Get Mystery Box with random crypto!

ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።

የቴሌግራም ቻናል አርማ dereje1678 — ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።
የቴሌግራም ቻናል አርማ dereje1678 — ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።
የሰርጥ አድራሻ: @dereje1678
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-14 16:00:21 ነው። የልዑል ባሮች ዓለም ላይ ሁሉ ከልዑል ዘንድ
በይሁንታው ያፀደቀውን ሕግጋተ ሥላሴ አፅንተው ብርሃናዊ
አገዛዛቸው ሲሰፍን ያኔ ብቻ ነው የልዑል የቁጣ እጆች
ወደሰገባቸው የሚመለሱት። በምትኩ የምሕረት የበረከት
የፍቅር የደስታ የብልፅግና የጤና የረጅም እድሜ በረከቶቹ
ሁሉ መፍሰስ የሚጀምሩት። ለምሕረት ያስቀራቸውን
የወደዳቸውን ያከበራቸውን የሚጠግንበት የሚያስደስትበት
የሚያከብርበት ወቅት ይሆናል። በፍቅር እንባቸው ከልብ
በመነጨ ምስጋናቸው በፊቱ በደስታ ይቀርባሉና ምስጋናቸው
ለልዑልም ለድንግልም ለሊቃነ መላእክትም ለቅዱሳንም
ለሰማዕታት ሐዋሪያት ነቢያትም እንደማያቋርጥ ጅረት
ይፈሳል። እሱም እናታችን ድንግልም በረከታቸውን
ያለማቋረጥ በልጆቻቸው ላይ ያፈሱታል። እውነቱ ይህ ብቻ
ነው። ፈላስፎችህም ስለቤተክርስቲያናችን እንቶ ፈንቶ
የአሮጊቶችን ተረት መሰል እየፃፉ ቢያደነቁሩህም ራሳቸው
ለሠሩት አመፅ ብርቱ እዳ ከፋይ ናቸው።
ወገኖቼ!! ከዚህ በታች የሚሰፍረው የቅጣት ዓይነትና ምንነት
ሲሆን እንደበፊቱ መልእክቶች አገላለፅ ጥቅል ትእዛዝ
ሳይሆን፤ የአሁኑ ብርቱ የቅጣት ትእዛዝ በመሆኑ በየደረጃው
የሚከናወነውን የሚገልፅ ምንስ ውጤት እንዲመጣ
እንደሚፈለግም የሚያረጋግጥ ነው። ቅጣቱ የሚያርፍባቸው
እንደግለሰብ፤ እንደመሪ፣ እንደ ቡድን፣ እንደማህበረሰብ፣
እንደድርጅት፣ እንደ ተቋማት፣ እንደጎሳ፣ እንደብሄር እንደ
ሕዝብ፣ እንደአገር፣ እንደአሕጉር በጥቅሉ ሁሉም በምድራችን
ላይ ያለ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ሰብአዊ ፍጡር
ሁሉ በመጪው ቁጣ የሚጎበኝ ነው። ለምሕረት የታሰበ
ቀድሞም የተመረጠ በግንባሩም ምልክት የተደረገበት ብቻ
ነፃና አንዳች የሚነካው የሌለ ሲሆን እንዲሁም በየትኛውም
አገር ውስጥ ያለ የዋህ ቅን ደግ እግዚአብሔር በወሰነው
መሰረት የሚሰበሰብበት የሚታረምበት በቅጣት
የሚመለስበት እርምጃም ይወሰዳል። ከእንግዲህ ዓለማችን
አሁን ባለችበት የጨለማ ሕይወት፤ የዲያብሎስ የንግሥና
ዘመናት አትቀጥልም። እሱም ለሺዎች ዘመናት የዘራው
የአመጽ፣ የጥፋት፣ የኃጢአት አዝመራውም ከነአለቃና
ምንዝሮቹ፤ በመልከ ብዙ ቅርጽ ምድሪቱን ከከድኑት ሕዝቦቹ
ጋር በእሳት ማዕበል ይጠረጋል።

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 8 ገፅ37-42 ካለው ተቀንጭቦ የተወሰደ
3 views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 16:00:21 ዘንድ በዙሪያው ካሉ ሊቃነ መላእከቶች ራሱን ሰወረ። በወቅቱ
ከከበሩት መላእክትም በክብሩም በሥልጣኑም ከልዑል
ቀጥሎ ይታይ የነበረው ሳጥናኤል ነበር። ልዑል ራሱን
ሲሰውር ሁሉም ተደናገጡ ፈጣሪያችን ማነው ወዴትስ ሄደ
ብለው ታወኩ። ሳጥናኤል ቀድሞም በልቡ ሥልጣንን
እነጥቃለሁ ብሎ ሃሳብ በልቡናው ያሳደረ በመሆኑ፤
ከመላእክቱም በከፍታ ያለ በመሆኑ መልስ ሰጪ ሆኖ
በመቅረብ እኔ ነኝ አምላካችሁ ብሎ መለሰላቸው። በዚህ
ወቅት ከከበሩ መላዕክት አንዱ የሆነው ገብርኤል
የሳጥናኤልን ድርጊት በመቃወም እሱን አትስሙት እሱም
እኛም የእግዚአብሔር ፍጡሮች ነን፤ ስለዚህ አምላካችን
ተገልጦ እስከሚረከበን ድረስ ባለንበት ፀንተን እንቁም
አላቸው። ብዙም ሳይቆይ ልዑል ራሱን ገለጠላቸው።
ሳጥናኤልና የተከተሉት ተፈረደባቸው። ተዋጉም ለውርደት
ለጥፋት ለፍርድ ለሰው ልጅ ፈተና ይሆኑ ዘንድ ወደምድር
ተጣሉ። ዛሬ እንደምናየው የሰውን ዘር በሙሉ ለማለት
በሚያስችል ቁጥር በቁጥጥራቸው ሥር አድርገው
የፈቃዳቸው ተገዢ አድርገውታል።
ዛሬም ለመጣው ፍርድና ቅጣት ማረፊያ እንዲሆን
አድርገውታል። በጊዜውም አለጊዜውም እንደ ሊቀመላእክት
ቅዱስ ገብርኤል ፀንቶ መቆም ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ሁሉ
የምሰነዝረው ምክር ነው። እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦች
ስንደክም ኃይለኞች ነን። በድካማችን የልዑል ጥበብ ነውና
አምላካችን ሥራው ይበረታል። በዚያን ጊዜም የእውሮች
ዐይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል በዚያን ጊዜ
አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፤ የዲዳም ምላስ ይዘምራል፤
በምድረበዳ ውኃ በበረሃም ፈሳሽ ይፈልቃልና፤ ደረቂቱ ምድር
ኩሬ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች። ቀበሮ
የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸንበቆ ደንገልም ይሆንበታል።
በዚያም ጎዳና መንገድ ይሆናል። እርሱም የተቀደሰ መንገድ
ይባላል። ንፁሃንም ያልሆኑ አያልፉበትም፤ አንበሳም
አይኖርበትም ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም ከዚያም
አይገኙም የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ፤ እግዚአብሔር
የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ እየዘመሩም ወደ ፅዮን ይመጣሉ፤
የዘለዓለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል። ሐሤትንና ደስታን
ያገኛሉ። ሃዘንና ትካዜ ይሸሻሉ።
ትንቢተ ኢሳይያስ ፡ 35 ፡5–10
ወገኔ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚጠብቅህ ከላይ ያየኸው
ቃል ነው።
ስማ! የአዳም ዘር አድምጥ! ልብ ብለህ አድምጥ! ላንዴም
ለመጨረሻ ጆሮህን ከፍተህ አድምጥ!
የሠራዊት ሁሉ ጌታ! የፍጥረት ሁሉ ጌታ! የነበረው ያለው
አልፋና ኦሜጋ የሆነው የሰማዩም የምድሩም ጌታ! የሌለውን
እንዲኖር ሕልው የሚያደርግ! ያለውን ወደሌለነት የሚለውጥ!
ከነበረ ወደአልነበረ፤ ከአልነበረ ወደነበረ የሚለውጥ ሁሉን
ቻይ አምሳያም አኳያም የሌለው ሁሉም በእጁ የሆነ ኃያል
ጌታ!! መጣሁብህ ይልሃል!!
በቁጣው የነደደው ልዑል!! እንደእቶን እሳት በታላቅ ቁጣ
እየጤሰ ያለው የሰራዊት ጌታ ደረስኩ ይልሃል!! እንግዲህ
ወገብህን ታጥቀህ ጠብቀኝ ፡ እኔው ፈጥሬሃለሁ፤ እኔው
አኑሬሃለሁ ከነከረፋው ምድርንም ሰማይን ካጠነባው
ኃጢአትህ ጋር መሽከሜ አንሶ እኔኑ ወጋህ! ስለሰው
ያፈሰስኩትን ደሜን ረጋገጥህ! በደሜ ተንቦጫረቅህ!
የተወጋው ጎኔን፤ የተቸነከረው እጅና እግሬን መልሰህ ወጋህ!
ከከፉት አይሁዶችም በላይ ሆንክ! በብዙ እጥፍም በለጥህ!
እኔው በፈጠርኩት ነገር ግን እኔን ሊዋጋ እኔንም ሊወርስ
ያላፈረውን፤ ለታላቁ ቁጣዬና ፍርዴ የጣልኩትን የቀደመውን
እባብ ዲያብሎስን እነገስህ አከበርህ አመንክ ታመንክበት
ያዘዘህን ሁሉ ፈፃሚ ሆንክ! በፍፁም ልብህ የሰራሁህን
የወደድኩህን የሞትኩልህን የፍቅር እጄን የዘረጋሁልህን
የክብሬ ወራሽ የስሜ አወዳሽ ቀዳሽ ያልኩህን አንተን ካድከኝ!
ፍፁም ጠላኸኝ ዘመትክብኝ በታላቁ ቅናቴም አነደድከኝ
ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ ባለተከሰተ ትእቢትህ ክህደትህ
ፌዝህ ንቀትህ እስከዛሬም ያልታየውን የቅናት ቁጣዬን
አነደድከው!! እንግዲህ ሁሉን አዘጋጅተህ የለ? /ሚሳየሉ ጀቱ
ኒኩለሩ፤ የጦር መርከቡ ጠመንጃው ታንኩ፤ ኬሚካሉ አጥቂ
ሳተላይቱ ምንም የቀረህ የለም ጧትም ማታም እሱኑ
ስታመርት ትወላለህ ታድራለህ! ልትዋጋ ተለማምደሃል
ተዘጋጅተሃል / ወገብህን ትጥቅህን አጥብቀህ ጠብቀኝ!!
የምጠርግህ የምባላው እሳት በቅናቴ ቁጣ እንደጢስ
የማተንህ የሰራዊት ሁሉ ጌታ መጣሁብህ!! ይላል
እግዚአብሔር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ!!
ተመልከት ወገኔ! እንግዲህ አደመጥከው አይደል፤ መጣ
ኃያሉ ጌታ፤ እኛን ስትፈጭ ስትቆላ፤ ነበርክ፤ ማንም
ያልመከተህ ነበርክ፤ መግቢያ መውጫ ያሳጣኸን እንልሰው
እንቀምሰው ያሳጣኸን በገዛ አባታችን ንብረት ሀብት አንተ
አዛዥ ናዛዥ እኛ እስረኞችህ ዘወትር መጫወቻህ ነበርን።
ውርደትን መናቅን ማሰደድ መንከራተትን መሞት መታሰርን
መቀጥቀጥን እንደዘወትር ቀለብ የሰፈርክልን የልዑል ባሮች /
ልጆች/ እኛ ነበርን። ዛሬ የሰፈርከውን በትእቢትህ በንቀትህ
በማንአለብኝነት የዘራኸውን ሊያሳጭድህ ሊያስቅምህ፣ አስር
እጥፍ ብድራትህን ሊከፍልህ መጣለህ! ያውም በሙላት!
እንደብርቱ ማዕበልና እንደሚንተከተክ እሳተገሞራ
እንደሚገተለተለው ጭስ ጢሶ መጣብህ!! ምን ይባላል
ተቀብለው!! ስለእናንተ በእውነት እኔንም አስጨነቀኝ። መፍቻ
የሌለው ጉዳይ!!
ይህ ስምንተኛ መልእክት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሊያፀና
እንደወጣ ሁሉ የመጨረሻው ሰዓት ላይ በመደረሱ ለተሰናባቹ
የጠፋ ትውልድ የሚፈስበትን የእሳት ማዕበል ሰይፍ
እንዲያውቀው ለማድረግም ነው። ኢላማቸውንም ለማሳወቅ
ነው። የመነሻ ጊዜአቸውንም የሚገለፅበት ነው። አሁን ያለው
ጅማሮ የአገራችንም ሆነ የዓለም ጥፋት ብዙም ትርጉም
ያለው አይደለም። ከተዘጋጀልህ ብርቱና ህሊና ከሚሸከመው
በላይ የሆነ ጠረጋ እስከ አሁን ያየኸው ኢምንት ነው።
እንዲያውም ሰላም ነው የሚያስብል ነው። ከላይ ሰማኸው
አይደል! ቃል በቃል ነው የልዑልን ታላቅ ቁጣ ያሰፈርኩልህ።
ወገኖቼ! ቁጣው በሙሉ ኃይሉ መፍሰስ ከጀመረ፤
የሚያስቆመው ምንም ኃይል አይኖርም በአንድ ነገር ብቻ
ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል። ልዑል እንዳሰበው፤
ሀ/በመጀመሪያ በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ባሉ ሀገሮች ሁሉ ላይ
የቀባቸው የመረጣቸው የአከበራቸው ታማኝ አገልጋዮቹ
መንበረ ሥልጣኑን መጨበጥ አለባቸው። ያውም ተለምነው
ደጅ ተጠንተው በብዙ እንባና ጩኸት ተወትውተው፤
ይሁንታንም ከልዑል ተቀብለው (ከድንግልም ተባርከው
ሲረከቡና እነሱም ለቀረው ሕዝብ ከታላቁ ቁጣ ላመለጠው
ሕዝበ ክርስቲያን የልዑል ቁጣ እንዲበርድ ልመናና ምልጃ
ሲያቀርቡ ብቻ፤ ያኔ የአንደኛው ሰይፍ /የልዑል ሰይፍ/
ከእርምጃው መቀዝቀዝ ይጀምራል ይቆማል አላልኩም
ከከፍታው ወደዝቅታው እንደሁኔታው ይቀንሳል። ይህም
ማለት አበቃ ማለት አይደለም ሁለተኛው ሰይፍ ይጀምራል።
ይህ ሰይፍ የታመኑት አገልጋዮቹ ሰይፍ ሲሆን በመላው ዓለም
የልዑል አገዛዝ እስኪሰፍን ድረስ እርምጃው የሚቀጥል
ይሆናል። እግዚአብሔር ባሮቹን በኃይል ያስታጥቃል። የዚህን
ዘመን ጥበብ እውቀት የዲያብሎስን የዘመናት ዝግጅት ሁለት
ሶስተኛውን እጅ በልዑል ቀጥተኛ እርምጃ ይደመሰሳል።
ቀሪውን አንድ አራተኛ ለባሮቹ የሚተው የማጽዳት እርምጃ
3 views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 16:00:20 ራስን_ማስመለከና_የውድቀት_መንገዱ

-ባሳለፍነው የጥፋት ዘመን ያሳለፍነው የአምልኮ ሁኔታችን
እጅግ የጠፋ ነበር። በብዙ ንግግሬ እንደተረዳችሁት ቀደምት
አባቶቻችን አምልኮታቸው በእውነትና በመንፈስ ነበር።
ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አምላካቸውን ያከብሩና ያስመልኩ
ነበር።
ዛሬስ? ዛሬ ብዙ ጳጳሳት ካህናት ዲያቆናት አገልጋዮች
ራሳቸውን የሚያስመልኩ ፡ የከበሬታ ወንበር የሚፈልጉ
ራሳቸውን ብቻ የሚያሰማሩ የወፈሩ በጎችን አርደው የሚበሉ
የከሱትን የሚጠሉ የሚገፉ የሚያሳድዱ ሆነው ተገኝተዋል።
ያውም ክርስቲያን ነን ብለው ካባውን ያጠለቁ ናቸው። ፈጣሪ
አምላካቸውን ከልባቸው ክደው ሆዳቸውን አንግሰው
ዲያብሎስን በልባቸው ተክለው የሥጋ ትርፋቸውን አምላክ
አድርገው ይመላለሳሉ። በአፋቸው ግን የከበረ ስሙን ለክፉ
ሥራቸው ሁሉ መሸፈኛ ያደርጉታል።
ወገኖቼ እንደተዋህዶ ክርስቲያን የሥጋ ስብእናችንን ብቻ
ገንብተን፤ ቤተ እምነታችን ያላስጨበጠችንን ክቡር
የእግዚአብሔር ቃል ያልተናገረንን በሕይወታችን እንግሰን
እንዴት ክርስቲያን እንሆናለን : ራሳችንን ለተለያዩ ክፋቶችና
ሃጢያቶች ካስገዛን እንዴት የልዑል ልጆች እንሆናለን?
ራስን መውደድ! ለሥጋ ትርፍ ብቻ መድከም! መናቅ ትእቢት
ማን አለብኝነት ጭካኔ ውሸታምነት ዘራፊነት እግዚአብሔርን
አለመፍራት አንግሰን የምንመላለስ ከሆነ ራሳችንና
የለበስነውን ሥጋ አመለክን እንጂ ለልዑል አይደለም ራሳችንን
ያስገዛነው።
ስለእምነት ስናነሳ እጅግ ወሳኝ የሆነውን ርእስ ማየታችን
ስለሚሆን በመጠኑ ዳስሼ አልፌዋለሁ። ምክንያቱም በዚህ
ጠባብ ሥፍራ ለትምህርት የታሰበ አይደለም መልእክት
ለማድረስ ብቻ እንጂ!
ስለእምነት በልዑል ቃል በእብራውያን በምእራፍ 11
የተገለፀውን በሙሉ አንብቡት።
የተዋህዶ አርበኞች የእግዚአብሔር ሕዝቦች!!
እነሆ እግዚአብሔር የሚገሥፀው ሰው ምስጉን ነው፤ ስለዚህ
ሁሉን የሚችለውን የአምላክህን ተግሳጽ አትናቅ! እርሱ
ይሰብራል ይጠግንማል፤ ያቆስላል እጆቹም ይፈውሳሉ ፡
በስድስት ክፉ ነገር ውስጥ ያድንሃል፤ በሰባትም ውስጥ ክፋት
አትነካህም ፡ በራብ ጊዜ ከሞት ፡ በሰልፍም ከሰይፍ እጅ
ያድንሃል ፡ ከምላስ ጅራፍ ትፈወሳለህ ፡ ጥፋትም ሲመጣ
አትፈራም! በጥፋትና በራብ ላይ ትስቃለህ ፡ ከምድረበዳ
ከአራዊትም አትፈራም ፡ ቃል ኪዳንህ ከምድረ በዳ ድንጋይ
ጋር ይሆናል፤ የምድረ በዳም አራዊት ከአንተ ጋር
ይስማማሉና፤ ድንኳንህም በሰላም እንዲሆን ታውቃለህ ፡
በረትህን ትጎበኛለህ አንዳችም አይጎድልብህም ዘርህም
ታላቅ እንዲሆን፤ ትውልድህም እንደ ምድር ሳር እንዲሆን
ታውቃለህ፤ በወራቱ የእህል ነዶ ወደ አውድማ እንዲገባ፤
በረጅም እድሜ ወደ መቃብር ትገባለህ። እነሆ ይህችን
መርምረን የሰማነውም ይህ ነው። ይላል የልዑል ቃል።
መጽሐፈ ኢዮብ ምእራፍ 5 ፡ 17 –27
ወገኖቼ የእግዚአብሔር ምርጦች አይዟችሁ! እንባችሁ
ይታበሳል፤ ቁስላችሁ ይፈወሳል፤ ያለአባት ያለእናት
አይደላችሁም። የሰፈራችሁትን መከራ፤ ያለፋችሁበትን
የጨለማ ዓለም፤ ዲያብሎስ ያደረሰባችሁን እስር እንግልት
ማሳደድ ርሃብ ስቃይ ውርደት ሁሉም በልዑል ፊት በድንግል
ፊት በቁጭት ታስበዋል። ብድራቱን ይከፍላሉ፤ የሆነው ሁሉ
ለእናንተ ለበጎ ነው። አባታችሁም እናታችሁም ሁለቱም አሁን
ደርሰዋል። ከአጠገባችሁም ናቸው። እንደ ጥጃ የምትቦርቁበት
ዘመን እነሆ ከፊታችሁ ነው። ሁለመናችሁ ይፈወሳል።
ስለእናንተ ቅዱሳን መላእክት ሁሉ ይተጋሉ።
የጠላቶቻችሁን ጥፋት በመልካም ሥፍራ ሆናችሁ
ትመለከታላችሁ። ብድራታቸውን በሰፈሩት አስር እጥፍ
ሊሰፈርላቸው ነውና ታያላችሁ። ምድሪቱንም ትወርሳላችሁ።
ከምርኮውም ፍፁም ትጠግባላችሁ። ቀኑም ሌቱም፤
ምድሪቱም ማህፀኗም ስለእናንተ ያላቸውን ሁሉ ይሰጣሉ።
የተወደዳችሁ በእሳት የተፈተናችሁ እንቁ የልዑል ልጆች
ናቸሁ ። ተዋህዶ ኦርቶዶክስ አርበኞች እንዲሁም ባላችሁበት
ባእታችሁ በቅንነታችሁ፣ በየዋህነታችሁ፣ እግዚአብሔርን
በመፈለጋችሁ የታጎዳችሁ ሁሉ ዛሬ ታስባችኋል። አትፍሩ
አትደንግጡ።።
ወገኖቼ ይህንን ለእናንተ እናገር ዘንድ በዋናነት የታዘዝኩበት
ነው። ከእንግዲህ አትፍሩ አትደንግጡ ያለፈው መከራ
ትውስታው አያስበርግጋችሁ። ሁላችንም ከየወደቅንበት
ከታሰርንበት እንፈታለን እንነሳለን። ልዑል፣ ድንግል፣ ቅዱሳን
ሊቃነ መላእክት የጠላትን ምሽግ የትምከህታቸውን ክምር
የጥፋት እጃቸውን እርዝመት ሊቆራርጡት ሊያጠፉት
ሊደመስሱት በጠላቶቻችን አናት ላይ ቆመዋል። ለአንዴም
ለሁሌም ወደገሃነማቸው ይወርዳሉ። ምን ልበላችሁ ወገኖቼ፣
ወንድም እህቶቼ፣ አባት እናቶቼ፣ እንዲሁም ልጆቼ፤ ድንቅ
ናቸሁ። ለእናንተ ልዑል ያዘጋጀላችሁን ድንግል ያሰናዳችውን
ብትመለከቱት ይህ ሁሉ ለእኔ፤ ማን ስለሆንኩ ምንስ ያህል
ፈጣሪም ድንግልም ቢወዱኝ ነው ብላችሁ ከመደመማችሁ
የተነሳ የደስታ እምባችሁ የማትገቱት እንዲሆን ልግለፅላችሁ
እወዳለሁ።
የዛሬው የጠፉ ትውልዶች በተለይም ወጣቶች፤ ተምረዋል
የሚባሉ ምሁሮች፤ አገር እንመራለን ብለው በሥልጣኑ ዙሪያ
የተኮለኮሉ ሰዎች፣ ጠመንጃ የጨበጡ የተለያዩ ኃይሎች
ሁሉንም ስናያቸው በምን ጎዳና ላይ ናቸው፤ ምንስ ጥፋት
ውስጥ ወድቀዋል ስንል ብናነሳው እጅግ ብዙ ነው።
ዛሬ ምንዝርና፣ ሌብነት፣ ዘረኝት፤ ውሸት፣ አምልኮ ባእድ፣
ሱሰኝነት፤ ጫት ቃሚነት፣ ሰካራምነት ጨካኝነት፣ ክህደት ፡
ትእቢተኝት፣ ነፍሰ ገዳይነት፣ ሰነፍነት፣ ተብታቢነት፤ አታላይነት፣
የአብዛኛው ትውልድ መገለጫ ሆኗል።
እውነት እምነት ጠፍቶ በምትኩ የውሸት እምነት ነግሷል።
በአገራችን የነገሱት ዘረኝነት በራሱም በመንግሥት ተብዬው
በመሆኑ አንዱ አንዱን እንዲጠላና በጠላትነት እንዲተያይ
ተደርጓል። እስልምና ምንፍቅና ኩትልክና
ዋቄ ፈታ ጣኦት አምላኪ፣ ተብታቢ፣ መተተኛ፣ ጠንቋይ
አስጠንቋይ፣ ውቃቢ የመሳሰሉ ትወልዱን ይዘውት የጠፉ
ሆነዋል።
ዛሬ በምናየው መንግሥታዊ አርቴፊሻል ለውጥ የሚመጣ
አንዳች ነገር የለም። እግዚአብሔር ያለው ቀድሞም
የተናገረው ፍርዱንም ያሳወቀው ኢትዮጵያ ወደትንሳኤው
እንድትሻገር ነው። አብሯት የሚሻገሩትም ዛሬ በእምነቱ ስም
የሚነግዱትን ቀጣፊዎችን ተኩላዎችን አይደለም። ራሱ
ኮትኩቶ ደክሞ በእሳት አንጥሮ ተሸክሞ በማእበሉ ሁሉ
ያሳለፋቸውን አገልጋይ ባሮቹን እንጂ!
ወገኖቼ!! ልትረዱት ይገባል፤ ልታደምጡም፤ ልትዘጋጁም
ይገባችኋል። የምድሪቱ ወራሾች የክብሩ ቀዳሽ አወዳሾች
እናንተ የልዑል ማሕተም ያረፈባችሁ ናችሁ።
ቤተ ክርስቲያናችን የተዋህዶ ቤታችን እግዚአብሔር
በወደዳቸው በአከበራቸው ባፀደቃቸው ልጆቹ እንደገና
የውርደትና የጥፋት ካባዋን አውልቃ እንደ አዲስ ትነሳለች
እንጂ!! ሌባ ተኩላ የበግ ለምድ ለብሶ ሁሌም የሚፈነጭባት
አትሆንም። አመጽን፤ ማፍረስን በቤተ እግዚአብሔር /
በተዋህዶ/ ላይ ሲፈጽም ሲያስፈጽም የነበረ የአገርም
የውጪም ጠላት ሁሉ ለአንዴም ለሁሌም እንዳይነሳ ሆኖ
በእሳት ባሕር ይከደናል።
የተዋህዶ አርበኞች ከዚህ በታች ያሰፈርኩት ሁሌም
የምትሰሙት ምሳሌ ነውና እንደልዑል ታማኝ አገልጋይ ሊቀ
መላእክት ገብርኤል ፀንተን እንቁም!
በአንድ ወቅት ልዑል ቅዱሳን መላእክትን ፅናት ይመለከት
3 views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 08:36:37
4 views05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 08:36:36 ግዜው አልቋል ግዜው አውን የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልክት ወደ አፈፃፀምና ወደ ተግብራ የተወሰነበት ነው ስማ የአዳም ዘር።አድምጥ ከኢትዮጵያ የዓለም ብራናዊ መንግስት ከታላቁ ንጉስ ቴድሮስ ነብይ ካህን መልካሙ እረኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሸናፊ እምነት አርበኛ ፡በስላሴ ፍቃድና ትህዛዝ የወጣ አስረኛ መልእክት።በኢትዮጵያ ምድር ለአገራችን እጅግ የከበደ መከራን ላደረሱ ዛሬም ነግሰው ላሉ የጥፋት አለቆች ፡- መንግስትና ካቢኔው፣ መንግስትና በተዋረድ የተከላቸው አለቃና ምንዝሮች ፣ ወታደሮች ፖሊሶች የፀጥታ ሠራተኞች ፣ የየክልል መሪዎች ካቢኒዎች ምክር ቤቶች ሁሉም እንድሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተወካዮች በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ መንግስት አምባሳደሮች ከነ ድፕሎማቶቻቸው በዚህ በየሁሉም ክልል ለኢትዮጵያ ጥፋት የሰሩ ልዩ ኃይል ሚሊሻ በመንግስት ተብዮው በስውር የሚደገፉ ዘር አጥፊዎች ዘረኞች ሁሉም በተለይ በኦሮሚያ በሚባል ክልል ውስጥ ለፈሰሰው ንፁህ ደም ለተጨፈጨፈው የእግዚአብሔር ድሃ ሁሉም ህዝብ የተሳተፈ ብቻ አይደለም በሃሳብ የደገፈ ዳር ቆሞ የተመለከተ ሁሉ ተጠያቂና እሱ ሲፈጽመው ሲያርድ ሲገድል ሲጨፈጭፍ እንዳስደሰተው ሁሉ ሞትን እየለመነ በምድር ባልታየ ስቃይ ተፈጭቶ የለመነውን ሞት እንደ ስጦጣ ያገኛል፡፡ በኦሮሚያ ምድር ወቄ ፈናን ዘረኛ መ>ና?ፍ?ቅ እስላም አስመሳይ ኦርቶዶክስ ዘራፊ ሌባ ትዕቢተኛ ሁሉም ባለውቃቢና ተከታዮቻቸው ጠንቋዮች ተብታቢዎች ሰላቢዎች አጋንት ጎታቾች ሁሉ ምንም ዘር ሳይቀርላቸው ከኢትዮጵያ ምድር በታላቅ እሳት ይጠረጋሉ፡፡ በውጭ ተቀምጠው ይህንኑ እርኩሰት ሲደግፉ ሲያስተባብሩ ሲመሩ ሲረዱ ያሉ ሁሉ ባሉበት ሀገር ታላቅ እሳት እንድበላቸው ተወስኖባቸዋል፡፡ ትእዛዙም ከጸባኦት ወጥቷል በፈጻሚዎች እጅ ደርሷል፡፡ ተፈጻሚም ይሆናል፡፡
የ #ኢትዮጵያ_የአለም_ብርሃን መልእክት #10 ገጽ 46 7/05/2015 ዓ.ም

የበለጠ ለመረዳትና ሁሉንም ለማድመጥና ለማንበብ


https://t.me/rayeyohanes20/329520
https://bit.ly/መልዕክት_10_ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_pdf
http://bit.ly/መልእክት_10_ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_በድምፅ
3 views05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 20:44:23

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፨

~ የካቲት 6 | ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት (ባለ ሽቱዋ ማርያም)

 (ዘክሯት፤ በስሟ ተማፀኑ)   
  ๏◦๏◦๏     
በዚህችም ቀን ጌታን ሽቱ ለቀባችው ማርያም የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው። ይችም ቅድስት አስቀድማ ኑሮዋን በዝሙት ያሳለፈች ኃጢአተኛ ነበረች።

እርሷም ጎልማሶችን ወደርሷ ትማርካቸው ዘንድ በየራሱ በሆነ ሽልማትና ጌጥ ትሸለም ነበር።

በአንዲትም ዕለት እንደ ልማድዋ ተሸልማ አጊጣ ሽቱም ተቀብታ ፊቷን በመስታዋት ተመለከተች።

የጉንጯ ቅላትና ደም ግባቷ የዓይኗም ወገግታና ጥራት ማማሩን አይታ እያደነቀች አንድ ሰዓት ያህል ቆየች ከዚህም በኋላ በጎ ኀሳብ በላይዋ መጣ ሞትንና የዚህን ዓለም ማለፍ አሰበች።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስም ኃጢአተኞችን እንደሚቀበልና ኃጢኣትንም እንደሚአስተሰርይ ሰምታ ገንዘቧን ወስዳ የአልባስጥሮስን ሽቱ ገዝታ በስምዖን ዘለምጽ ቤት ለምሳ ተቀምጦ ሳለ ወደ ጌታችን ሔደች።

ከእግሩ በታችም ሰግዳ ያንን ሽቱ ቀባችው እግሮቹን በዕንባዋ አጠበችውና በራስዋ ጠጉር ወለወለችው።

ጌታችንም የፍቅርዋን ጽናት አይቶ ኃጢኣቷን በደሏን ተወላት የመንግሥት ወንጌልም በሚሰበክበት ይህን ያደረገችውን እንዲአስቡ አዘዘ።
◦◍◦◍◦
4 views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 11:10:40 በወንድማችን ተክለ ኪዳን የተጻፈ፦
"ማን ያዉቃል የእግዚአብሔርን ሥራ?"

https://t.me/Ewnet1Nat/9929
4 views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 15:05:58
3 views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-10 15:05:57 ''ውሸታሙ እረኛ''

ውሸታሙ እረኛ
ሲያልፍ መንገደኛ
ቀበሮ መጣብኝ
በጎቼን በላብኝ
እያለ ዘወትር
ሲቀልድ ሲያስቸግር
በዚህ አድራጎቱ
ደግሞም በውሸቱ
ሁሉም ሰው ተማሮ
አንድ ቀን ቀበሮ
መጣና በድንገት
በጎቹን በላበት
ውሸታሙ እረኛ
ዘወትር ልማደኛ
ኡ ኡ እያለ ወጣ
የሚረዳው አጣ !

... #የሆኑ_ውሸታም_እረኞች_የመጨረሻ_እጣ_ፈንታ_ይኸው_ነው ።
3 views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 12:00:44 የአባ አምኃ ኢየሱስ ገብረዮሐንስ መደበኛና ድንገተኛ አገራዊ መልዕክቶች

መልዕክት ፩ https://t.me/christian930/2763

መልዕክት ፪ https://t.me/christian930/2764

መልዕክት ፫ https://t.me/christian930/2765

መልዕክት ፬ https://t.me/christian930/2766

መልዕክት ፭ https://t.me/christian930/3471

መልዕክት ፮ https://t.me/christian930/3487

PDF+Audio+Video ሁሉንም በአንድ ላይ ለማግኘት https://t.me/christian930/4289

ድንገተኛ መልዕክታት (በፅሑፍ) https://t.me/christian930/4290
8 views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ