Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ assebpress — አዲስ መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ assebpress — አዲስ መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @assebpress
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.82K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-01-21 16:07:13
ሰበር!

ጥር 13/2015 (አዲስ አበባ): የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አምስት ከፍተኛ አባላቱን አገደ

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በነበረው ስብሰባ ተጠያቂነት እሰከሚረጋገጥ ፦

1. ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
2. ፈትለወርቅ ገብረዝጊሔር
3. ጌታቸው ኣሰፋ
4. ኣለም ገብረዋህድ እና
5. ጌታቸው ረዳን ከማዕከላዊ ስራ ኣሰፈፃሚ አባልነታቸው አግዷል።
ኮሚቴው ከጥር 7 እስከ 10/2015 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ስማቸው ከላይ የተጠቀሰውን አባላቱን ከተጠያቂነት ጋር በተያያዘ አግዷል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ያገዳቸው በጦርነቱ ለደረሰው ኪሳራ ሁሉ ተጠያቂ እናንተ ናችሁ በሚል እንደሆነም የመረጃ ምን ጮቻችን አረጋግጠዋል።
825 viewsHusen Mohammed, 13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 15:58:19 ማን ታግዶ ማን ይቀራል ጌታቸው አሰፋ ከታገደ እነ አባይ ፀሃዬ፣ እነ ስዩም መስፍን፣ እነ መሌ ሳይቀሩ መታገድ አለባቸው።
681 viewsHusen Mohammed, 12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 15:58:08
ሰበር!

ጥር 13/2015 (አዲስ አበባ): የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አምስት ከፍተኛ አባላቱን አገደ

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በነበረው ስብሰባ ተጠያቂነት እሰከሚረጋገጥ ፦

1. ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
2. ፈትለወርቅ ገብረዝጊሔር
3. ጌታቸው ኣሰፋ
4. ኣለም ገብረዋህድ እና
5. ጌታቸው ረዳን ከማዕከላዊ ስራ ኣሰፈፃሚ አባልነታቸው አግዷል።
ኮሚቴው ከጥር 7 እስከ 10/2015 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ስማቸው ከላይ የተጠቀሰውን አባላቱን ከተጠያቂነት ጋር በተያያዘ አግዷል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ያገዳቸው በጦርነቱ ለደረሰው ኪሳራ ሁሉ ተጠያቂ እናንተ ናችሁ በሚል እንደሆነም የመረጃ ምን ጮቻችን አረጋግጠዋል።
721 viewsHusen Mohammed, 12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 21:44:43
ሰበር ዜና
በመላው ትግራይ No More TPLF ማለት ተከትሎ
የመቐለ ወጣት ህወሓት በቃን ውጡልን ኣንፈልጋቹም ብሎ ድምፁን ለማሰማት ተደራጅቶ ነበር፤ይህ ኣንዳንድ የTPLF ኣሽከሮች ሚስጥሩን በማስወጣታቸው መቐለ ጥምቀት እንዳይከበር official ክልከላ ተደረገ።
438 viewsHusen Mohammed, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 16:04:01
ምክር ቤቱ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሹመት አጸደቀ

ጥር 9/2015 (ዋልታ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትን ሹመት አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ቴዎድሮስ ምሕረት ከበደን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አድርጎ በ3 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ሹመታቸውን ያጸደቀው።

በተመሳሳይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አበባ እምቢአለ በሙሉ ድምፅ ሹመታቸውን ያፀደቀ ሲሆን ተሿሚዎችም በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ መፈጸማቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
549 viewsHusen Mohammed, 13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 14:38:37
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንት ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዚደንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊና ምክትላቸው አቶ ሰሎሞን አረዳ በፈቃዳቸው ከኃላፊነት ለመልቀቅ ለፖርላማ ያቀረቡት ደብዳቤ ዛሬ ጥር 9 2015 ዓም ከሰዓት በኋላ በምክር ቤቱ እየታየ ነው።
ምንጭ ሪፖርተር
495 viewsHusen Mohammed, 11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 21:02:31
ዶ/ር ደብረፅዮን ምን አሉ

በዛሬው እለት በመቀሌ በተካሄደው የአትሌቶች ውይይይ ላይ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን ስለደራርቱ ይህንን ብለዋል

" ከሁሉም በፊት በራሴና በትግራይ ህዝብ ስም ደራርቱን ላመሠግን እወዳለሁ ፤ ከዚህ ቀደም ወደ ጦርነት እንዳንገባ ወደ'ኔ እየደወለች ነገሩ የከፋ ደረጃ እንዳይደርስ እባካችሁ ለህዝባችሁ ስትሉ ሁለታችሁም ተሸነፉ ስትል ስለሰላም ያላትን ፅኑ አቋም ስታንፀባርቅ ነበር ። ደራርቱ በችግራችን ወቅት ከጎናችን የነበረች የሰላም ሰው በመሆኗ ደግሜ ደጋግሜ አመሠግናታለሁ ፤ ከትግራይ አትሌቶች ጎን እንደ እናት በመሆን ብርታት የሆነቻቸው ደራርቱ የትግራይ አትሌቶች በችግር ውስጥም ሁነው በአለም አደባባይ የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ከፍ ማድረግ በመቻላቸው ክብር ይገባቸዋል ፤ የፅናትም ተምሳሌቶች ናቸው።" ብለዋል።
226 viewsHusen Mohammed, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 21:02:16
ህወሃት ከባድ መሳሪያ ማስረከብ ጀምሯል
በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካካል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተከትሎ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት የተቋቋመው የቁጥጥር እና ክትትል ቡድን ስራውን በይፋ መጀመሩን አስታወቀ።

የቡድኑ አበላት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተገለፀው በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የከባድ መሳርያ ርክክብ ስራ መጀመሩን ገልፃል።
በጋዜጣዊ መግለጫው የቁጥጥር እና ክትትል ቡድን አባላት ጨምሮ የሁለቱም ወገኖች ወታደራዊ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት አሁንም ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
የሰላም ስምምነቱ በቀጣይነት ተግባራዊ እንዲሆን ሌሎች ከፍተኛ ትኩረት እና ስራ የሚሹ ጉዳዮች እንዳሉም በመግለጫው ተመላክቷል።

=====================
221 viewsHusen Mohammed, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 20:50:31
የመቀሌ ነዋሪ ዛሬ አንድ የኢትዮጲያ አየር መንገድ አውሮፕላን እነ ሬድዋንን ይዛ በሰማያ ስታንዣብብ ሲያይ በጩሀት እና በእልልታ ከተማዋን ሲያናውጣት በጆሮው የሰማ ዳዊት ከበደ የተባል አንድ ልክስክስ ተላላኪ፥ እንዲህ ሲል አማረረ ... (ትርጉም) "የመራከው ትግል መጨረሻው ወደ ሚሊዮን የሚጠጋ ሞቶ የተቀረው እነ ሬድዋንን አይቶ በእልልታ የሚጨፍርን መፍጠር ከሆነ፥ ምህረቱን ያውርድ ነው የሚያስብለው"

ጋዜጠኛ መድህን ገ/ስላሴ መለሰችለት፥ "ይሄ እልል ካላስባለ ምን እልል ያስብለላል?"
305 viewsHusen Mohammed, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 18:47:14
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ስልክ የሚጠልፍ ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑ ተገለጸ

ረቡዕ ታሕሳስ 12 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ ‹‹ዩኤፍ ኢዲ›› የተሰኘ ከግለሰቦች የእጅ ስልክ መረጃ በድብቅ በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችለውን ቴክኖሎጂ ከእስራኤል መግዛቷ ተሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ቴክኖሎጂውን ከእስራኤሉ የዲጂታል መረጃ (ሴሌብሪቲ) ድርጅት የገዛ ሲሆን፣ ይህም በተለይ የተቃዋሚ ኃይሎችና ጋዜጠኞችን የእጅ ስልክ ለመጥለፍ  በእጅጉ ያግዛል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፈረንጆች 2021 ጀምሮ በማዕከላዊ መንግስቱና በትግራይ ኃይሎች መካከል በተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት ይህን ቴክኖሎጂ ሲጠቀም መቆየቱም ተነግሯል፡፡

ቴክኖሎጂው በይለፍ ቃል የታሰሩና የተያዙ ስልኮችን ለመጥለፍ ባለስልጣናት የሚጠቀሙበት ሲሆን፣ የሚዲያ ፋይሎችን እና የፅሁፍ መልዕክቶችን፣ የጥሪ ታሪኮችን፣ እውቂያዎችን እና ሌሎችንም ጨምሮ በስልኮች ውስጥ የተከማቸውን ሁሉንም መረጃዎች እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

ሃሬትዝ ድረገጽ ይዞት በወጣው ዘገባ፣ የእስራኤሉ የቴክኖሎጂ ተቋም ደንበኞች ጨቋኝ ስርዓት የነበራቸው እንደ ቤላሩስ፣ ቻይና፣ ሆንክ ኮንግ፣ ኡጋንዳ፣ ቬንዙዌላ፣ ኢንዶኔዥያ እና ፊሊፒንስ ይገኙበታል፡፡

እስራኤላዊው የሰብዓዊ መብት ጠበቃ ኢታይ ማክ ለእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴርና ለሴሌብሪቲ ኩባንያ በላኩት ደብዳቤ፣ “ኩባንያው ለኢትዮጵያው አፋኝ ስርዓት የሚያደርገውን የቴክኖሎጂ ሽያጭ እንዲያቆም” ጠይቀዋል ተብሏል፡፡

‹‹ዩኤፍ ኢዲ›› የሚባለው እስራኤል ሰራሽ የሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ሰላዮች የግለሰቦችን የስልክ መረጃ በቀላሉ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ቴክኖሎጂ ነው፡፡
257 viewsHusen Mohammed, 15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ