Get Mystery Box with random crypto!

ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።

የቴሌግራም ቻናል አርማ dereje1678 — ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።
የቴሌግራም ቻናል አርማ dereje1678 — ደረጀ እና የድንግል ማርያም ልጆች ግሩፕ ቻናል።
የሰርጥ አድራሻ: @dereje1678
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-23 09:30:37
3 views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 09:30:37

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፨

▸ ሚያዝያ 15 |
#_የመጥምቁ_ዮሐንስ ቅድስት ራስ 15 ዓመታት ከሰበከች በኋላ ዐረፈች።

         
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደጻፈውም ፦

የመጥምቁን አንገት ቆርጠው፣ በጻሕል አድርገው ወደ ኄሮድስ አመጡለት። እርሱም ለኄሮድያዳ ልጅ ሰጣት፤ እርሷም ለእናቷ ወስዳ ሰጠች።

ይቺም የረከሰች አመንዝራ ልትዳስሣት በወደደች ጊዜ በወጭቱ ውስጥ ጠጒሯ ተዘርግቶ (ክንፍ አውጥታ) ወደ አየር በረረች።

በአየርም ሁና የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች የምትጮኽ ሆነች። እንዲህም እያለች ዐሥራ አምስት ዓመት ኑራ በዓረቢያ ምድር (ሚያዝያ 15) ዐረፈች፤ በዚያም ተቀበረች።
                        ✧◦✧◦✧

፨ እንኳን አደረሳችሁ ፨
3 views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 13:02:51


▸ ሚያዝያ ፲፪ | የመላእክት አለቃ
#_ቅዱስ_ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ #_ነቢዩ_ኤርምያስ ላከው፡፡

ቅዱስ ኤርምያስ ነቢይ፥ ጠባቡና ረግረግ ከሆነ እሥር ቤት ሴዴቅያስ ንጉሥ በአሠረው ጊዜ የንጉሡ ባለሟልና የጭፍራ አለቃ የሆነው አቤሜሌክ አወጣው።

ያንጊዜም የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ መራራ ምርኮንም እንዳይቀምስ ኤርምያስ ነቢይ መረቀው እንዲሁም ሆነ።

ስሳ ስድስት ዓመትም ተኝቶ ኖረ። ከእርሱ ጋራ ወይንና በለስ ነበረ። አልተለወጠም። የእስራኤል ልጆች ከምርኮ እስቲመለሱ በለሱንም ከደብዳቤ ጋራ ወደ ኤርምያስ ባቢሎን አገር ላከው።

ስለዚህም የዚህን የከበረ መልአክ ሚካኤልን በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን መታሰቢያውን እንድናደርግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን።
~ ~ ~

በአማላጅነቱም በኢትዮጵያን ላይ ከሚወርደው ጥፋት ሸፍኖ ከትንሣኤው ዘመን ያድርሰን፤ አሜን።

እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰ
ን ! አሜን ።
1 view10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 15:59:57 በተክለ ኪዳን ህዳር 2011 ዓ.ም
3 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 21:15:33 ​​ ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

ሰኞ

ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

ማክሰኞ

ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

ረቡዕ

አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

ሐሙስ

አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

ዓርብ

ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

ቅዳሜ

ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

እሁድ

ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
ወስብሐት  ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል  ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን።
5 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 07:17:25 እንኳን ለዕለተ "ማዕዶት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የትንሳኤ ሰኞ ስያሜ
+*" ማዕዶት "*+

=>ማዕዶት ማለት (ዐደወ-ተሻገረ) ከሚል የግእዝ ግስ የተወረሰ ሲሆን በጥሬው "መሻገር" ማለት ነው:: ይሕም በደመ ክርስቶስ ተቀድሰን: በትንሳኤውም ድኅነት ተደርጐልን መከራን: መርገምን: የኃጢአትን ባሕር: አንድም ባሕረ እሳትን መሻገራችንን ያመለክታል::

+ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ደሙ
*ከባርነት ወደ ነጻነት
*ከጨለማ ወደ ብርሃን
*ከሞት ወደ ሕይወት
*ከኃጢአት ወደ ጽድቅ
*ከሲዖል ወደ ገነት
*ከገሐነመ እሳት ወደ መንግስተ ሰማያት
አዳምንና እኛን ልጆቹን አሸጋግሮናል::

+አባታችን አዳምና ልጆቹ ከሲዖል የወጡት በዕለተ ዐርብ በሠርክ ቢሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚሕ ዕለት እዲታሰብ ታዛለች::

+ጌታችን ምርኮን ማርኮ: ጥጦስ መንገድ ጠራጊ ሆኖለት ወደ ገነት ሲያስገባቸው ለድንግል ማርያም አሳይቷታል:: እመ አምላክም በፍጹም ልቧ ደስ ተሰኝታለች:: አዳምና ልጆቹ እመቤታችንን ከላይ ሆነው እጅ ነስተዋታል:: እርሷ የድኅነታቸው ምክንያት ናትና::

=>አማናዊው ብርሃን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ጨለማችንን በምሕረቱ ያብራልን::

=>+"+ ክርስቶስም እኮ ስለ ሰው ኃጢአት አንድ ጊዜ ሞቶአል:: ኃጢአት የሌለበት ክርስቶስ ጻድቁ ስለ እኛ ሞተ:: ስለ ኃጢአታችን እኛን ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ::
በሥጋ ሞተ: በመንፈስ ግን ሕያው ነው:: ነፍሳቸው ታስራ ወደ ነበረችበት ሔደ:: ቀድሞ ክደውት ለነበሩት ነጻነትን ሰበከላቸው:: +"+ (1ዼጥ. 3:18)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >
2 views04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 13:55:34
3 views10:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 04:25:02
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
"ኢየሱስም። ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤"
የዮሐንስ ወንጌል 11 :25- 26
3 views01:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 04:23:14
3 views01:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 04:23:14
2 views01:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ