2023-01-07 21:10:10
من أنت عند الله ؟؟؟
“አንተ”/“አንቺ” አሏህ ዘንድ ምን ያህል ደረጃ አለህ/ አለሽ?
احرص ان تكون من خير الخلق !
አሏህ ዘንድ ከሁሉም የተሻለ ፍጥረት ለመሆን ጣር!
قال تعالى : إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ
"አሏህ ዘንድ በላጩ አሏህን ይበልጥ የሚፈራው ነው።
قال ﷺ : (خيركم من تعلم القرآن وعلمه) البخاري
«ከናንተ ውስጥ በላጫችሁ ቁርዓንን ቀርቶ ያስቀራ ነው ።»
قال ﷺ (خياركم أحاسنكم أخلاقا) البخاري
«ከናንተ ውስጥ በላጫችሁ ስነምግባሩ ያማረው ነው ።»
قال ﷺ (خياركم في الجاهلية خياركم في الإسلام إذا فقهوا) البخاري
"ጃሂሊያ ላይ በላጭ የነበረ እስልምናም ላይ በላጭ ይሆናል ከተማሩና ዲኑን ከተረዱ"
قال ﷺ ( خيركم أحسنكم قضاءً) البخاري
"ከሰዎች በላጫቸው ዕዳውን ሲከፍል አሳምሮ ሚከፍል ነው"
قال ﷺ (خيركم خيركم لأهله) صحيح ابن حبان
«ከናንተ በላጫቻችሁ ለሴቶቻቸው በላጭ የሆኑት ናቸው»
" قال ﷺ ( خير النساء التي تسره إذا نظر، وتطيعه إذا أمر، ولا تخالفه في نفسها ولا مالها بما يكره».
"ከሴቶች ሁሉ በላጭ ስታያት የምታስደስትህ፣ ስታዛት የምትታዘዝህ፣ ስትርቅ እራሷንም ገንዘብህንም የምትጠብቅ ናት።"
قال ﷺ (خيركم من أطعم الطعام وردَّ السلام) صحيح الجامع
«በላጫችሁ ምግብን ያበላ እና ሰላምታን የመለሰ ነው»
قال ﷺ (خيركم من يُرجى خيره ويُؤمٓن شره) صحيح الترمذي
«በላጭ ሰው ማለት ከርሱ መልካም የሚከጀልና መጥፎው የማይፈራ ሰው ነው።»
قال ﷺ (خير الناس أنفعهم للناس) صحيح الجامع
"ከሰዎች ውስጥ በላጭ የሆነው ጠቃሚው ነው"
قال ﷺ ( خير الناس ذو القلب المخموم واللسان الصادق ) صحيح الجامع
"ከሰዎች ውስጥ በላጭ ቀልብ ንፁህ [አላህን የሚፈራ ያ በሱ ላይ ድንበር ማለፍ የሌለበት ነው] እና ሐቅ ተናጋሪ የሆነው ነው።"
قال ﷺ (خير الأصحاب عند الله خيركم لصاحبه، وخير الجيران عند الله خيركم لجاره) صحيح الأدب
«አላህ ዘንድ በላጭ ባልደረባ ማለት ለባልደረባው በላጭ የሆነው ነው አላህ ዘንድ በላጭ ጎረቤት ማለት ለጎረቤቱ በላጭ የሆነው ሰው ነው።»
قال ﷺ (خيار أئمتكم الذين تحبونهم ويحبونكم) مسلم
"ከመሪያችው በላጭ የሆነው የምትወዷቸው እና የሚወዳችው ናቸው"
قال ﷺ ( خير الناس من طال عمره وحسن عمله) صحيح الجامع
"በላጭ ሰው እድሜው ረዝሞለት ስራውም ያማረለት ነው አሉ።»
@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
576 views18:10