Get Mystery Box with random crypto!

ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።

የቴሌግራም ቻናል አርማ dereje1678 — ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።
የቴሌግራም ቻናል አርማ dereje1678 — ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።
የሰርጥ አድራሻ: @dereje1678
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-03-18 23:49:01 #መጋቢት_10 ተቀብሮ አልቀረም ተገኝቷል መስቀሉ።

በዚህች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ለዘመናት ተቀብሮ ከኖረበት ቦታ የወጣበት ቀን ነው። መስከረም 16 ቀን ደገኛዋ እናት እሌኒ ቅድስት ደመራ ደምራ በደመራው ጢስ አማካኝነት የተቀበረበትን ቦታ አገኘች መስከረም 17 ቁፋሮ ጀመረች፤ከ 300 ዘመናት በላይ ቆሻሻ እየተጣለበት ታላቅ ተራራ አህሎ ነበርና እነሆ ቁፋሮ ስድስት ወራት ፈጀባቸው መጋቢት 10 በዛሬዋ ቀንም መስቀሉ ወጣ።

ሦስት መስቀሎች ናቸው፤ሁለቱ መስቀሎች ሽፍታዎቹ የተሰቀሉባቸው ሲሆኑ አንዱ የጌታችን ነው፤ ታዲያ እንዴት ለየችው ቢሉ የጌታችን መስቀል ታላላቅ ታአምራትን አድርጓል ድውይ ፈውሷል ዓይነስውር አብርቷል። ይህንን ቀን ቅድስት ቤተክርስቲያን "መስቀለ እየሱስ" ስትል ታከብረዋለች፤ በዛሬዋ ቀን ዝማሬው፤ ምስጋናው፤ ትምህርቱ፤ ቅዳሴው ፤ ንባቡ ሁሉም መስቀልን የሚመለከቱ ናቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ መስቀል የሚጣፍጥ ነገር ተናገረ እንዲህ ሲል “ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።” ገላትያ 6፤14።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
8 views20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 08:18:15 ኢሳይያስ 60
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ።
² እነሆ፥ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤
³ አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ።
⁴ ዓይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል።
⁵ በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፥ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፥ አይተሽ ደስ ይልሻል፥ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል።
⁶ የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ።
⁷ የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።
⁸ ርግቦች ወደ ቤታቸው እንደሚበርሩ፥ እነዚህ እንደ ደመና የሚበርሩ እነማን ናቸው?
⁹ እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለእግዚአብሔር ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመጡ ዘንድ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።
¹⁰ በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ፥ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል።
¹¹ በሮችሽም ሁልጊዜ ይከፈታሉ፤ ሰዎች የአሕዛብን ብልጥግና የተማረኩትንም ነገሥታቶቻቸውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊትና ቀን አይዘጉም።
¹² ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።
¹³ የመቅደሴንም ስፍራ ያስጌጡ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው ባርሰነቱም፥ ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ።
¹⁴ የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።
¹⁵ ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።
¹⁶ የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የያዕቆብ ኃይል፥ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
¹⁷ በናስ ፋንታ ወርቅን፥ በብረትም ፋንታ ብርን፥ በእንጨትም ፋንታ ናስን፥ በድንጋይም ፋንታ ብረትን አመጣለሁ። አለቆችሽንም ሰላም፥ የበላይ ገዢዎችሽንም ጽድቅ አደርጋለሁ፤
¹⁸ ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ።
¹⁹ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፥ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም።
²⁰ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም ጨረቃሽም አይቋረጥም።
²¹ ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እከብር ዘንድ የአታክልቴን ቡቃያ፥ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ።
²² ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሹ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር በዘመኑ ይህን አፋጥነዋለሁ።ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
7 views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 20:57:59
- አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሕልው እንደሆነ ፣ ወልድም በአብ በመንፈስ ቅዱስ ሕልው እንደሆነ መንፈስ ቅዱስም በአብ በወልድ ሕልው እንደሆነ እናምናለን ይህች ሦስትነት ያለመለየት ያለመለወጥ በሦስት አካላት በአንድ መለኮት የተካከለች ናት ፡፡ 
- አንዲት አገዛዝ አንዲት ፈቃድ አንዲት ሃይል አንዲት መንግሥት አንዲት ስግደት አንዲት ምሥጋና አንዲት ክብር አንድ ጽንዕ ለሥላሴ ይገባል ፡፡ አንዲት ምክር አንዲት ሥልጣን አንድ ክብር አንዲት ጽንዕ አንድ አኗኗር አንድ ፈቃድ ለሥሉስ ቅዱስ ነው ፡፡
  - አብም አብ ነው እንጂ ወልድን መንፈስ ቅዱስን አይደለም ፡፡ ወልድም ወልድ ነው እንጂ አብን መንፈስ ቅዱስን አይደለም ፡፡ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ አብን ወልድን አይደለም ፡፡ አብ ወልድን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም ፡፡ ወልድም አብን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም መንፈስ ቅዱስም አብን ወልድን ወደመሆን አይለወጥም ፡፡ እሊህ ሦስቱ አካላት በጌትነት በክብር ፍጹማን ናቸው ፡፡ በአንድ መለኮት አንድነትም አንድ ናቸው ፡፡
  - ይኸውም ሦስትነት ከእርሱ የሚገኝ አንድ ብርሃን ነው ፡፡ በዓለሙ ሁሉ መሉዕ ነው ፡፡ ከምድር በታች ላሉትም ያበራል ፡፡ በሰማይ በምድር ምሉ ነኝ እኮ ! በሲኦልም ያሉ ጌትነቱን አዩ ተብሎ እንደተፃፈ ፡፡


ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት 9 ገፅ 23
7 views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 14:33:48
11 views11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 08:45:34 ክፍል 1
9 views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 09:51:00
6 views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 09:50:59 ሩካቤ_ሥጋ_የማይፈጸምባቸው_ጊዜያት

ሩካቤ ሥጋ፣ በምን ዓይነት ሥርዓት ሊፈጸም እንደሚገባው በሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ተደንግጓል፤ እግዚአብሔር ሩካቤን ለሰው የሠራው ልጅ ለመውለድ ብቻ አይደለም፤ የማይወሰን የማይገታ የፈቲውን ፆር ለማራቅ ጭምር ነው እንጂ፡፡

አንድ ጊዜ የሚከለከሉበትን፣ አንድ ጊዜ ፈቃዳቸውን የሚፈጽሙበትን ሠራ፡፡ ነገር ግን አንድ ወንድ ለአንድ ሴት፣ አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ ብለው ዘወትር ሊያደርጉት አይገባም፡፡

አጽዋማትን፣ በዓላትን፣ ኅርስን፣ ትክትን ለይቶ ሊያደርጉት ይገባል እንጂ፤” (ፍት.ነገ.አን.15፥፣ ቍ.
38-58)፡፡
ከላይ እንደ ገለጽነው ሩካቤ ሥጋ በሥርዓት የሚፈጸም እንደ መኾኑ የማይፈጽምባቸው ጊዜያትም አሉ፡፡

እነዚህም የሚከተሉት ናቸው ፦

የእርግዝና እና የንጽሕ ጊዜያት ሚስት በፀነሰችበት ወይም ባረገዘችበት ወቅት

በወር አበባዋ ጊዜ

በመውለጃዋ ጊዜ (ወንድ ከወለደች ከዐርባ ቀን ሴት ከወለደች ከሰማንያ ቀን በፊት) ሩካቤ ሥጋ መፈጸም አይገባም

ዘሌ. (8፥18)፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም “በኅርሷ፣ በደሟ ወራት ሚስትህን አትድረስባት" ፡፡ ግቢህ ከመጽሐፍ ሥርዓት የወጣ እንዳይኾን” በማለት በፅንስ (እርግዝና) እና በንጽሕ ጊዜያት ማለትም በአራስነትና በወር አበባ ወቅት ግንኙነት መፈጸም እንደማይገባ አዝዟል (ፍት. ነገ. አን. 24፣ ቍ. ፷፬)፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የሚስት ፅንሷ ከታወቀ በኋላ ለመረዳዳት ካልኾነ በቀር ባሏ ሊቀርባት እንደማይገባ ተደንግጓል (አን. ፳፬፣ ቍ. ፰፻፴፰)፡፡

ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሔዱባቸው ቀናት እስራኤላውያን እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር ሲነጋገር ከመስማታቸው (ሕጉን ከመቀበላቸው) ከሦስተኛው ቀን በፊት እንዲቀደሱ፣ ልብሳቸውን እንዲያጥቡና ሩካቤ እንዳይፈጽሙ ታዝዘው ነበር፡፡ ዛሬም በሐዲስ ኪዳን ባለ ትዳሮች ትምህርተ ወንጌል ለማዳመጥ፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል፣ ጠበል ለመጠመቅና ለመጠጣት፣ ወይም ለሌላ አገልግሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሔዱ ከሩካቤ ሥጋ እንዲከለከሉ ታዝዟል (ዘፀ. 19፥10-25 )፡፡ ከዚህም ሌላ በጥምቀት ክርስትና የሚያነሡ (የክርስትና እናት ወይም አባት የሚኾኑ ምእመናን) ክርስትና ከማንሣታቸው በፊትና በኋላ ለሁለት ቀናት ከሩካቤ ሥጋ መከልከል ይገባቸዋል፡፡

ይኸውም መንፈስ ቅዱስን ለማክበር ነው፡፡ ምሥጢረ ጥምቀት ጸጋን፣ ክብርንና ልጅነትን የሚያሰጥ ምሥጢር ስለ ኾነ፡፡ ካህኑ ዘካርያስ የቤተ መቅደሱን አገልግሎት ከፈጸመ ከሁለት ቀን በኋላ ከኤልሳቤጥ ጋር መገናኘቱም ለዚህ ትምህርት ነው፡፡ " ከሁለት ቀን በኋላም ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች” ተብሎ እንደ ተጻፈ (ሉቃ. 1፥24፤ ፍት. ነገ. አን. 24፣ ቍ. 38)፡፡

በዓላት ቅዳሜ፣ እሑድና በዓበይት በዓላት ሩካቤ ሥጋ መፈጸም የተከለከለ ነው፡፡

ይኸውም በመንግሥተ ሰማያት ጋብቻና ፈቃደ ሥጋን መፈጸም አለመኖሩን ለማጠየቅ ነው፡፡ በዓላት፣ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌዎች ናቸውና ፡፡

“በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይኾናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም” እንዲል (ማቴ. 22፥23)፡፡

ሌላው ምክንያት ደግሞ “ንጹሕ የኾነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው … በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው” በማለት ቅዱስ ያዕቆብ እንደ ተናገረው (ያዕ. ፩፥፳፯)፣ በእነዚህ ዕለታት ወደ ቤተክርስቲያን በመሔድ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበልና ራስን መጠበቅ ተገቢ ስለ ኾነ ነው፡፡

ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፣ ሰንበትንም ደስታ፣ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ‹ክቡር› ብትለው፣ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ፣ ፈቃድህንም ከማግኘት፣ ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፣ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፤ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ” ተብሎ ተጽፏልና (ኢሳ. 48፥13-14)፡፡

አጽዋማት

“ጸዋሚ ሆይ፥ መላው አካልህ ይጹም፤ አፍህ ክፉ ከመናገር፣ አንደበትህ ከሐሜትና ከስድብ፣ ዓይንህ ሴቶችን ከማየት፣ ጆሮህም ዘፈንና ጨዋታ ከመስማት ይጹም” ተብሎ እንደተነገረን (ርቱዐ ሃይማኖት) ሩካቤ ሥጋም ሰውነት የሚደሰትበት ፈቃድ ስለ ኾነ በጾም ወቅት መታቀብ ይገባል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ባልና ሚስት በንስሓ አባታቸው የተሰጣቸዉን የንስሐ ቀኖና ወይም በራሳቸው ፈቃድ የገቡትን የጾም ሱባዔ እስከሚፈጽሙ ድረስ ከሩካቤ ሥጋ መከልከል ይገባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ ባልና ሚስት በፅንስ፣ በአራስነትና በወር አበባ ወቅት፤ እንደዚሁም በበዓላትና በአጽዋማት ቀን ሩካቤ ሥጋ ማድረግ እንደማይገባቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡

ከዚህ በተረፈ ግን ሰይጣን የሚፈትንበትን ክፍተት እንዳያገኝ ባልና ሚስት ሊለያዩ አይገባም፡፡ “ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልኾነ በቀር እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን
እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ ኹኑ፤” እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ (1ኛ ቆሮ. 7፥5)፡፡

ይህ የሐዋርያው ትምህርት "ሰውነታችሁን ንጹሕ አድርጋችሁ በምትጾሙበት፣ በምትጸልዩበት ጊዜ ነው እንጂ ሥራችሁን ከፈጸማችሁ በኋላ ግን ወደ ፈቃዳችሁ ተመለሱ ይላል፡፡

ይህም ትእዛዝ ባልና ሚስት፣ የጾም፣ የጸሎት፣ የበዓል ወቅት ካልኾነ በቀር ሳይለያዩ ፈቃዳቸዉን መፈጸም እንደሚገባቸው ያስገነዝባል፡፡

ለእርኩሰትና ለበደል ከሚፈፀም ሩካቤ ይጠብቀን።
6 views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 20:33:17
6 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 20:33:17
6 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 20:33:17 ወደ ጥያቄዉ ምላሽ ስገባ፡ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረዉ ከሰዉ ፍጥረት ጀምሮ ነዉ፡፡ ይኸዉም አዳምና ሔዋን ከገነት እንደተባረሩ የተገለጡበት የመጀመሪያ ምድር የኢትዮጵያ ምድር ነዉ፡፡ “ ዔደን ገነት” የተባለችዉ የግዮን (የዓባይ) ወንዝ የሚነሳባት፣ በተለያዩ ወንዞችና ፈሳሾች የተከበበች አገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ታሪክ የሚጀምረዉ ከአዳምና ሔዋን ጀምሮ ነዉ፡፡ በዓለም ዉስጥ ያሉት ሕዝቦች አላስተዋሉትም እንጂ ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያዉያን፤ የአዳምና ሔዋን ዘሮች የሆኑ የካም፣ የሴም፣ የያፌት ነገዶች እንዲሁም የሦስቱ ነገድ ዉሕድ ዘር የሆነዉ የኢትዮጲስ ልጆች የመልከጼዴቅ ልጆች ናቸዉ፡፡

ይሁንና እንኳን ሌላዉ የዓለም ሕዝብ ይቅርና የቅርቦቹ ኢትዮጵያዉያን የነበሩት የባሕረነጋሽ (የኤርትራ) ተወላጆች “እኛ የባለ ቃል ኪዳኗ ኢትዮጵያ ዜጎች አይደለንም፡፡” በማለት በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ በግልጽ ዓመጻ ፈጽመዋ፤ ኢትዮጵያዊነት ላይም ክህደት ፈጽመዋል፡፡ ይህ ዓመጻና ክህደት ደግሞ ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል እጅግ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ የምንመለከተዉ ይሆናል፡፡ እንደ ወገንነታችንና ቤተሰብነታችን የምንመክራቸዉ ዛሬ ነገ ሳይሉ፣ ቀኑ ሳይመሽባቸዉና ሳይጨልምባቸዉ በእዉነተኛ ንስሐ ተመልሰዉ ከእናት አገራቸዉ ከኢትዮጵያ እቅፍ እንዲገቡ ነዉ፡፡ እነሱ ብቻ አይደለም በቀኝ ገዥ ከፋፋይ ሴራ ኢትዮጵያዊነታቸዉን የካዱት፤ በኢትዮጵያ ዙሪያ ያሉ ወገኖቻችን ከእናት አገራቸዉ ኢትዮጵያ ጋር ቢዋሐዱ ከጥፋትና ከመደምሰስ ይተርፋሉ፡፡ ሌላዉ ዓለምም ቢሆን የእግዚአብሔር እዉነት የሆነዉን ኢትዮጵያዊነት ቢቀበሉና እንደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እምነትና ሥርዓት ቢመላለሱ ራሳቸዉን ከጥፋትና ከመደምሰስ ሊያድኑ እንደሚችሉ ወገናዊ ምክራችንንና ጥሪያችንን በዚሁ አጋጣሚ እናቀርባለን፡፡” በማለት የድሆችና የችግረኞችም አምላክ የእግዚአብሔር አገልጋይና መልእክተኛ ለጠየቃቸዉ አካል ምላሻቸዉን ሰተዋል፡፡

ምንጭ በ2005 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በእግዚአብሔር ትእዛዝ፣ ገላጭነትና አሳሳቢነት “ታላቅ የብርሃን ተስፋ ለኢትዮጵያዉያንና ለዓለም” በሚል ርእስ ከተጻፈዉና በኅዳር 2014 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ ታትሞ ለትዉልዱ ከቀረበዉ ከክፍል 8 ከምእራፍ 5 ከገጽ 354-355 ድረስ የተወሰደ፡፡

ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ!
እግዚአብሔር ያናገረዉንና ያስመሰከረዉን ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል የማይቀርና፤ ምንም ኃይል ሊያስቀረዉ ቀርቶ ሊያዘገየዉ አይችልም፡፡ ከላይ በጥያቄና መልስ እንዲቀርብ እግዚአብሔር ያስደረገዉ፤ ትዉልዱ እዉነታዉን አዉቆና አስተዉሎ በእዉነተኛ ንስሐ እንዲመለስና ከእግዚአብሔር እዉነት ጋር እንዲሰለፍ ነበር፡፡ ይሁንና የእግዚአብሔርን እዉነት የሚሰማና የሚቀበል ስለሌለ ለ27 ዓመት የንስሐ እድል ተሰቷቸዉ የነበሩትና አዛዥ፣ ናዛዥ፣ ፈላጭ፣ ቆራጭ የነበሩት ሕወሐት ኢሕአዴግ፤ የዓመጻና የግፍ ጽዋቸዉ ሲሞላ እንደልነበሩ እንደሆኑና ለመከራ፣ ለዉርደትና ለሞት እንደተዳረጉ በዚህ አጭር ዓመታት ዉስጥ ተመልክተናል፡፡ አሁንም በእዉነተኛ ንስሐ ተመልሰዉ ከእግዚአብሔር እዉነት ጋር ካልተሰለፉ በስተቀር የመደምደሚያ የእግዚአብሔር ቁጣና ጠረጋ የሚያሰናብታቸዉና አቅማቸዉና ትዕቢታቸዉ እስከምን ያህል ድረስ እንደሆነ ያሳያቸዋል፡፡

የሚያሳዝነዉና የሚገርመዉ ደግሞ ከሕወሐት ኢሕአዴግ አወዳደቅና አጠፋፍ ትምህርት መዉሰድ ያልቻለዉ፤ የእግዚአብሔርን ፍርድና አሰራር ማስተዋል ያቃተዉ የቀድሞ የሕወሐት ኢሕአዴግ አገልጋይና መሳሪያ የነበረዉ ኦህዴድ፤ የአሁኑ ኦዴፓ/ኦነግ ብልጽግና ነዉ፡፡ እግዚአብሔር ፈቃዱ ስለሆነ ብቻ ነዉ ማንነታችሁ እንዲታይና እንዲታወቅ፣ በሕወሐት (ወያኔ) ኢሕአዴግ የተፈራችሁ “ መራራ ፍሬ” የተባላችሁ፣ ከኢትዮጵያ እዉነተኛ ትንሣኤ በፊት የሚቀረዉን ክፉ ትንቢት እንድትፈጽሙ ነዉ ወደ ወንበር የመጣችሁትና ባለ ጊዜ ሆናችህ አዛዥ ናዛዝ ፈላጭ ቆራጭ የሆናችሁት እንጂ፤ የዓመጻና የግፋችሁ ጽዋ ሲሞላ የአንዲት ቀን እድሜ እንደማይጨመርላችሁና ከሕወሐት (ወያኔ) ኢሕአዴግ መንግሥት በላይ የከፋ የእግዚአብሔር ቁጣና ጠረጋ እንደሚመጣባችሁ በእምነት ዉስጥ ያለ ሰዉ በሚገባ ያዉቃልና፤ በሚታየዉና በሚሰማዉ የክፋትና የበቀል፣ የጭከናና የግፍ ተግባራችሁ ከማዘንና ወደ ፈጣሪ የባለጊዜነታችሁ ዘመን እጅግ እንዲያጥር ከመጸለይ ዉጭ አንደች ተስፋ አይቆርጥም፣ የእግዚአብሔርን ኃይል አንዳች አይጠራጠርም፡፡

እንግዲህ ምናልባት የንስሐ ልብ ያላችሁ ካላችሁ እናንተም ዛሬ ነገ ሳትሉ በእዉነተኛ ንስሐ እንድትመለሱና ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንድትሰለፉ ወንድማዊ ጥሪዬንና ማሳሰቢያዬን አቀርባለሁ፡፡ ነገር ግን “የምን የእግዚአብሔር ፍርድና ጥሪ ነዉ? በከሸፈዉና ለአብዮታዉያኑ ያልሆነዉ አብዮታዊ ዲሞክራሲ እምነታችን ሳይሆን፤ በቃሉ መንፈስ በኦሮሙማ እምነታችን ሁሉንም እናሸንፋለን፣ ማንም ምንም ሊያደርገንና ከወንበራችን ሊነቀንቀን አይችልም፣ ጊዜዉ የእኛ ነዉና የፈለግነዉን ማድረግ እንችላለን፣ እንዲህ ይሆናል ብላችሁ ያላሰባችሁት ዐይን ባወጣ መልኩ ፍላጎታችንንና ዓላማችንን እያከነዉን እንደሆነና በነፍስ በሥጋችሁ እየተጫወትንባችሁ መሆኑን እያያችሁት አይደለም ወይ!…ወዘተ ” ብላችሁ፤ በዓመጻችሁ፣ በክህደታችሁ፣ በርኩሰታችሁ፣ በትዕቢትና እብሪታችሁ፣ በግፋችሁ ከጸናችሁ፤ እጅግ እጅግ በቅርቡ እግዚአብሔር ፍርዱና ቁጣዉ ምን እንደሆነና አቅማችሁና እብሪታችሁ እስከምን ያልህ ድረስ እንደሆነ ሁላችንም የምንመለከታዉ ነዉና፤ የንስሐ እድሜ፣ ጤናዉን፣ ትእግሥትና ጽናቱን እግዚአብሔር ይስጠን ከማለት ዉጭ ምንም አልልም፡፡

ፀረ ኢትዮጵያዉያን ላፈሩበትና በእግዚአብሔር ኃይል የተማመኑት ኢትዮጵያዉያን ከመሪያቸዉ ከአጼ ምኒልክ ጋር በመሆን የጣሊያን ወራሪ ቀኝ ገዢዎችን ድል በማድረግ እብሪተኞችንና ግፍኞችን ላሳፈሩበት ለ127ኛዉ ለዐድዋ ድል መታሰቢያ በዓል እንኳን አደረሰን እያልኩ፤ የእግዚአብሔር ኃይል፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት ፤ የጀግኖቻችን ኢትዮጵያዉያን ወኔ፣ የቅዱሳን ጥበቃ አይለየን፡፡ አሜን

ተጻፈ በመከራ ዉስጥ ካለችዉ ከባለተስፋዋ አገር ኢትዮጵያ!
፳፫፥፮፥፳፻፲፭
7 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ