2023-03-22 23:04:38
. >| በየዕለቱ ከሴተኛ አዳሪ ጋር የሚያድረው መነኵሴ ሞተ |<
~ እጅግ ግርም ያለኝ ታሪክ እነግራችሁ ዘንድ ግድ ይለኛል። ታሪኩ እንደዚህ ነው፦
#_በቅርብ_በምናውቃት_ሀገር ፥ በአንዱ ገዳም ውስጥ መንኵሶ የሚኖር አንድ መነኰስ ነበር። እሱ ያለበት ገዳም አበምኔት፥ እዛው ባሉ መነኰሳት ላይ ነገረ ሠሪን እንደሚቀበል ሲሰማ በዓቱ ትቶ ይወጣል። ሹልክ ብሎ ወጥቶ፣ ከተማ ገብቶ የቀን ሥራን ይሠራ ጀመር።
ከቀን ሥራው የሚያገኘውን ገንዘብ ጥቂት ለሆዱ ያደርግና የተቀረውን ይዞ ወደ ሴተኛ አዳሪዎች ይሄድ ጀመር። የምንኵስናውንም ልብስ ሳይጥል በዚህ ድርጊቱ ገፋበት። ነዋሪውም ያዝንበትና ያማው ጀመር።
{ ቆይ እዚህ ጋር፥ ምን ተሰማችሁ }
{ በዚህ መነኰስ አዘናችሁበት? ወይስ አፈራችሁበት? }
ነገሩ ግን እንዲህ ነው፦
ይሄ በሰው ድርጊት ሰውን ማማት የማይወድ መነኰስ የቀን ሥራውን ሂሳብ ተቀብሎ ይሔድና በከተማ ያሉትን ሴተኛ አዳሪዎች ስም ይጽፋል፤ ይመዘግባል።
ለምን?
ምክንያቱም ከቀን ገቢው ላይ የሽንብራ ቂጣ በልቶ ያስቀረውን ገንዘብ በቀን አንድ ሴተኛ አዳሪ ወደ ኃጢአት እንዳትገባ ይሰጣታል። #_ወደ_ኃጢአት_እንዳትገባ
... በየቀኑ ወደ ሴተኛ አዳሪ ጋር እየሔደ፦ "በዚች ቀን ከአንቺ ጋራ አድራለሁና ራስሽን ለእኔ አዘጋጂ" ይላታል። ከኃጢአትም ሊጠብቃት ከእርስዋ ዘንድ ያድራል። #_ሌሊቱን_ሁሉ_ተነሥቶ_ሲጸልይና_ሲሰግድ_እግዚአብሔርንም_ሲለምን_ያድራል። ሲነጋም ሥራውን ለማንም እንዳትገልጥ አምሏት (ቃል አስገብቷት) ወደ ቀን ሥራው ይሔዳል።
... በዚህም የተነሣ...በከተማው.. እጅግ ይታማ ጀመር። ይህንን መታማቱን ያልወደደች አንዲቱ አመንዝራ ምሥጢሩን (ንጽሕናውን) ተናገረችበት። እርሷም "እንዳናመነዝር ገንዘብ በመስጠት ከኃጢአት ይጠብቀናል እንጂ ነውር የለበትም" አለች።
#_ስትናገርም_ጋኔን_ይዞ_አሳበዳት። የአካባቢው ሰዎችም "ስለዚህ ክፉ ሽማግሌ 'ክፉ ሥራ የለበትም' ብላ ዋሽታለችና እግዚአብሔር መልካም አደረገባት" ተባባሉ።
የቀሩት አመንዝራ ሴቶች ደሞ በእርሷ ላይ የሆነውን በአዩ ጊዜ ደነገጡ። እንደርሷም እንዳያብዱ "እውነቷን ነው" ማለትን ፈሩ። መነኰሱም እውነቱን ሳይናገር ወደ አመንዝራዎቹ ጋር መግባቱን ቀጠለ። ሰዎችም ሁሉ እጅግ ይነቅፉትና ይንቁት ጀመር። (የሚያዝንለትና ከክፉ ድርጊቱ እንዲመለስ የሚጸልይለት ኖሮ ይሆን?!)
°°° በሐሜቱ ያልተበገረው መነኰስ "መነኰስ ሰው አይደለምን? በፍትወት መቃጠልና መሞት አለበትን?" ይላቸው ነበር። እነርሱም "ልብስህን ለውጠህ ሚስት አግባ" አሉት።
እርሱም፦ "አዎን ብወድ በሚስቴ እጠነቀቃለሁ። በዚህም በክፉ አኗኗር እኖራለሁ። እናንተ ግን ከእኔ ዘንድም ሒዱ ምን ትሻላችሁ? በእኔ ላይ እግዚአብሔር ፈራጆች አድርጓችኋልን? ይልቁንስ #_እናንተ_እንዳይፈረድባችሁ_ለራሳችሁ_አስቡ። ፈራጅ አንድ ነውና ዕለቲቱም አንዲት ናትና" አላቸው።
... ይህም #_ቅዱስ_መነኰስ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን አገኘ በሰው ዘንድ ግን የተናቀ ሆኖ ኖረ።
#_ታዲያ_መጨረሻው_ምን_ሆነ?
°°° ከመነኰሱ ድርጊት በኋላ ከእርሱ ጥቅም የአገኙ አመንዝራዎች ዝሙታቸውን ተዉ። አንዳንዱ ሕጋዊ ጋብቻ ተጋብቶ መኖር ጀመረ። አንዳንዱ ወደ ገዳም ገብቶ መንኵሶ፣ በጾም በጸሎት ተወስኖ የኖረ አለ።
°°° ይህ መነኰስ እንደለመደው፥ በአንዲት ዕለት፥ ከአንዲት አመንዝራ ቤት ሲወጣ ያቺን ሴት አስቀድሞ የለመዳት አንድ ሰው አገኘውና "ይህ ሽማግሌ እስከ መቼ ድረስ በዚህ በክፉ ሥራ ይኖራል" ብሎ ፊቱን በጥፊ መታው።
✧ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን በበዓቱ ውስጥ ሰግዶ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጥቶ በቤቱም መድረክ፦
"የዚች አገር ሰዎች፥ #_ጊዜው_ሳይደርስ_እንዳይፈረድባችሁ_በማንም_ላይ_አትፍረዱ!" የሚልም ጽሑፍ ተጽፎ ተገኘ።
•• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• ••
✧ እኚህ መነኰስ ፍጹማን መነኰሳት ከሚባሉት ውስጥ አንዱ የሆኑት #_አባ_ባጥል_ዘእስክንድርያ ናቸው። መጋቢት 14 የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል ነው።
"በባሕርይህ ንጹሕ የሆንክ አምላከ አባ ባጥል ሆይ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልን፤ የቀናውንም መንፈስ በውስጣችን አድስ" እያልን በስማቸው እንማፀን፤ እንዘክራቸው።
•• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• •• ••
5 views20:04