2022-10-04 13:26:05
#በሰሜን ሸዋ ዞን አራት ወረዳዎች የማሽላ ጢንዚዛ ተከሰተ
****************************
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አራት ወረዳዎች የማሽላ ጢንዚዛ መከሰቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
እስካሁን 1 ሺህ 21 ሔክታር የማሽላ ሰብል ላይ ጢንዝዛ የተከሰተ ሲሆን÷ 966 ሔክታሩን በባህላዊ መንገድ ቀሪውን 55 ሔክታር ደግሞ በኬሚካል የመከላከል ሥራ መሠራቱ ተገልጿል፡፡
በመምሪያው የሰብል ልማት ቡድን መሪ አበበ ጌታቸው እንደገለጹት÷ በአንኮበር፣ ጣርማበር፣ ቀወት እና በረኸት ወረዳዎች የማሽላ ጢንዚዛ ተከስቷል፡፡
የቀበሌና የወረዳ ባለሙያዎች ጢንዚዛው በሰብሉ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ÷ በባህላዊ ዘዴ በመልቀም፣ ማሽላውን በማወዛወዝና ጭስ በማጨስ እንዲሁም በኬሚካል የመከላከል ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ጢንዚዛው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊስፋፋ እንደሚችል ትንበያ መኖሩን ጠቁመው÷ ወደ አጎራባች ወረዳዎች እንዳይዛመት ሁሉም አርሶአደርና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያ የመከላከል ሥራው ላይ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በውሸት አካውንት እንዳትሸወዱ ትክክለኛው የቻናሌ ሊንክ ከስር ያለው ብቻ ነው
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
37.7K viewsAyu, 10:26