2022-12-09 23:09:26
ይነበብ
የኦሮምያ ክልል መሪዎች ግን የትኛውን ነጻ ወረዳ ነው የሚያስተዳድሩት?
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት የሚከተሉት የኦሮምያ ቦታዎች የግጭት ማዕከሎች እንደሆኑ ተጠቅሷል:-
በምዕራብ ወለጋ ዞን ውስጥ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ፣ መነ ሲቡ ወረዳ (ነጆ መንዲ ከተማ)፣ ለታ ሲቡ፣ ቦጂ ድርመጂ (ቢላ ከተማ)፣ ነጆ ከተማ፣ ቆንዳላ ወረዳ፣ ቤጊ ወረዳ፣ ቅልጡ ካራ ወረዳ፤
በምሥራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ዴጋ ወረዳ፣ ሳሲጋ ወረዳ፣ ጊዳ አያና ወረዳ፣ ኪረሙ ወረዳ፣ ጉትን ወረዳ፣ ሊሙ ወረዳ፣ ጅማ አርጆ፤
በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ውስጥ ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ (አሊቦ፣ ጃርደጋ እና ጃርቴ ከተሞች)፣ አሙሩ ወረዳ (አሙሩ ከተማ፣ አገምሳ ከተማ እና ከ10 በላይ ቀበሌዎች)፣ ሆሮ ቡልቅ ወረዳ፣ ጉዱሩ ወረዳ፤
በቄለም ወለጋ ዞን ውስጥ ሀዋ ገላን ወረዳ (መንደር 20 እና 21)፤
በምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ ሜታ ወልቂጤ ወረዳ፣ አደዓ በርጋ ወረዳ፣ ጮቢ ወረዳ፣ ጀልዱ ወረዳ፣ አቡና ግንደበረት ወረዳ፣ ግንደበረት ወረዳ፣
በምሥራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ ቦሰት ወረዳ፣ ዱግዳ ወረዳ፣ ፈንታሌ ወረዳ፤
በአርሲ ዞን ውስጥ ጀጁ ወረዳ፣ መርቲ ወረዳ፤
በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ኩዩ ወረዳ ወረጃርሶ ወረዳ፣ ደራ ወረዳ፤
በኢሉ አባ ቦር ዞን ውስጥ ደርሙ ወረዳ፣ አሊጌ ሰቺ ወረዳ፤
በቡኖ በደሌ ዞን ውስጥ ጨዋቃ ወረዳ፣ ዳቦ ሃና ወረዳ፣ መኮ ወረዳ፣ ዴጋ ወረዳ።
በእነዚህ ሁሉ ቦታዎች ሸኔ ከተንቀሳቀሰ፣ እንግዲህ ሽመልስ አብዲሳ የሚያስተዳድረው ወረዳ የትኛው ነው? ክልሉን አረጋግቶ የሚመራ የተሻለ ሰው ጠፋ ማለት ነው? ከዚህ የበለጠ የክልሉን አመራር ውድቀት ማሳያስ አለ?
ሰላም በሃይል ብቻ አይመጣም። ከሃይል እኩል የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስራዎች መሰራት አለባቸው። የሽመልስ አስተዳደር ግን በሶስቱም መስፈርቶች በከባዱ ወድቋል። ይህን አመራር ይዞ በመቀጠል ኦሮምያን ማረጋጋት ከተቻለ እናያለን። እንደኔ እምነት ግን አመራሩ ከዚህ በላይ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም።
396 viewsHusen Mohammed, 20:09