨረሻ የጸደቀ ፍያታዊ ቀርቶ በዘመናቸው የኖሩ ጻድቃንን ያውቃል፤ አዳምን ፤አብርሃምን፤ይስሐቅን ሳያውቅ ቀርቶም አይደለም፡፡ ነገር ግን ሊቃውንት ሲተረጉሙት ‹‹አዳም ነህ›› ማለቱ የአዳምን ያህል ሥራ አለህን? አብርሃም ነህ ሲለው ደግሞ የአብርሃምን ያህል ሥራ አለህን? ለማለት ነው፡፡ ‹‹በጌታችን ኢየሱስ መስቀል አጠገብም እናቱ፤ የእናቱም እኅት፤ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፤መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር›› (ዮሐ.፲፱፥፳፭) ‹‹እነርሱም ማርያም መግደላዊት፤ የታናሹ ያዕቆብ እና የዮሳ እናት ማርያም፤ የዘብዴዎስም የልጆቹ እናት ሰሎሜም ነበሩ›› (ማር.፲፭፥፵)፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ከተናገራቸው የአደራ ቃላት አንዱ እመቤታችን ለቅዱስ ዮሐንስ መሰጠቷ ነው፤ ለወዳጁ ዮሐንስ ከስጦታ ሁሉ ስጦታ የሆነች እናቱን እናት ትሁንህ ብሎ ሰጠው፤‹‹እነኋት እናትህ፤ እነሆ ልጅሽ›› (ዮሐ.፲፱፥፳፮)፡፡ በኋላ ወደ ቤቱ ወስዷት ፲፭ ዓመት ኖራለች፤ በዚህም የዮሐንስ ቤት በአቢዳራ ቤት ተመስላለች፤እመቤታችንም የሚያጽናናትን ወዳጁ ዮሐንስን ሰጥቷታል፡፡ የእመቤታችን ለዮሐንስ መሰጠት ቀድሞ በሙሴ አንጻር ጽላቷ ለሕዝቡ ሁሉ እንደተሰጠች፤በዮሐንስ አንጻርም እመቤታችን ለሁላችን ለምእመናን ተሰጥታናለች፡፡
፱ ሰዓት በሆነ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ፤አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ›› ብሎ በታላቅ ቃል ተናገረ፤(ማር.፲፭፥፴፬)፡፡ በዚያም ቆመው የነበሩት ‹‹አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ፤›› የሚለውን ድምጽ የሰሙ ኤልያስን ይጣራል እያሉ አሙት፤ ክህደትንም ተናገሩ፤ ያንጊዜ አንዱ ወታደር ሮጦ ሆምጣጤ የመላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበርና  በሰፍነግ መልቶ በሂሶጽም አድርጎ በአፉ ውስጥ ጨመረለት፡፡
2 views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ