2023-02-18 20:02:20
ራሳቸው (አባ ጳውሎስ) በጉባኤ እንደተናገሩት በገጠር ያሉ ድኾች አብያተ ክርስቲያናት የሚረዱበት አጥተው በሙታን ሴቶች ቀሚስ እየተቀደሰ ይኽን የሚሰሙ ምእመናንን ናቸው ዝም ብለው የሚያጨበጭቡ፡፡ ደግሞስ በቤተ ክርስቲያን ላይ ደም እየፈሰሰ ደም አፍሳሽ ቅዱስ ነው እንዴ? ደም አፍሳሽ ቅዱስ ነው? ይኼንን የአዲስ አበባ ሕዝብ ዐይኑ አይቶ የለምን? ሰምቶስ የለምን? ከዚኽ ነው ቅዳሴ የሚያገኘው?
ጥያቄ ፦ ሰው በቤተ ክርስቲያን ተገኝቶ አስቀድሶ ሥጋ ወደሙን ለመ ቀበል ለምን ተከለከለ?
አለቃ አያሌው ፦ እኔ አልከለከልኩም፡፡ የሚያቀብላችሁ ከአገኛችሁ ቅዳሴ የሚቀድስ ቄስ ጳጳስ ከአላችሁ እኔ አልከለከልኩም የላችሁም እንጂ፡፡
ጥያቄ ፦ የጌታ ሥጋ ወደሙን በካህናት አባቶች እጅ አትቀበሉ፡፡ የፓትር ያርኩ ተባባሪዎች ናቸው ለምን ተባለ?
አለቃ አያሌው ፦ ሥልጣነ ክህነት የላቸውም እኮ ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ የፓትርያርኩ ተባባሪ የኾነ ኹሉ ሥልጣነ ተክህኖ የለውም፡፡ ምክንያቱም ሚያዝያ 3ዐ ቀን 1988 ዓ. ም. የወጣው ሕግ ሲኖዶሱ የፈረ መብት ሕግ እስከዛሬ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የምትሠራባቸውን ደንቦችንና ሕጐችን አሻሻሎ የሚመራና ለሲኖዶሱ ተጠሪ የነበረው ፓትርያርክ በመንፈስ ቅዱስ ፈንታ መሪ እንዲኾን አመራር ሰጪ እንዲኾን ፈቅዶ ቤተ ክርስቲያንንና አባላቷን የፓትርያርክ አባ ጳውሎስ ተጠሪ እንዲኾኑ አድርጓል፡፡
ከዚያ ጊዜ ወዲህ ጳጳሳትም ቀሳውስትም ራሳቸውን ሽረው የአባ ጳውሎስ ፍጡራን ስለኾኑ አባ ጳውሎስ ደግሞ ሥልጣነ ክህነት የመስጠት መብት ስለሌላቸው አሁን ዛሬ የሚቀድሱ የሚያወድሱ ካህናት ቄሶችም ጳጳሳትም የሉንም፡፡ ስለዚህ ከአሏችሁ አልቃወምም፡፡
ጥያቄ ፦ የእናንተ የሃይማኖት አባቶች ፍቅር መጥፋት ለመናፍቃን በር አይከፍትም ወይ? ዛሬ ዛሬ መናፍቃን”…በእነርሱ በኩል ፍቅር ጠፍቷል፡፡ እንደምታይዋቸው አንዱ አንዱን እየወገዘ ነው ያሉት” እያሉ ይሣለቁብናል፡፡ በእርስዎ በኩል ይኼን እንዴት ያዩታል?
አለቃ አያሌው ፦ ፍቅር እኮ አልጠፋም፡፡ ግን በእግዚአ ብሔር ቀልድ የለም፡፡ በእግዚአብሔር አድማ የለም፡፡ አድማ እኮ ነው፡፡ ምን አጣላን? ምንም ፀብ የለንም፡፡
ጥያቄ ፦ ይኸ ውግዘት የተላለፈው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው? ወይስ ለአዲስ አበባ ከተማ ብቻ?
አለቃ አያሌው ፦ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ነው፡፡ በዓለም ላሉ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፡፡
ጥያቄ ፦ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀልን በካህን አባቶች እጅ አትሳለሙ ለምን ተባለ?
አለቃ አያሌው ፦ መስቀል ብቻውን መባረኪያ አይኾንም፡፡ ታዲያ ለምን አንጥረኛው አይባርክበትም፡፡ ነጋዴው ለምን አይባርክበትም? ለምንድን ነው? መስቀሉ ዕኩል ነው፡፡ የሠራው አንጥረኛው ነው፡፡ የሸጠውም ነጋዴው ነው፡፡ ቄሱ ብቻ ስለያዘው መባረኪያ የሚኾነው ለምንድን ነው? የመባረክ ሥልጣን ያለው ቄሱ ብቻ ስለኾነ ነው፡፡ ያ ቄስ ደግሞ እግዚአብሔርን ከካደ በረከት የለውም ማለት ነው፡፡ በትንቢተ ሚልኪያስ”እናንተ ካህናት ስሜን አርክሳችኋልና እኔም በረከቴን ከእናንተ ወስጃለሁ፡፡” ይላል፡፡
ጥያቄ ፦ ውግዘት ከተላለፈ ወዲህ ብዙ እናት አባቶች እኀት ወንድሞች ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ አሉ፡፡ እነዚኽ ሰዎች እንደተወገዙ ነው የሞቱት ወይስ ተፈትተው? ይኼንንም ቢያብራሩልን?
አለቃ አያሌው ፦ ትእዛዜን አክብረው ከኾነ ተፈትተዋል፡፡ ከአላከበሩ ግን እስረኞች ናቸው፡፡
ጥያቄ ይኼን ውግዘት በግል ጋዜጣ ከማስተላለፍዎ በፊት ለምን በእየቤተ ክርስቲያኑ ተገኝተው ለምእመኑ አላስተላለፉም?
አለቃ አያሌው ፦ እኔማ ታግጃለሁ፡፡ ስለታገድኩ እኮ ነው በግል ጋዜጣ ለመተንፈስ የበቃሁት እንጂ ይኽንንማ ዕድል ከአገኘኹ ለምን በጋዜጣ እናገራለሁ፡፡ በመድረክ ላይ ነበር የምናገረው፡፡ ጥር 24 ቀን 1988 ዓ.ም. በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፉ መበላሸቱን ተናግሬአለሁ፡፡ ከዚያ ቀደም ብሎም አንድ ዓመት ሙሉ ሲኖዶሱ እንዲያየው በደብዳቤም በቃልም ተናግሬያለሁ እምቢ ስላሉ እንደጌታ ቃል ነው ያወገዝኩኝ፡፡ ከዚያ ውጪ አልሔ ድኹም፡፡ «መጀመሪያ ጠይቅ፡፡”እምቢ” ሲሉ ለቤተ ክርስቲያን ንገር ከዚያ በኋላ አውግዝ…» ነው ያለ፡፡ እንዳዘዘኝ ነው ያደረግኹት፡፡
ጥያቄ ፦ ይኸ ውግዘት እስከመቼ ነው የሚቆየው? ለምን?
አለቃ አያሌው ፦ እስከተፈታ ድረስ፡፡ ነገሩ ውሳኔ ከአላገኘ ያው ነው፡፡ አርዮስ ተፈቷልን? መቅዶንዮስስ ተፈቷልን? ንስጥሮስስ ተፈቷልን? አሁንም በዚህ ዓለም ብቻ አይደለም፡፡ በውዲያኛውም ዓለም ውጉዛን እሱራን ናቸው፡፡ በሥልጣነ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እሱራን ውጉዛን ይኹኑ፡፡
ጥያቄ ፦ አባ ጰውሎስ”የግል ጋዜጣ ገዝታችሁ አታንብቡ” ብለው አውግዘዋል፡፡ የእርስዎ ውግዘት የተላለፈው ደግሞ በግል ጋዜጣ ነው ይኼ ሊጋጭ አይችልም ወይ?
አለቃ አያሌው ፦ ምን ያጋጨዋል? እሳቸውም እንደ ዐመፁ ናቸው፡፡ እኔም ከእግዚአብሔር ጋራ እንደቆምኩ ነኝ፡፡ ምን ይጋጫል? መጀመሪያ ጸባቸው የማይኾን ኾኖ ወጡ፡፡ ከወጡ በኋላ የሚያደርጉት ነገር የላቸውም፡፡ እውነት ከኾነ ውግዘቱን ለማ ገድ ከመሞከር ወይም”የግል ጋዜጣ አታንብቡ” ብሎ ከማስገደድ የሊ ቃውንት ጉባኤን ከማገድ ሲኖዶሱን ከማፍረስ ይልቅ የሊቃውንት ጉባ ኤውም እንዳለ ሲኖዶሱም እንዳለ እኔን አቅርበው መጠየቅ ነበረባቸው እውነቱ ይኼ ነው፡፡
ጥያቄ ፦ ካህናት ለምን ይወገዛሉ? አጥፊው ሌላ ነው፡፡ ደግሞም ከሥራ ቢፈናቀሉ ችግር ላይ ይወድቃሉ፡፡
አለቃ አያሌው ፦ከቤተ ክህነት የሚያገኙት ገንዘብ የለም ለልብሳችን ለምግባችን ብለው ሊመካኙ አይችሉም፡፡ ደግሞ ከዚህ ነፃ ካልወጡ ካህናት አይደሉም፡፡ ጌታ ራሱ አንድ ባሪያ ለኹለት ጌታ መገዛት እንደማይችል እናንተም «…ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ ልት ገዙ አትችሉም…» ነው ያለው፡፡ ይኽንን ሲያብራራ ነገሩን በዚህ ብቻ ሳይወስን ምክንያቶቹ ገንዘብ ፈለጋ የሚሰዱን ልብስና ምግብ ስለኾኑ «ምን እንበላለን? ምን እንለብሳለን? ብላችሁ አታመካኙ፡፡ ወፎችን አበቦችን እዩ» ብሎ በገንዘብ ምክንያት ከእሱ እንዳንለይ አዝዟል ከዚህ በላይ ከአልኼድን ስንኳን ካህንነቱ ምእመንነቱም አይኾንም፡፡
ካህናትማ ከዚህ በላይ መሔድ አለብን፡፡ አንድ በጐቹን ለመጠበቅ የተሰየመ እረኛ ዐቅሙ እስከ ፈቀደ ድረስ ከአራዊት ጋራ ተከላክሎ በጐቹን ማዳን አለበት፡፡ እሱ መሞት አለበት እንጂ እነሱን አሳ ልፎ መስጠት የለበትም፡፡ ስንኳን ለጥቅም ብሎ አሳልፎ ሊሰጣቸው ስለሕይወቱም አሳልፎ ሊሰጥላቸው ነው የታዘዘው፡፡ ጌታ ራሱ”ስለበጐቼ ራሴን እለውጣለሁ” ነው ያለው፡፡ ይኽንንም ለሐዋርያቱ ለካ ህናቱ ሊያስተላልፍ”ራሱን ለወንድሙ ለውጥ አድርጐ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር ምን አለ?” ብሎ ነው እንድንቀበለው የአዘዘን፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰዎች የኾንን ኹሉ አስተማሪዎች የኾንን ኹሉ ስንኳን በምግብ በልብስ ልናመካኝ ይቅርና ስለምእመናን ራሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ተጠይቀናል፡፡
ጥያቄ ፦ ከኹለት አንዳችሁ ከዚህ ዓለም በሞት ብትለዩ ወግዘቱ እንደታሠረ ይቀራልን? ወይስ ይፈታል?
2 views17:02