2023-02-17 21:35:28
ሰባኛ ተአምር
ስለ ባለጠጎችና ስለ ችግረኞች
፩ ይቅርታው ቸርነቱ ለዘለዓለም በዕውነትህ ለሁላችን ይደረግልንና ጌታችን አምላካችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገው ተአምር ይህ ነው ።
፪ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤ በዚያን ጊዜ ለካደኝና
ለከዳኝ ወዮለት ለማትጠፋ የእሳት እራት ይሆናልና ።
፫ ፤ በክርስቲያናውያን ምዕመናኖቼ ላይ የሣቅ የተሣለቀ ወዮላት ፤ በፍርድ ቀን በሰው ሁሉ
ፊት መላእክት ይሣለቁበታልና። የቤተ ክርስቲያናትን መመዝበር የሚደግፉ ሁሉ ወዮላቸው
ሥጋቸውን እሳት ታንጨረጭረዋለችና ።
፬ ፤ በክርስቲያናዊ ጥምቀት ያልተጠመቀችውን የአረመኔያዊት ሴት ያገባ ወዮለት አጋንንት
በሲኦል እንደ ጭቃ ይረግጡታልና ፤ ከጠላቶቼ መናፍቃን ጋር አብሮ የሚበላ የሚጠጣ
ወዮለት ፤ በፍርድ ቀን ከነሱ ጋር እደምረዋለሁና ።
፭ ፤ የመበለታትን ልጆች የሚንበድል ወዮለት ፤ ማደሪያው እና በጨለማ ይሆናልና ፤
በአገልጋይ ካህናቶቼ የሚሣለቅ በነሱም ላይ በሐሰት የሚመሰክር ወዮለት ፍርዱ ሊሻሻልለት
አይችልምና ፤ በቅዱስ ሥጋዬና በክቡር ደሜ የሚሣለቁ ወዮላቸው የቅጣት ፍርዳቸው
ይግባኝ የለውምና ።
፮ ፤ በጐቼን ለማጥፋት የሚያስቡ ወዮላቸው ከመጻሕፍት ውስጥ ስሜን ለሚሠርዙ
ወዮላቸው ፤ ከነገሥታትና ከመኳንንት ጋር ወንድሞቻቸውን ለሚያጣሉ ወዮላቸው ፤
በተድላቸውና በደስታቸው ከነዳያን ጋራ ለማይተባበሩ ባለጸጐች መዮላቸው ፤ መኖሪያ
ቦታቸው ከዚያ በእሳት ወላፈን ከሚለበለበው ባለጸጋ ጋር ይሆናልና።
፯፤ በምዕመን ወንድሙ ላይ ዋሽቶ ክፉ ስም የሚያወጣ ወዮለት ፤ የሰው ገንዘብ ለሚሠርቅ
ወዮለት ፤ የነዳያንን ገንዘብ በግፍ ነጥቆ የሚበላ ወዮለት፤ የወንጌልን ቃል ለማይሰሙና
ለሚቀጣጠቡበትም ወዮላቸው
፰ ፣ ንጹሓን የሚሆኑ አል ዮቼ የቤተ ክርስቲያናትን ካህናት የሚረግም ወዮላቸው። ከአፀደ
ቤተ ክርስቲያን አንዲት ጠጠር ስንኳ ያነሣ ወዮለት ፤ ከበጐቼ አንዱን ያናቀ ያቃለለ
ወዮለት አገልጋዮች ካህናቱቼን በግዞት አሥረው ለሚገርፋቸው ለሚወጓቸው
ለሚጠቀጥቋቸው ወዮላቸው ።
፱ ፤ የክህነትን ሕግ ለሚደፋፈሩ ወዮላቸው። ካህን ሥልጣን የሚሰጠው በእኔ ፈቃድ ነውና
የክህነቱንም ሕግ በትክክል ቢጠብቅ እሱ የዘለዓለም ሕይወት አለው ፤ አገልጋዮች ካህናትን
ከክብር የሚያሳንሱ ወዮላቸው ፤ እኔ ከዘመናት በፊት መርጬ ሾሜአቸዋለሁና
እወዳቸዋልሁምና ።
፲ ፤ መንድሞቻቸው ነዳያን እየተራቡ ከመጠን በላይ ለሚመግቡ ወዮላቸው ፤ ከርኵሳን
አሕዛብ ጋር ሥጋቸውን ለሚያረክሱ ወዮላቸው ፤ ዕውነትን ሽሽገው ሐሰትን ለሚያንፀባርቁ
ወዮላቸውን ፤ ክርስቲያኖችን በችግራቸው ጊዜ ለማይራዱ ወዮላቸው። መድ%ቸ@ኑ ።
፲፩፤ ከኢአማንያን ጋር ሥጋቸውን ለሚያረክሱ ሴቶች ወዮላላቸው፤ ላልተጠመቁ
አረማውያንም ምቹ አልጋ መኝታ ለሆኑ ሴቶችም ወዮላቸው ፣ ክብርት ቤተ መቅደሴን
ለሚያረክሱ ወዮላቸው፤ ይህች ቤተ መቅደሴ በሷ ህልዉ ሆኜ የምኖርባት ናትና ።
፲፪ ፤ አገልጋዮቼ ካህናት ወደነሱ ሲመጡ እያዩ ተነሥተው በክብር ላልተቀበሏቸው
፲፪ ፤ አገልጋዮቼ ካህናት ወደነሱ ሲመጡ እያዩ ተነሥተው በክብር ላልተቀበሏቸው
ወንዶችና ሴቶች ወዮላቸው። ካህናት የኔን ሥልጣን የተጐናፀፉ ናቸውና ።
፲፫ ፤ ክፋትን በገዛ እጁ ለሚያመጣት ወዮለት ። እሱስ ባልተወለደ በተሻለው ነበር ፤
ዳግመኛም የወፍጮ መጅ በአንገቱ ላይ አሥረው ከጥልቅ ባሕር በጨመሩት በተሻለው ነበር
፲ሽ እህል ከበላ በኋላ ሥጋዬን ለሚበላ ወዮለት ፤ ከመናፍቃን ጋር በበዓላት ቀን ተድላ
ደስታ በማድረግ በመብል በመጠጥ አብሮ የሚሳተፍ ወዮለት።
፲፭፤ነገር ግን ከወገኖቼ ጋር የፋሲካዬን በዓል የሚያከብር እሱ የተመሰገነ ነው፤ እሱ ከእኔ
ጋር ይሆናል እኔም በጌትነቴ ክብር ከሱ ጋር እሆናለሁ ።
፲፮ ፤ በእኔ ስም የተጠመቁትን ክርስቲያን የሚገድል ወዮላት። በእኔ ዘንድ ኃጢአቱ
አይሠረይለትምና ፤ ልጆቻቸውን ወንድሞቻችውን የሚክዱ ሁሉ ወዮላቸው።
፲፯ ፤ እኔ ሳልልካቸው ነቢይ ነን ብለው ራሳቸውን በነቢይነት ለሚሠይሙ ወዮላቸው፤
ሐዋርያችን ለማይቀበሉ ወዮላቸው፤ ከአረማውያን ጋር በዓል የሚያከብሩ ለአጋንንትም
የታረደውን የሚበሉ ወዮላቸው፤ የምሥራቼን ለልጆቻቸው ለማይናገሩ ወዮላቸው።
፲፰፤የደወል ድምፅ ሰምተው ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመሄድ የማይፋጠኑ ወዮላቸው
በዕለተ ሰንበት ሥራ የሚሠሩ ወዮላቸው፤ በዕለተ ሰንበት የሚሸጡ የሚለውጡ የሚገዙ
ወዮላቸው ፤ በዕለተ ሰንበት የመንገዳቸውን በር ለሚከፍቱ ወዮላቸው ፤ በዚህም
ጥምቀታቸው ይሻርባቸዋልና ።
፲፱ በዕለተ ትንሣኤ ዕድል ፈንታቸው ከሰዶምና ከገሞራ ጋር እንደሆነ በልዑል ክንዴና
በመለኮታዊ ሥልጣኔ እናገራለሁ ፤ ሰንበቶቼን የሻረ ፈጽሞ ፀጥታና ዕረፍት አይኖረውም ።
የክህነትን ሥራ ጊዜያዊ የሚያደርሱ ሥጋዬን ከመብላትና ደሜን ከመጠጣት ቸል የሚል
ወዮለት።
፳ በቅዳሴ ጊዜ ቄሱ ቅዱስ ሥጋዬን እየፈተተ እያለ የሚጫወቱ ወይም የሚነጋገሩ
ወዮላቸው። በዕለተ ሰንበት በመታጠቢያ ትቤ ገብተው የሚታጠቡ ሰዎች ወዮላቸው።
በአምላክነቴ ባሕሯ የሚሰነካከል ወዮለት።
፳፩ ፤ ከቤተ ክርስቲያንና ከመሠዊያው አገልጋዮች ካህናትን ያበረሩ ያሳደዱ ወዮላቸው ፤
ከመናፍቃን ጋር በዓልን ለማክበር የሚተባበሩ ወዮላቸው ። በእኔ ስም ያልተጠመቀችውን
ጡት ለልጁ ያጠባ እንድታሳድገውም ሞግዚት ያደረገ ወዮለት።
፳፪ ከአረማውያን ጋር ለሚጋቡ ወዮላቸው ። መወለዴን መሰቀሌን ክብርት ትንሣኤንም
የሚክዱ ወዮላቸው ። ወንድሞቻቸው በረኃብ በችግር ሲንገላቱ ከመጠን በላይ በድሎትና
በምቾት የሚኖሩ ወዮላቸው፣ በዕለተ ሰንበት ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገስግሰው
ለማይመጡ ወዮላቸው ።
፳፫፤ እሱ ክብር ምስጋና ይሁንና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሕዝብ ሕጉንና ሥርዓቱን
ያስተምሩ ዘንድ ለደቀ መዛሙርቱ ይህን አስተማራቸው።
፳፬ ፤ ይቅርታው ቸርነቱ ለዘላለሙ በዕውነት ለሁላችን ይደረግልን።
2 views18:35