Get Mystery Box with random crypto!

❥ ዳሩል ኢስላም/Darul Islam ❥

የቴሌግራም ቻናል አርማ darul_islam_channal — ❥ ዳሩል ኢስላም/Darul Islam ❥
የቴሌግራም ቻናል አርማ darul_islam_channal — ❥ ዳሩል ኢስላም/Darul Islam ❥
የሰርጥ አድራሻ: @darul_islam_channal
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.06K
የሰርጥ መግለጫ

وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ
صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?
ለአስተያየት☞☞ @Darulisalam_bot ለይ ይላኩልን
ለጥያቄ ☞ @Hayatbintkedir ለይ ይላኩ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2022-09-09 22:47:23 ሰዓት አልቆዋል
954 views19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 21:17:40 ሁለተኛው ዙር / ዙር ②/ ጥያቄ
ከታች ዳሹን መሙላት እንዳትዘነጉ
ሙሉ ስድስት ጥያቄዎችን ይዞዋል

የመጀመሪያው ዙር አብዛኞቻችሁ የከበዳችሁ ይመስላል በዝሂኛውም ድክመት እንዳላይ ቆፍጠን በሉ አላህ ይጨምርላችሁ

መልካም እድል
አንድ ሰዓት ከ30 ደቂቃ አላቹህ

መልስ መስጫ @RemedanM ላይ

1) ከበደሎች ሁሉ እጅግ የከፋው ትልቁ በደል ምንድነው?
ሀ) ግድያ
ለ) በአላህ ማጋራት (ሺርክ)
ሐ) ሐሜት
መ) ድግምት

2) የቀብር ዓለም መጠሪያው?
ሀ) ሰክረህ
ለ) በርዘኽ
ሐ) ዐዛብ

3) ሱጁድ በሚወረድበት ጊዜ መሬት መንካት የሌለበት
ሀ) የእግር አውራ ጣት
ለ) ግንባር
ሐ) አፍንጫ
መ) ክንድ

4) የጀነት ሰዎች ቁመት?
ሀ) ስልሳ ሜትር
ለ) ሰላሳ ክንድ
ሐ) ስልሳ ክንድ
መ) አርባ ክንድ

5) የሒራ ዋሻ የሚገኝበት ተራራ?
ሀ) ኑር
ለ) ሰውር
ሐ) ሒራ

6) የቂያማ ቀን ወደ አንድ ጎኑ አጋድሎ/ተጣሞ/ የሚነሳ ሰው ………………
1.2K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 21:07:12 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

ዛሬ የጁሙአ

የጥያቄና መልሱ ውድድር ሁለተኛ ዙር ጥያቄው ይፖሰት ዝግጁ ናችሁ

ላለፈው ሳምት ሚስ ለተደረገው ሁላችሁንም ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን

ሼር ለማድረግ ለሚሳተፍ
ሚቀርብበት ቻናል
@Darul_Islam_channal
1.1K viewsedited  18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 15:09:39


የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች


ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው፡፡ ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ እምነትን የሚጎዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ፡፡ በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ፡፡ በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ፡፡ ጥንቆላና ድግምት 
- ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
)وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ( البقرة: ١٠٢
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ፡፡ ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና፡፡) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ፡፡” [አልበቀራህ፡ 102] ነብዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ በወረደው ክዷል፡፡} [አስሶሒሐህ፡ 3387]
- ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም፡፡ ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም፡፡” [ጧሃ፡ 69] 
- ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው፡፡ ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው፡፡ ነብዩ ዐለይሂስሰላም እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም፡፡ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ፡፡} [አስሶሒሐህ፡ 946]
- ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው፡፡ የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ፡፡ በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ 
- ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም፡፡} [ሙስሊም፡ 5957]
2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው፡፡ እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት፡፡ በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም፡፡ ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል፡፡ ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ፡፡ በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ፡፡ ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ፡፡ በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?!! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ፡፡
3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው፡፡ አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ፡፡ ነገሩ እጅጉን የፈጠጠ እውነታ ሆኖ ሳለ በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው፡፡ ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣ አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣ የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ “እንኳን ከዘመነ ምንትስ ወደ ዘመነ ምንትስ አደረሳችሁ” ማለታቸው ጥሩ ጠቋሚ ናቸው፡፡
ስለዚህ ከየትኛውም ከአይሁድ፣ ከክርስቲያን እና ከሌሎች እምነቶች ጋር ከሚያመሳስሉ ነገሮች እራስን መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ይላሉና፡፡
ወሶለላሁ ዐላ ነቢይዪና ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊሂ ወሶሕቢሂ ወሰለም
        

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
715 views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 19:46:34

እርዝ



ሀ. ትርጉሙ፦
እርዝ ከክፋት ይጠብቅ ዘንድ ታሽጎ አንገት ላይ የሚንጠለጠል ፅሁፍ፣ ክሮች፣ አጥንቶች የመሳሰሉ ነገሮች ሲሆን ድሮ ዓረቦች በተሳሳተ አመለካከታቸው ልጆችን ከሰው አይን ለመከላከል የሚያንጠለጥሉላቸው ጥቅምን ለማግኘት ወይም ጉዳትን ለመከላከል በማሰብ የሚደረግ ነው፡፡

ለ. ሸሪዓዊ ብይኑ፦
ሀራም (የተከለከለ) ከመሆኑም በላይ ከሽርክ አይነቶች አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱ ከአላህ ውጭ በሆነ ነገር መንጠልጠል ነው፡፡
ክፉን መካች አላህ ብቻ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ጎጂን ነገር መከላከል ያለበት በአላህ በስሞቹና በባህሪያቱ ብቻ ነው፡፡
ኢብኑ መስዑድ እንዳሉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው ‹‹ሩቃ፣ እርዝና መስተፋቅር መስራት ሽርክ ነው”

አብደላህ ኢብኑ ዑከይም እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “በአንድ ነገር ላይ የተንጠለጠለ ወደ ለርሱ ይተዋል”
ዑቅበት ኢብን ዓሚር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “እርዝን ያንጠለጠለ አላህ አይሙላለት፣ ዛጎልንም ያንጠለጠለ አላህ አይተውለት”
ዑቅበት ኢብን ዓሚር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “እርዝን ያንጠለጠለ ሽርክን ፈፅሟል”

እነዚህና መሰል ጥቅሶች ዓረቦች በብዛት ሲያንጠለጥሉት የነበሩትን ሽርካዊ እርዞች የሚከለክሉ ሲሆኑ የተከለከሉትም ከአላህ ውጭ በሆነ ፍጡር ላይ መንጠልጠል በመሆኑ ነው፡፡

ሐ. የሚንጠላጠለው ፅሑፍ የቁርአን ቃል ከሆነ፦
ዑለማዎች በዚህ ዙሪያ አልተስማሙም ከፊሉ የሚፈቅድ ሲሆን ሌላው ደግሞ ይከለክላል፡፡ ቁርአንን ለፈውስ ማንጠልጠል አይቻልም የሚሉ አቋሟቸው ከአራት ምክንያቶች አንፃር ሲታይ ትክክል ነው፡፡

1. ነብዩ እርዝን የከለከሉት በጥቅሉ ሲሆን ይህን አይነቱን ነጥሎ የሚያወጣ ማስረጃ አለመኖሩ፡፡
2. ይህን መፍቀድ ከቁርአን ያልሆነን ፅሁፍ ለማንጠልጠል መንገድ ስለሚከፍትና ወደ መጥፎ የሚመራን መንገድ መዝጋት ደግሞ ተፈላጊ ስለሆነ::
3. አንጠልጣዩ በመፀዳጃ፣ በኢስቲንጃና በመሳሰሉት ቦታ ይዞት ስለሚገኝ ቁርአንን ዝቅ የሚያደርግ በመሆኑ፡፡
4. በቁርአን መፈወስ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት ስለተገለፀ (እሱም ህመምተኛው ላይ መቅራት ነው) እና ይህን መተላለፍ ስለማይቻል



@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
644 views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 16:56:32 ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
‹‹አጫጭሱላቸው››፣ በሽርክ አይሳቅም፡፡ 
በአላህ ፈቃድ ወደ መደበኛ ትምህርታችን እንመለሳለን፡፡ ሽርክ አላህ ታላቅ በደል ብሎ የጠራው ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም) ታላላቅ አጥፊ ወንጀሎችን ሲጠቅሱ ከሽርክ ነው የጀመሩት፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መዲና ተቀምጠው የመን ውስጥ የምትመለከዋ ቀብር እረፍት ነሳችኝ ብለው ነበር፡፡ ዛሬ አላህ ካዘነላቸው ውጭ፣ የሽርክ ጉዳይ ብዙም ቦታ አይሰጠውም ዱዓት በሚባሉት ዘንድ፡፡ አላህ ሁሉንም ተጣሪዎች ነብያቱን አስታጥቆ ወደላከበት አርስት ተውሂድ ይመልሳቸው፡፡ 
በሶዎች ሞባይል ውስጥ በተለይ በጫት ቃሚዎች መሃል አንድ በ ብሉ ቱዝ የሚቀባበሏት አፉ ላይ ጫት የያዘ ወጣት የሚያንጎራጉራት የሽርክ ስንኞች፣ አደብ ማጣት እና ኹራፋት ውስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ
1) ‹‹የቦረናው ጌታ ነው እንደ ጡላጊ፣
ትልቁን ጠቃሚ፣
ትንሹን አሳዳጊ››
ይሄ ስንኝ በግልፅ የአላህን መብት አሳልፎ ለቦረናው ሸይኽ እየሰጠ ነው፡፡ ጠቃሚ ጎጂ፣ ሰጪ ነሺ አላህ ብቻ ነው፡፡ አላህ ብቻ ሊያደርገው በሚችለው ጉዳይ ፍጡራንን መጥራት ሽርክ እና ኩፍር ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ደግሞ ከአላህ ውጭ ያለን እየጠራ የሞተ እሳት ገባ ብለዋል፡፡ ነፍሳችንን፣ ቤተሰቦቻችንን ከእሳት በአላህ ፈቃድ በታደግ ግድ ይለናል፡፡ ተውሂድን መማር እና ማስተማር ከምንም በፊት የሚቀደም
 
ቴሌግሪም ቸናልአቺንን ተቀላቀሉ

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
921 views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:55:55 በነብዩ ላይ ሰላትና ሰላም ማብዛት
የሶላት አለነብይ ፋኢዳና ትሩፋት

قال العلامة السعدي رحمه الله:

«الإكثار من الصلاة على النبي ﷺ فيها غفران الزلات وتكفير السيئات وإجابة الدعوات وقضاء الحاجات وتفريج المهمات والكربات وحلول الخيرات والبركات ورضا رب الأرض والسماوات وهي نور لصاحبها في قبره منجية من الشرور والآفات».
[الفواكه الشهية (٤١)]

አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
245 views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 15:57:22 አስብ ሞት እንዳለብህ

እንደሞት ማን መካሪ ነበር!? ሞት ያላስተማረው ሰው በምን ይማራል? ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ጥፍጥናዎችን ቆራጭ የሆነውን (ሞትን) ማስታወስን አብዙ" ማለታቸው ለዋዛ አልነበረም። ምን ዋጋ አለው ዛሬ ከሞትም የምንማረው ጥቂቶች ሆነናል። በቤተሰባችን፣ በጓደኛችን ሞት ከማዘን ከማንባት በዘለለ "ድንገት ተረኛ ብሆንስ?" ብለን ተጨንቀን ላፍታ እንኳን የቀብር ህይወትን፣ ቂያማን፣ ሲራጥን፣ ሚዛንን ወዘተ አስታውሰን በመዘናጋታችን የደነገጥነው ከሰመመናችን የነቃነው ስንቶቻች ነን? 
እኩይ ምግባርን ባህሪህ ያደረግከው ወገኔ ሆይ ከፊትህ ሞት አለ። የሰው ሐቅ ያለ አግባብ የምትነጥቀው ብልጥ መሳዩ ቂል ሆይ ከፊትህ ሞት ተደቅኗል። ሃሜተኛው ነገረኛው ፍጥረት ሆይ የስራህን ታጭድ ዘንድ ሞት ከፊትህ እየጠበቀህ ነው። በሶላትህ የምትቀልደው የምትዘናጋው ቦዘኔ ሆይ! ዘላለማዊ ቁጭትን የሚያወርስህ ሞት ተደግሶልሃል። የወላጆችህን ሐቅ የምትጥሰው አደራ በላ ሆይ ዛሬ ነገ ሳትል በፍጥነት እራስህን አስተካክል፣ ከጌታህ ጋር ታረቅ፡፡ በጥቅሉ ለጌታህ ለዲንህ ጀርባህን የሰጠኸው ዝንጉ ሆይ! ሞት ወደ አንተ እየመጣ ነው፡፡ ወንድሜ ሆይ እህቴ ሆይ ወደ ጌታችን እንመለስ፡፡ ጧት ማታ ሞትን እናስታውስ፡፡ አንዱ ዓሊም እንዲህ ይላሉ፡ “ሞትን ማስታወስን ያበዛ ሰው ሶስት ነገሮችን ይታደላል፡፡ እነሱም ተውባን ማፋጠን፣ የልብ መብቃቃት እና ለዒባዳህ መነሳሳት፡፡ ሞትን የረሳ ደግሞ በሶስት ነገሮች ይቀጣል፡፡ ተውባን እየተዘናጉ ማሳለፍ፣ ባለ አለመብቃቃት እና ከዒባዳህ መዘናጋት፡፡” እስኪ እራሳችንን እንገምግም፡፡ ሞት አማክሮ አይመጣምና በተጠንቀቅም እንሁን፡፡ ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ “ካመሸህ ንጋትን አትጠባበቅ፡፡ ካነጋህ ደግሞ ምሽትን አትጠባበቅ፡፡ በጤናህ ጊዜም ለህመምህ ጊዜ የሚሆንህን፤ በህይወት ሳለህም ስትሞት የሚሆንህን ያዝ” ይላሉ፡፡ በጥፋት የምንጠምዳቸው የአካል ክፍሎቻችን በኛ ላይ ምስክር ከመሆናቸው በፊት እንንቃ፡፡ ሞት የትና መቼ እንደሚይዘን አናውቅምና አዋዋላችንን እናሳምር፣ ባስቸኳይ ወደ አላህ እንመለስ፡፡ ጌታዬ ሆይ ይቅር በለን። አንተን በማስታወስ፣ አንተን በማመስገን፣ አንተን ባማረ መልኩ በመገዛትም ላይ አግዘን። 
አንተ የቆምከው ከቀብሬ
አትደነቅ በነገሬ
እንዳንተው ነበርኩኝ ትላንት
የዘነጋሁ ከዚህ መዐት
ይልቅ ተመከር አንሰራራ
ነገ አንተ ነህ ባለ ተራ

         ።ቴሌግራም ቸናላቺን ተቀላቀሉ

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
482 viewsedited  12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:36:57
እውነተኛ መሀይም(ጃሂል) ብሎ ማለት መፃፍ እና ማንበብ የማይችል ሰው ሳይሆን ።

የቂብላን አቅጣጫ ካወቃ በኋላ የማይሰግድ ሰው ነው።

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
618 viewsedited  18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:18:18 እህቴ ለምን ይሆን ይህን መልበስሽ?
የምእራባውያንን መንገድ መከተልሽ?
የተወዳጆቹን ምእመናት ልብስ መተውሽ?
እኮ ለምን?
እነርሱ እኮ ለኢስላም ያላቸውን ጥላቻም እያንፀባረቁ ይሆናል፣ይህንን ተገንዝበሻል?
በነፃነት ስም እርቃንሽን እንዳስኬዱሽ፣እንዳስቀሩሽ?
መለስ በይ ወደ ጌታሽ
ሞት እንደሆነ እድሜሽን ሳይጠይቅ፣
ምክኒያት ሳይፈልግ ያንኳኳል በርሽን በድንገት ሊወስድሽ፣
ታዲያ ለምን ይሆን መልበስሽ?
ጌታሽ ፊት ቆመሽ ስትጠየቂ?ስትተሳሰቢ
ጌታሽ ለምን እንደለበሽው ምክኒያቱን ሲጠይቅሽ
በተመለከተሽ ወጣት ዓይን ልክ
እርቃንሽን ባየሽ ሰው መጠን
ያኔ ለምን ለበሽ ? ስትባይ
መልስ የለሽም ከፀፀት በቀር
አስቢበት ዱንያ ምን ብታስደስት አጭር እና ጠፊ ነች።
ተመለሽ ጊዜው ሳያልፍ ፀፀት የማይጠቅምበት ጊዜ
ከመምጣቱ በፊት

ቴሌግራም ቸናል

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal
1.4K views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ