Get Mystery Box with random crypto!

አስብ ሞት እንዳለብህ እንደሞት ማን መካሪ ነበር!? ሞት ያላስተማረው ሰው በምን ይማራል? ነብ | ❥ ዳሩል ኢስላም/Darul Islam ❥

አስብ ሞት እንዳለብህ

እንደሞት ማን መካሪ ነበር!? ሞት ያላስተማረው ሰው በምን ይማራል? ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ጥፍጥናዎችን ቆራጭ የሆነውን (ሞትን) ማስታወስን አብዙ" ማለታቸው ለዋዛ አልነበረም። ምን ዋጋ አለው ዛሬ ከሞትም የምንማረው ጥቂቶች ሆነናል። በቤተሰባችን፣ በጓደኛችን ሞት ከማዘን ከማንባት በዘለለ "ድንገት ተረኛ ብሆንስ?" ብለን ተጨንቀን ላፍታ እንኳን የቀብር ህይወትን፣ ቂያማን፣ ሲራጥን፣ ሚዛንን ወዘተ አስታውሰን በመዘናጋታችን የደነገጥነው ከሰመመናችን የነቃነው ስንቶቻች ነን? 
እኩይ ምግባርን ባህሪህ ያደረግከው ወገኔ ሆይ ከፊትህ ሞት አለ። የሰው ሐቅ ያለ አግባብ የምትነጥቀው ብልጥ መሳዩ ቂል ሆይ ከፊትህ ሞት ተደቅኗል። ሃሜተኛው ነገረኛው ፍጥረት ሆይ የስራህን ታጭድ ዘንድ ሞት ከፊትህ እየጠበቀህ ነው። በሶላትህ የምትቀልደው የምትዘናጋው ቦዘኔ ሆይ! ዘላለማዊ ቁጭትን የሚያወርስህ ሞት ተደግሶልሃል። የወላጆችህን ሐቅ የምትጥሰው አደራ በላ ሆይ ዛሬ ነገ ሳትል በፍጥነት እራስህን አስተካክል፣ ከጌታህ ጋር ታረቅ፡፡ በጥቅሉ ለጌታህ ለዲንህ ጀርባህን የሰጠኸው ዝንጉ ሆይ! ሞት ወደ አንተ እየመጣ ነው፡፡ ወንድሜ ሆይ እህቴ ሆይ ወደ ጌታችን እንመለስ፡፡ ጧት ማታ ሞትን እናስታውስ፡፡ አንዱ ዓሊም እንዲህ ይላሉ፡ “ሞትን ማስታወስን ያበዛ ሰው ሶስት ነገሮችን ይታደላል፡፡ እነሱም ተውባን ማፋጠን፣ የልብ መብቃቃት እና ለዒባዳህ መነሳሳት፡፡ ሞትን የረሳ ደግሞ በሶስት ነገሮች ይቀጣል፡፡ ተውባን እየተዘናጉ ማሳለፍ፣ ባለ አለመብቃቃት እና ከዒባዳህ መዘናጋት፡፡” እስኪ እራሳችንን እንገምግም፡፡ ሞት አማክሮ አይመጣምና በተጠንቀቅም እንሁን፡፡ ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ “ካመሸህ ንጋትን አትጠባበቅ፡፡ ካነጋህ ደግሞ ምሽትን አትጠባበቅ፡፡ በጤናህ ጊዜም ለህመምህ ጊዜ የሚሆንህን፤ በህይወት ሳለህም ስትሞት የሚሆንህን ያዝ” ይላሉ፡፡ በጥፋት የምንጠምዳቸው የአካል ክፍሎቻችን በኛ ላይ ምስክር ከመሆናቸው በፊት እንንቃ፡፡ ሞት የትና መቼ እንደሚይዘን አናውቅምና አዋዋላችንን እናሳምር፣ ባስቸኳይ ወደ አላህ እንመለስ፡፡ ጌታዬ ሆይ ይቅር በለን። አንተን በማስታወስ፣ አንተን በማመስገን፣ አንተን ባማረ መልኩ በመገዛትም ላይ አግዘን። 
አንተ የቆምከው ከቀብሬ
አትደነቅ በነገሬ
እንዳንተው ነበርኩኝ ትላንት
የዘነጋሁ ከዚህ መዐት
ይልቅ ተመከር አንሰራራ
ነገ አንተ ነህ ባለ ተራ

         ።ቴሌግራም ቸናላቺን ተቀላቀሉ

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal