Get Mystery Box with random crypto!

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ‹‹አጫጭሱላቸው››፣ በሽርክ አይሳቅም፡፡  በአላህ ፈቃድ ወደ መደ | ❥ ዳሩል ኢስላም/Darul Islam ❥

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
‹‹አጫጭሱላቸው››፣ በሽርክ አይሳቅም፡፡ 
በአላህ ፈቃድ ወደ መደበኛ ትምህርታችን እንመለሳለን፡፡ ሽርክ አላህ ታላቅ በደል ብሎ የጠራው ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም) ታላላቅ አጥፊ ወንጀሎችን ሲጠቅሱ ከሽርክ ነው የጀመሩት፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መዲና ተቀምጠው የመን ውስጥ የምትመለከዋ ቀብር እረፍት ነሳችኝ ብለው ነበር፡፡ ዛሬ አላህ ካዘነላቸው ውጭ፣ የሽርክ ጉዳይ ብዙም ቦታ አይሰጠውም ዱዓት በሚባሉት ዘንድ፡፡ አላህ ሁሉንም ተጣሪዎች ነብያቱን አስታጥቆ ወደላከበት አርስት ተውሂድ ይመልሳቸው፡፡ 
በሶዎች ሞባይል ውስጥ በተለይ በጫት ቃሚዎች መሃል አንድ በ ብሉ ቱዝ የሚቀባበሏት አፉ ላይ ጫት የያዘ ወጣት የሚያንጎራጉራት የሽርክ ስንኞች፣ አደብ ማጣት እና ኹራፋት ውስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ
1) ‹‹የቦረናው ጌታ ነው እንደ ጡላጊ፣
ትልቁን ጠቃሚ፣
ትንሹን አሳዳጊ››
ይሄ ስንኝ በግልፅ የአላህን መብት አሳልፎ ለቦረናው ሸይኽ እየሰጠ ነው፡፡ ጠቃሚ ጎጂ፣ ሰጪ ነሺ አላህ ብቻ ነው፡፡ አላህ ብቻ ሊያደርገው በሚችለው ጉዳይ ፍጡራንን መጥራት ሽርክ እና ኩፍር ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ደግሞ ከአላህ ውጭ ያለን እየጠራ የሞተ እሳት ገባ ብለዋል፡፡ ነፍሳችንን፣ ቤተሰቦቻችንን ከእሳት በአላህ ፈቃድ በታደግ ግድ ይለናል፡፡ ተውሂድን መማር እና ማስተማር ከምንም በፊት የሚቀደም
 
ቴሌግሪም ቸናልአቺንን ተቀላቀሉ

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal