Get Mystery Box with random crypto!

እህቴ ለምን ይሆን ይህን መልበስሽ? የምእራባውያንን መንገድ መከተልሽ? የተወዳጆቹን ምእመናት ልብስ | ❥ ዳሩል ኢስላም/Darul Islam ❥

እህቴ ለምን ይሆን ይህን መልበስሽ?
የምእራባውያንን መንገድ መከተልሽ?
የተወዳጆቹን ምእመናት ልብስ መተውሽ?
እኮ ለምን?
እነርሱ እኮ ለኢስላም ያላቸውን ጥላቻም እያንፀባረቁ ይሆናል፣ይህንን ተገንዝበሻል?
በነፃነት ስም እርቃንሽን እንዳስኬዱሽ፣እንዳስቀሩሽ?
መለስ በይ ወደ ጌታሽ
ሞት እንደሆነ እድሜሽን ሳይጠይቅ፣
ምክኒያት ሳይፈልግ ያንኳኳል በርሽን በድንገት ሊወስድሽ፣
ታዲያ ለምን ይሆን መልበስሽ?
ጌታሽ ፊት ቆመሽ ስትጠየቂ?ስትተሳሰቢ
ጌታሽ ለምን እንደለበሽው ምክኒያቱን ሲጠይቅሽ
በተመለከተሽ ወጣት ዓይን ልክ
እርቃንሽን ባየሽ ሰው መጠን
ያኔ ለምን ለበሽ ? ስትባይ
መልስ የለሽም ከፀፀት በቀር
አስቢበት ዱንያ ምን ብታስደስት አጭር እና ጠፊ ነች።
ተመለሽ ጊዜው ሳያልፍ ፀፀት የማይጠቅምበት ጊዜ
ከመምጣቱ በፊት

ቴሌግራም ቸናል

@Darul_Islam_channal
@Darul_Islam_channal