Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ assebpress — አዲስ መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ assebpress — አዲስ መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @assebpress
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.82K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-02 18:00:13
ሰጋጆችን ገደ'ሏቸው
===============
የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ኃይሎች ወደ አንዋር መስጅድ ካኪና ሙሶላ ይዘው ሃገር ሰላም ብለው ባዶ እጃቸውን የገቡ ሰላማዊ ሰጋጆችን፤ ሶላታቸውን ከጨረሱ በኋላ ሱንና እንኳ እንዲሰግዱ ሳይፈቅዱላቸው ነበር ቀድመው በተዘጋጁበት ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያ ታግዘው የጥይት እሩምታ የከፈቱባቸው።

ሰላታቸውን ሰግደው በሰላም እየተመለሱ በነበሩ ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ አጥብቀን እናወግዛለን!

#ሰጋጁን_ገደሉት
#የአንዋርመስጂድጭፍጨፋ
#ሙስሊምጠልነት
#ኢስላምጠልነት
#AnwarMsjidMassacre
#Islamophobia
#EthiopianMuslimsUnderAttack

||
485 viewsHusen Mohammed, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 17:23:16
አሁንም ይታሰብበት
===============
በአንዋር መስጅድ ውስጥ የሚገኙ ወንድምና እህቶች በር ተቆልፎባቸው ውስጥ ላይ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ገዳ'ዩና ደብዳቢው ኃይል በርካታ አውቶቢሶችን አዘጋጅቷል። ትንሽ መሸት ሲል ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በጅምላ አፍሶ ወደ በርሃ በመውሰድ የእስር ሰቀቀን በማቅመስ ሞራላቸውንና አካላቸውን ለመጉዳት ተሰናድቷል።

በተጫማሪም መስጂዱ የሚገኙ አባቶች በጭሱ ምክንያት እየደከሙ ነው። ደም የፈሰሳቸውም ራሳቸውን እየሳቱ ነው። የግል አምቡላንስ እንዳይገባ ተከልክሏል። በመርካቶ ዙሪያ ያሉ መስጂዶች ከበባ ላይ ናቸው። መርካቶና አካባቢው ላይ ያሉ ወጣቶች እየተያዙ ነው። መስጂድ ውስጥ ያሉትን አፍሰው ለመጫን ከታች እንደምትመለከቱት ባዶ ባሶች ተደርድረዋል።

ሰዓቱ ሳይሄድ የሚመለከተው አካል በተለይ የመጅሊስ ሰዎች በአስቸኳይ ለታገቱት ሙስሊሞች መፍትሄ ሊያፈላልጉ ይገባል።

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

||
t.me/MuradTadesse
445 viewsHusen Mohammed, 14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 15:24:55
ትናንት መጅሊስ ለዛሬ ተቃውሞ የለም ሲለን ያቋቋማቸው ዘጠኝ ኮሚቴዎች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር እያደረጉት ያለው ውይይት ጥሩ ውጤት ያመጣል ብለን ተስፋን ሰንቀን፣ ረብሻን ፈርተን፣ ሁከት ላለመቀስቀስ ነበር ዛሬ ተቃውሞ የለም ብለን በተደጋጋሚ እየተሰደብን ስንወተውት የነበረው።

የመንግስት ኃይሎች ግን ተቃውሞ ቢኖርም ባይኖርም ለመግደል አቅደው፣ ለሳምንት ያክል ተዘጋጅተው ነበርና የወጡት፤ እንኳን ሊቃወሙ ሰግደው ባልጨረሱ ወንድሞችና እህቶች ላይ የጥይት እሩምታ በአንዋር መስጅድ ከፍተው የቻሉትን ገ'ደሉ፣ ደበደቡ፣ አፈኑ።


ትናንት ተቃውሞ ያለን መጅሊስ ቢያንስ አሁን በአንዋር መስጅድ የታፈኑትን ሙስሊሞች ያስለቅቅልን።
428 viewsHusen Mohammed, 12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 15:20:33
ትናንት መጅሊስ ለዛሬ ተቃውሞ የለም ሲለን ያቋቋማቸው ዘጠኝ ኮሚቴዎች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር እያደረጉት ያለው ውይይት ጥሩ ውጤት ያመጣል ብለን ተስፋን ሰንቀን፣ ረብሻን ፈርተን፣ ሁከት ላለመቀስቀስ ነበር ዛሬ ተቃውሞ የለም ብለን በተደጋጋሚ እየተሰደብን ስንወተውት የነበረው።

የመንግስት ኃይሎች ግን ተቃውሞ ቢኖርም ባይኖርም ለመግደል አቅደው፣ ለሳምንት ያክል ተዘጋጅተው ነበርና የወጡት፤ እንኳን ሊቃወሙ ሰግደው ባልጨረሱ ወንድሞችና እህቶች ላይ የጥይት እሩምታ በአንዋር መስጅድ ከፍተው የቻሉትን ገ'ደሉ፣ ደበደቡ፣ አፈኑ።


ትናንት ተቃውሞ ያለን መጅሊስ ቢያንስ አሁን በአንዋር መስጅድ የታፈኑትን ሙስሊሞች ያስለቅቅልን።
422 viewsHusen Mohammed, 12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 16:01:35
እስክንድር ቢሸፍት እስከ ጓሮ . . . እስክንድር ነጋ ትናት ለሊት መያዙን አረግግጫለሁ

የባልደራሱ መስራችና ፕሬዚዳንት እስክንድር ነጋ መሰወር የከተማችን አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኖ መክረሙ ይታወሳል፡፡ ግለሰቡ በተሳሳተ የትግል ዓላማና ስልት አይኑ ታውሮ ለዥያ ለገናዥ አስቸግሮ እንዳልነበር አሁን ደግሞ ‹‹

እስክንድር ቢሸፍት እስከ ጓሮ›› እንዲሉ ቡሬ አካባቢ በአማራ ክልል የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ከእስክንድር በቁጥጥር መዋል ጋር በተያያዘ የሚወጡት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ጠፍቶ በከረመባቸው ወራት በሰሜን ሸዋና ምዕራብ ጎጃም አካባቢዎች ታጣቂ መልምሎ አዲስ አበባን ‹‹ነጻ›› ለማውጣት የትጥቅ ትግል ለማድረግ ሲሞክር ነበር፡፡

የተወሰኑ ተከታዮች ማፍራት የቻለው የአዲስ አበባው ነጻ አውጪ በምዕራብ ጎጃም በኩል ወደ ወለጋ ታጣቂዎች አስርጎ በማስገባት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጉም ይነገራል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲኖዶስ ውስጥ የተፈጠረው ችግር እንዲባባስም በአዲስ አበባ ለሚገኙት የባልደራስ ፓርቲ አባላት ስምሪት ሲሰጥ መቆቱ በመረጃ ተረጋግጧል፡፡

የእስክንድር በቁጥጥር ስር መዋል ኢሕጋዊ በመሆነ መንገድ የመንግሥት ሥልጣን ለመያዝ ለሚያልሙ አካላትና ግለሰቦች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡ ግለሰቡ በስመ ፓርቲ ሰላማዊ አማራጭና የትጥቅ ትግልን በመቀላቀለቅ ቅስቀሳ ሲያደርግ በትዕግስት ታልፏል፡፡ ከዚህም ብሶ መንግሥትን በኃይል ለመጣል ታጣቂ በመመልመል፣ በማደራጀትና ስምሪት በመስጠት ለጥፋት ቢሸፍትም ለሀገር ሰላምና ጸጥታ መከበር ከተሰለፉት ብርቱዎቹ የንስር አይኖች መሸሸግ አልቻለም ነበር፡፡

ገመዱ ሲረዝምለት ነጻ የሆነ የመሰለው ሁሉ ከዚህ ትምህርት ይውሰድ፡፡ ተጠያቂነት መኖሩንም ይገንዘብ . . .
311 viewsHusen Mohammed, 13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 03:00:39
ይህቺ የሲሚንቶ ፋብሪካ ፕሮጀክት የት ደረሰች

በነገራችን ላይ ሲሚንቶ ፋብሪካውን ለመገንባት 1 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሎ ነበር። እንደ ምንም ከብሔራዊ ባንክ ውስጥ ወዳጅ ከሆኑ ሰዎች ጋር በመመሳጠር የሆነ ጨላ አስይዘህ 400 ሚሊዮን ዶላር በፕሮጀክት ፕሮፖዛል ቅድሚያ ብትቀበል ..

ሶስት ሲኖ ትራክ መኪና ለአምስት ወራት የሲሚንቶ ፋብሪካው ይገነባበታል የተባለው አካባቢ ላይ አቧራ እንዲያቦኑ ታደርጋለህ .. አንድ መጋዘን ትገነባለህ ፣ አንድ የሚቆፍር ስካቫተር ታሳይና ትወክባለህ ..

ልክ ከአምስት ወር በኃላ የውጭ ምንዛሬ በማጣቴ ምክንያት ሲሚንቶ ፋብሪካው ስራ አቆመ ብለህ በሚዲያ ታስጮኸዋለህ ...

ከአንድ አመት በኃላ ደግሞ ከስሬያለሁ ብለህ ሶስት ሲኖ ትራክ ፣ አንድ ስካቫተርና ፣ አንድ የቆርቆሮ መጋዘንህን አስወርሰህ ላሽ ትላለህ ..

400 ሚሊዮን ዶላር በሿሿና በጓጓ ፣ ሰዎችን ተጠቅመህ በፕሮፖዛል ትበላና ... በዶላር ምንዛሪ ምክንያት ከሰርኩ ብለህ ታለቅሳለህ.. ሚዲያዎችም ድንኳን ጥለው ያስለቅሳሉ ..

ሀገር ወዳዱ ባለሃብት ሀገራቸውን ለመታደግ አስበው በጀመሩት ግዙፍ ፕሮጀክት ምክንያት በመንግስት እንዝላልነት ቢሊዮን ዶላሮችን ከሰሩ ብለው ይጮሃሉ። ህዝቡንም ያስጮሃሉ።

በቃ በፕሮጀክት ፕላን ከብሔራዊ ባንክ ጋር በመመሳጠር በብድር መዝረፍ ነው የአንዳንዱ ግለሰብ የሃብት ምንጭ ከዛን ብሩን በየጭፈራው ኮራ ብሎ ሲበትን ታየዋለህ
.
.
.
125 viewsHusen Mohammed, 00:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 22:16:07
𝓢𝓶𝓪𝓻𝓽𝓔𝓽𝓱𝓲𝓸_1677179909879.mp4
176 viewsHusen Mohammed, 19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 19:06:37 Official Says 4.4 Million Bales Of Hay Needed To Save 10pct Of Cattle In Borena Zone
Borena Zone of Oromia Regional State disclosed that at least 4.4 million bales of hay are needed to save 10 percent of the cattle being affected by the drought condition.
It is stated that more than 3 million livestock have already died due to starvation out of this 85 percent are cattle.
Saying that efforts are underway to salvage the remaining 230 cattle in dire condition, the Zonal Administration stated that 4.4 million bales of hay is desperately needed to for the rescue operation.
Jarso Boru, Chief Administrator of Borena Zone, said 135 quintals of animal fodder is needed; but, he said, only 1 percent of the required amount has been met.
Jarso said the emergency works may not be effective to save lives of the vulnerable cattle due to shortage of assistance, he said.
Borena Zone has so far sustained losses amounting to 33 billion birr due to the death of millions of livestock in the area, according to the Chief Administrator.
232 viewsHusen Mohammed, 16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 19:04:08
223 viewsHusen Mohammed, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 19:04:03
#ቦረና

ለራሱ ሳር በልቶ እድሜውን ማራዘም ባይችል ቤቱን አፍርሶ ከብቶቹን
ይመግባል። ችግሩ መኖሪያውን አፍርሶ ከብቱን እስከመመገብ ደርሷል። ያ
ሲያልቅ ሁሉም አለቀ ማለት ነው።
214 viewsHusen Mohammed, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ