Get Mystery Box with random crypto!

ዘንድ በዙሪያው ካሉ ሊቃነ መላእከቶች ራሱን ሰወረ። በወቅቱ ከከበሩት መላእክትም በክብሩም በሥልጣኑ | ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።

ዘንድ በዙሪያው ካሉ ሊቃነ መላእከቶች ራሱን ሰወረ። በወቅቱ
ከከበሩት መላእክትም በክብሩም በሥልጣኑም ከልዑል
ቀጥሎ ይታይ የነበረው ሳጥናኤል ነበር። ልዑል ራሱን
ሲሰውር ሁሉም ተደናገጡ ፈጣሪያችን ማነው ወዴትስ ሄደ
ብለው ታወኩ። ሳጥናኤል ቀድሞም በልቡ ሥልጣንን
እነጥቃለሁ ብሎ ሃሳብ በልቡናው ያሳደረ በመሆኑ፤
ከመላእክቱም በከፍታ ያለ በመሆኑ መልስ ሰጪ ሆኖ
በመቅረብ እኔ ነኝ አምላካችሁ ብሎ መለሰላቸው። በዚህ
ወቅት ከከበሩ መላዕክት አንዱ የሆነው ገብርኤል
የሳጥናኤልን ድርጊት በመቃወም እሱን አትስሙት እሱም
እኛም የእግዚአብሔር ፍጡሮች ነን፤ ስለዚህ አምላካችን
ተገልጦ እስከሚረከበን ድረስ ባለንበት ፀንተን እንቁም
አላቸው። ብዙም ሳይቆይ ልዑል ራሱን ገለጠላቸው።
ሳጥናኤልና የተከተሉት ተፈረደባቸው። ተዋጉም ለውርደት
ለጥፋት ለፍርድ ለሰው ልጅ ፈተና ይሆኑ ዘንድ ወደምድር
ተጣሉ። ዛሬ እንደምናየው የሰውን ዘር በሙሉ ለማለት
በሚያስችል ቁጥር በቁጥጥራቸው ሥር አድርገው
የፈቃዳቸው ተገዢ አድርገውታል።
ዛሬም ለመጣው ፍርድና ቅጣት ማረፊያ እንዲሆን
አድርገውታል። በጊዜውም አለጊዜውም እንደ ሊቀመላእክት
ቅዱስ ገብርኤል ፀንቶ መቆም ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ሁሉ
የምሰነዝረው ምክር ነው። እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦች
ስንደክም ኃይለኞች ነን። በድካማችን የልዑል ጥበብ ነውና
አምላካችን ሥራው ይበረታል። በዚያን ጊዜም የእውሮች
ዐይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል በዚያን ጊዜ
አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፤ የዲዳም ምላስ ይዘምራል፤
በምድረበዳ ውኃ በበረሃም ፈሳሽ ይፈልቃልና፤ ደረቂቱ ምድር
ኩሬ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች። ቀበሮ
የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸንበቆ ደንገልም ይሆንበታል።
በዚያም ጎዳና መንገድ ይሆናል። እርሱም የተቀደሰ መንገድ
ይባላል። ንፁሃንም ያልሆኑ አያልፉበትም፤ አንበሳም
አይኖርበትም ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም ከዚያም
አይገኙም የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ፤ እግዚአብሔር
የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ እየዘመሩም ወደ ፅዮን ይመጣሉ፤
የዘለዓለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል። ሐሤትንና ደስታን
ያገኛሉ። ሃዘንና ትካዜ ይሸሻሉ።
ትንቢተ ኢሳይያስ ፡ 35 ፡5–10
ወገኔ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚጠብቅህ ከላይ ያየኸው
ቃል ነው።
ስማ! የአዳም ዘር አድምጥ! ልብ ብለህ አድምጥ! ላንዴም
ለመጨረሻ ጆሮህን ከፍተህ አድምጥ!
የሠራዊት ሁሉ ጌታ! የፍጥረት ሁሉ ጌታ! የነበረው ያለው
አልፋና ኦሜጋ የሆነው የሰማዩም የምድሩም ጌታ! የሌለውን
እንዲኖር ሕልው የሚያደርግ! ያለውን ወደሌለነት የሚለውጥ!
ከነበረ ወደአልነበረ፤ ከአልነበረ ወደነበረ የሚለውጥ ሁሉን
ቻይ አምሳያም አኳያም የሌለው ሁሉም በእጁ የሆነ ኃያል
ጌታ!! መጣሁብህ ይልሃል!!
በቁጣው የነደደው ልዑል!! እንደእቶን እሳት በታላቅ ቁጣ
እየጤሰ ያለው የሰራዊት ጌታ ደረስኩ ይልሃል!! እንግዲህ
ወገብህን ታጥቀህ ጠብቀኝ ፡ እኔው ፈጥሬሃለሁ፤ እኔው
አኑሬሃለሁ ከነከረፋው ምድርንም ሰማይን ካጠነባው
ኃጢአትህ ጋር መሽከሜ አንሶ እኔኑ ወጋህ! ስለሰው
ያፈሰስኩትን ደሜን ረጋገጥህ! በደሜ ተንቦጫረቅህ!
የተወጋው ጎኔን፤ የተቸነከረው እጅና እግሬን መልሰህ ወጋህ!
ከከፉት አይሁዶችም በላይ ሆንክ! በብዙ እጥፍም በለጥህ!
እኔው በፈጠርኩት ነገር ግን እኔን ሊዋጋ እኔንም ሊወርስ
ያላፈረውን፤ ለታላቁ ቁጣዬና ፍርዴ የጣልኩትን የቀደመውን
እባብ ዲያብሎስን እነገስህ አከበርህ አመንክ ታመንክበት
ያዘዘህን ሁሉ ፈፃሚ ሆንክ! በፍፁም ልብህ የሰራሁህን
የወደድኩህን የሞትኩልህን የፍቅር እጄን የዘረጋሁልህን
የክብሬ ወራሽ የስሜ አወዳሽ ቀዳሽ ያልኩህን አንተን ካድከኝ!
ፍፁም ጠላኸኝ ዘመትክብኝ በታላቁ ቅናቴም አነደድከኝ
ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ ባለተከሰተ ትእቢትህ ክህደትህ
ፌዝህ ንቀትህ እስከዛሬም ያልታየውን የቅናት ቁጣዬን
አነደድከው!! እንግዲህ ሁሉን አዘጋጅተህ የለ? /ሚሳየሉ ጀቱ
ኒኩለሩ፤ የጦር መርከቡ ጠመንጃው ታንኩ፤ ኬሚካሉ አጥቂ
ሳተላይቱ ምንም የቀረህ የለም ጧትም ማታም እሱኑ
ስታመርት ትወላለህ ታድራለህ! ልትዋጋ ተለማምደሃል
ተዘጋጅተሃል / ወገብህን ትጥቅህን አጥብቀህ ጠብቀኝ!!
የምጠርግህ የምባላው እሳት በቅናቴ ቁጣ እንደጢስ
የማተንህ የሰራዊት ሁሉ ጌታ መጣሁብህ!! ይላል
እግዚአብሔር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ!!
ተመልከት ወገኔ! እንግዲህ አደመጥከው አይደል፤ መጣ
ኃያሉ ጌታ፤ እኛን ስትፈጭ ስትቆላ፤ ነበርክ፤ ማንም
ያልመከተህ ነበርክ፤ መግቢያ መውጫ ያሳጣኸን እንልሰው
እንቀምሰው ያሳጣኸን በገዛ አባታችን ንብረት ሀብት አንተ
አዛዥ ናዛዥ እኛ እስረኞችህ ዘወትር መጫወቻህ ነበርን።
ውርደትን መናቅን ማሰደድ መንከራተትን መሞት መታሰርን
መቀጥቀጥን እንደዘወትር ቀለብ የሰፈርክልን የልዑል ባሮች /
ልጆች/ እኛ ነበርን። ዛሬ የሰፈርከውን በትእቢትህ በንቀትህ
በማንአለብኝነት የዘራኸውን ሊያሳጭድህ ሊያስቅምህ፣ አስር
እጥፍ ብድራትህን ሊከፍልህ መጣለህ! ያውም በሙላት!
እንደብርቱ ማዕበልና እንደሚንተከተክ እሳተገሞራ
እንደሚገተለተለው ጭስ ጢሶ መጣብህ!! ምን ይባላል
ተቀብለው!! ስለእናንተ በእውነት እኔንም አስጨነቀኝ። መፍቻ
የሌለው ጉዳይ!!
ይህ ስምንተኛ መልእክት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሊያፀና
እንደወጣ ሁሉ የመጨረሻው ሰዓት ላይ በመደረሱ ለተሰናባቹ
የጠፋ ትውልድ የሚፈስበትን የእሳት ማዕበል ሰይፍ
እንዲያውቀው ለማድረግም ነው። ኢላማቸውንም ለማሳወቅ
ነው። የመነሻ ጊዜአቸውንም የሚገለፅበት ነው። አሁን ያለው
ጅማሮ የአገራችንም ሆነ የዓለም ጥፋት ብዙም ትርጉም
ያለው አይደለም። ከተዘጋጀልህ ብርቱና ህሊና ከሚሸከመው
በላይ የሆነ ጠረጋ እስከ አሁን ያየኸው ኢምንት ነው።
እንዲያውም ሰላም ነው የሚያስብል ነው። ከላይ ሰማኸው
አይደል! ቃል በቃል ነው የልዑልን ታላቅ ቁጣ ያሰፈርኩልህ።
ወገኖቼ! ቁጣው በሙሉ ኃይሉ መፍሰስ ከጀመረ፤
የሚያስቆመው ምንም ኃይል አይኖርም በአንድ ነገር ብቻ
ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል። ልዑል እንዳሰበው፤
ሀ/በመጀመሪያ በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ባሉ ሀገሮች ሁሉ ላይ
የቀባቸው የመረጣቸው የአከበራቸው ታማኝ አገልጋዮቹ
መንበረ ሥልጣኑን መጨበጥ አለባቸው። ያውም ተለምነው
ደጅ ተጠንተው በብዙ እንባና ጩኸት ተወትውተው፤
ይሁንታንም ከልዑል ተቀብለው (ከድንግልም ተባርከው
ሲረከቡና እነሱም ለቀረው ሕዝብ ከታላቁ ቁጣ ላመለጠው
ሕዝበ ክርስቲያን የልዑል ቁጣ እንዲበርድ ልመናና ምልጃ
ሲያቀርቡ ብቻ፤ ያኔ የአንደኛው ሰይፍ /የልዑል ሰይፍ/
ከእርምጃው መቀዝቀዝ ይጀምራል ይቆማል አላልኩም
ከከፍታው ወደዝቅታው እንደሁኔታው ይቀንሳል። ይህም
ማለት አበቃ ማለት አይደለም ሁለተኛው ሰይፍ ይጀምራል።
ይህ ሰይፍ የታመኑት አገልጋዮቹ ሰይፍ ሲሆን በመላው ዓለም
የልዑል አገዛዝ እስኪሰፍን ድረስ እርምጃው የሚቀጥል
ይሆናል። እግዚአብሔር ባሮቹን በኃይል ያስታጥቃል። የዚህን
ዘመን ጥበብ እውቀት የዲያብሎስን የዘመናት ዝግጅት ሁለት
ሶስተኛውን እጅ በልዑል ቀጥተኛ እርምጃ ይደመሰሳል።
ቀሪውን አንድ አራተኛ ለባሮቹ የሚተው የማጽዳት እርምጃ